Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  law  የሀሰት የወንጀል ምርመራ መዝገብ አደራጅተው ከባለሃብት ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ ፖሊሶች ተከሰሱ
law

የሀሰት የወንጀል ምርመራ መዝገብ አደራጅተው ከባለሃብት ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ ፖሊሶች ተከሰሱ

Ethioreview newsEthioreview news—December 10, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሀሰተኛ የወንጀል ምርመራ መዝገብ በማደራጀት አንድን ባለሃብት በማስፈራራት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ አራት በአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና ሁለት ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ። ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ ያቀረበባቸው ተከሳሾች 1ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው መኩሪያ ማሞ ወይም (መስፍን ማሞ)፣ 2ኛ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቂሊንጦ ፖሊስ ጣቢያ የክትትል ቲም ሀላፊ ኢንስፔክተር ዘለቀ ጥላሁን፣ 3ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ዘውዴ አሰግደው፣ 4ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ዋ/ሳጅን መለሰ ማርቆስ፣ 5ኛ በፖሊስ ጣቢያው የክትትል አባል ምክትል/ሳጅን አጅቦ ተፈሪ እና 6ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው ተገኔ ሀ/ማርያም ወልዴ ናቸው።

ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ)፣ አንቀጽ 33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር (2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች የመንግስት ስራ ላይ በመስራት ላይ እያሉ ከ1ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ላይ ጉዳት እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ባለሃብት ግለሰብ ላይ 1ኛ ተከሳሽ ሀሰተኛ የወንጀል ጥቆማ አቅራቢ ሆኖ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ጥቆማ ያቀረበ በማስመሰል ከ2ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች ከህጋዊ አሰራር ውጭ የምርመራ መዝገብ እንዲደራጅ አድርገው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል

More stories

ግማሽ ሚሊየን ብር በጥሬው ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ

February 1, 2022

ዐቃቤ ህግ በቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የክስ መዝገብ ሌሎች ድርጅቶችን አካቶ ለመቅረብ ጠየቀ

July 7, 2023

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የተቋቋመው የሚኒስቴሮች ግብረ-ሀይል ስራውን በይፋ ጀምሯል

November 29, 2021

ሰው በማገት ወንጀል የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች 22 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው

February 16, 2022

በዚህም ግለሰቡን አስረው “የወንጀል ምርመራው እንዲቋረጥልህ ገንዘብ መክፈል አለብህ” በማለት አስፈራርተው የግል ተበዳዩ ለጊዜው ባልተያዘ ምስጋና ዓለሙ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር በነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም 180 ሺህ ብር፣ በመስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም 300 ሺህ ብር ገቢ እንዲያደርግላቸው ማስገደዳቸው በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ለጊዜው ባልተያዘ ለማ ባጃ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ በመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም 200 ሺህ ብር ገቢ ያስደረጉ በመሆኑን በክሱ ዝርዝር ላይ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ በ3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች አማካኝ የግል ተበዳዩን ከህግ አግባብ ውጭ በጣቢያው አስረው ካቆዩ በኋላ በ4ኛ ተከሳሽ ስም ከአዋሽ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ 200 ሺህ ገቢ ያስደረጉ መሆኑ በክሱ ተገልጿል።

በ6ኛ ተከሳሽ ስም ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 300 ሺህ ብር ገቢ ካስደረጉ በኋላ ከዚሁ ገንዘብ ላይ በ4ኛ ተከሳሽ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 200 ሺህ ብር ማስተላለፋቸው ተጠቅሷል።

ከዚሁ ገንዘብ ላይ ደግሞ ለ3ኛ ተከሳሽ እና ለ2ኛ ተከሳሾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳባቸው ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር የተላለፈላቸው መሆኑ በክሱ ተዘርዝሯል።

ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱ የሚያስገኘውን አጠቃላይ ውጤት በመቀበል በሀሰተኛ የምርመራ የወንጀል መዝገብ በማደራጀት ግለሰቡን ከህግ ውጪ በማሰር በአጠቃላይ ከግል ተበዳዩ 1 ሚሊዮን 180 ሺህ ብር በመቀበል ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መሆኑ ተጠቅሶ በልዩ እና ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈጸም ክስ ቀርቦባቸዋል።

ዐቃቤ ሕግ ከክሱ ጋር የሰውና የሰነድ ማስረጃ ዝርዝር አያይዞ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾቹ ችሎት ቀርበው የክሱ ዝርዝር እንዲደርሳቸው ከተደረገ በኋላ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 4 ቀን 2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ ፋና

law
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት ያደረሰው ተከሳሽ ተፈረደበት፤ ከ132 ሚሊየን ብር በላይ ታክስ ያጭበርበሩ ተያዙ
ከበሽር አል አሳድ ውድቀት በኋላ ሶሪያ እንደ ሊቢያ ወይስ በተስፋ ጉዞ?
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
law

የአዲስ አበባ የከንቲባ ፅ.ቤት ፕሮቶኮልን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌብነት ተከሰው ተፈረደባቸው

July 23, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2