Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  ENTERTAINMENT  “በምድር ንጉሥ፣ በሰማይ ቅዱስ”
ENTERTAINMENT

“በምድር ንጉሥ፣ በሰማይ ቅዱስ”

Ethioreview newsEthioreview news—January 8, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ወልድያ፡ ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) እንደ ንጉሥ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፣ እንደ ቅዱስ በቅድስና ከሰማየ ሰማያት ይወጣል። እንደ ንጉሥ ለሕዝቦቹ ፍርድን ይሰጣል፤ እንደ ቅዱስ በጸሎቱ ምህረትን ያሰጣል። እንደ ካህን ኪዳን ያደርሳል፣ አሀዱ ብሎ ይቀድሳል፤ ያወድሳል። እንደ ቅዱስ በቅድስና ይመላለሳል።

የቤተ መንግሥት ንጉሥ፣ የቤተ ክህነት ቅዱስ ነው። ንግሥናው ቅድስናውን አላስረሳውም። አድናቆት እና ሙገሳ አላስታበየውም። ከንግሥናው ሳይጎድል፣ ከቅድስናውም ዝቅ ሳይል በትህትና ኖረ እንጂ። ቃሉ ትደመጣለች። ምክሩ ትሰማለች። ሰላምታው ትናፈቃለች። አኗኗሩ ታስቀናለች።

እንደ አብርሃም በድንኳን ያድራል፤ ለጌታው ግን በአለት ላይ ቤት ይሠራል። እንደ አጣ ሰው ይራባል፤ የተራቡትን ግን ያጠግባል። እንደ ንጉሥ እጅ ንሱልኝ ከማለት ይልቅ በነጋ በጠባ ለአምላኩ እጅ ይነሳል። በምትጣፍጥ አንደበቱ የአምላኩን ስም እየጠራ ያወድሳል።

በጸሎት፣ በስግደት ይበረታል። በቅድስናው ጥበብ ተገለጠለችለት። አለት እጅ ሰጠችለት። ምድርን ሰማይ አደረጋት። ሰማይንም በምድር ሠራት። ቅድስቲቱን ሥፍራ ለዓለም ሁሉ ገለጣት። የምሥጢር ማኅተም አተመባት። የማይጠፋ ቃል ኪዳን አኖረባት። ንጉሥ ወቅዱስ ላሊበላ።

መጽሐፍ እንዲህ ይላል የአማኞች ንጽሕናም ከስጋው አራቀም። የመላእክት ትጋት ሀብት ከእርሱ ጋር ትኖራለች። የሁሉም የአምላክ ወዳጆች በረከትም በመሐል ራሱ አለች።

የበዛች የበጎ ሥራው ድካም ከእነርሱ ጋር አስተካክለዋለችና። ጻድቅ ነው። ሰውነቱ በጭምትነት በትር የተቀጣ ነውና። ሰማዕትም ነው፤ የበደለው ሳይኖር በግፍ ከሀገር ወደ ሀገር ሲሰደድ እና ሲቀጣ ኖሯልና።

ታላላቆቹም መረቁት፤ እርሱ ከፍ አድርጓቸዋልና። ሽማግሌዎችም መረቁት፤ እርሱ በእርጅናቸው ደግፏቸዋልና። ሕጻናትም መረቁት፤ እርሱ አሳድጓቸዋልና። ድሆችም መረቁት፤ እርሱ አረጋግቶ አሳድጓቸዋል። ድህነታቸውን እስኪረሱ ድረስ ለቅሷቸውን አስጥሏልና።


ባልቴቶችም መረቁት፤ እርሱ ከሀዘናቸው አረጋግቶ ችግራቸውን አስወግዷልና። ባለጸጎችም መረቁት፤ እርሱ አክብሯቸዋልና። የተጋፋቸውም ነገር የለምና። የእርሱን ከመስጠት በስተቀር ከእነርሱ የወሰደባቸው የለምና።

ችግረኞችም መረቁት፤ እርሱ ለአሰቡት ሁሉ እየረዳ መጠጊያ ኾኗቸዋልና። የታረዙትም መረቁት እርቃናቸውን ሸፍኗልና። የተራቡም መረቁት እርሱ መግቧቸዋልና። የተጠሙትም መረቁት፤ እርሱ በጣፈጠ ባማረ መጠጡ አርክቷቸዋልና።

ባሕታውያንም መረቁት እርሱ ረዳት እና መጋቢ ሁሉንም በሁሉ ኾኖላቸዋልና ተብሎ ተጽፏል።

ንጉሥ ወቅዱስ ላሊበላ ለንግሥናውም  ለቅድስናውም የተመቻቸ እና የተገባ ነው።

የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ዲያቆን ተካ ውቤ ቅዱስ ላሊበላ ኢትዮጵያን ያስዋበ፣ ንጉሥም፣ ካህንም፣ ቅዱስም ኾኖ ኢትዮጵያን የመራ ታላቅ ነው ይላሉ። በአካለ ነፍስ ወደ ሰማይ ያረገ በሰማይ የተመለከታቸውን በምድር የሠራ፣ ሰውና እግዚአብሔር የሚገናኙበትን ያነጸ ቅዱስ ነው።

መላእክት የሚመሩት፣ የሚያግዙት፣ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚገለጥበት ንጉሥም ቅዱስም ነው ይላሉ። ንጉሥ ወቅዱስ ላሊበላ ኢትዮጵያን በአራት አሥተዳደር ከፍሎ ያሥተዳደረ፣ ትሁት፣ ደግ እና ቅን ነበር ነው የሚሉት።  የአሥተዳደር ሥርዓቱ ጥበብ የተመላበት። በፍቅር የሚመራ ነውም ይላሉ።

አምላክ የሚመሠገንባቸውን፣ ኢትዮጵያ ከፍ ብላ የምትታይባቸውን አብያተ ክርስቲያናትን ያነጸ። አምሣለ ኢየሩሳሌምን በኢትዮጵያ የሠራ ታላቅ ነው።  ፍቅርን እንጂ ጠብን የማይወድ፣ ሀገሩን የሚያስከብር ነው ይሉታል።

የእርሱ የእጅ ሥራዎች ቅድስናውን የሚመሰክሩለት፤ ታላቅነቱን የሚገልጡለት፤ የጥበብ ቀንዲልነቱን የሚያሳዩለት፤ ኢትዮጵያን ያንቆጠቆጠ፣  በክብር ዙፋን ላይ ያስቀመጠ ነው ይላሉ።

ቅዱስ ላሊበላ ኀያላን የሚያከብሩት፣ በሩቅ ያሉት እና  አሳዳጅ የበዛባቸው ይታደገናል፤ ጠላቶቻችን በኀይሉ ድል ይነሳልናል ብለው የሚጠብቁት ታላቅ ነው ይሉታል። የእርሱ ኀይልም መንፈስ ቅዱስ ናት። ከእጁ የሚሰጠው እስከሚያጣ ድረስ ለደሀዎች የሚሰጥ ሩህሩህ ነው።

ቅዱስ ላሊበላ ኢትዮጵያ በዓለሙ ፊት ጎብኚዎች እንዲበዙላት፤ አድናቂዎቿ እንዲበረክቱላት፣ አብያተ ክርስቲያናትን የሠራ፤ የኢትዮጵያውያንን የቀደመ ጥበብ ያሳየ ድንቅ አባት ነው። የኢትዮጵያን ታላቅነት በአለት ላይ ያሰረጸ ነውም ይሉታል። የእርሱ የእጅ ሥራዎች የማንነት መገለጫዎች ናቸው።

የእርሱ ከተማ የቀደመችዋ ሮሃ የኢትዮጵያ የሥልጣኔ መብራት ናት። ሮሃ ማለት የጸዳ፣ ንጹሕ፣ ቅድስና ያለበት ቦታ ነው ይላሉ። በደብረ ሮሃም ሰው እና መላእክት ይገናኛሉ።

በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም የአራቱ ጉባኤያት መምህር ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ በዓለም ላይ የማይስማሙ ንግሥና እና ቅድስና የተስማሙለት ቅዱስ ነው ይላሉ።

የዚህ ዓለም የመጨረሻ አክሊል የንግሥና አክሊል ነው፤ የዚህኛው የዓለም የመጨረሻ የደስታ አክሊል የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚያወርስ ቅድስና ነው።

ላሊበላም የዚህኛውም የዚያኛው የደስታ አክሊል የተስማሙለት ነው ይላሉ። ጦር ሳያነሳ ሀገር እና ሕዝብ ይገብርለታል።  እንደ ንጉሥነቱ ፍትሕ ይሰጣል፤ እንደ ካህንነቱ እግዚአብሔር ይፍታህ ብሎ ከሐጥያት ይፈታል ብለዋል።

እርሱ ማዕከላዊ መንግሥት አለው። ወደ ሰማይ ለእግዚአብሔር፣ ወደ ምድርም ለሰው የቀረበ መንግሥትን ይዟልና። በዘመኑ ሰዎች ያላለቀሱበት፤ ደሀዎች ያልተበደሉበት ነው ይላሉ። መንግሥትነትን በሕዝብ ዘንድ ያስወደደ፣ ሀገርን ሰላም ያደረገ፣ ሕጻናትን ያሳደገ፤ ኀይሉ ክህነቱ  የኾነ፤ ክህነቱ ለንግሥናው አብነት የኮነችው ጻድቅ ነው ይሉታል ሊቁ። 

ሀገርን አንድ ያደረገ፣ ለኢትዮጵያ ጌጧን የሰጣት፣ ሰማይን በምድር ያበጃትም ነው ይላሉ ሊቁ። በሰማይ ሀገር አለን እንላለን፤ የሰማይ ሀገራችን ደግሞ ላሊበላ ቀርጾ አስቀምጦ ያሳየናል።

ሰማይና ምድርን አንድ አድርጎ ሰጥቶናል። የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት አምሳያቸው  በምድር የለም። በቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ያለ ምክንያት እና ያለ ምልክት የተሠራ የለም። ሁሉም ሃይማኖትን ይናገራል እንጂ ነው የሚሉት።

ላሊበላ በጨለማ ውስጥ የሚያበራ እንቁ ነው። ቅዱስ ላሊበላ ሰባት ጊዜ የነጠረ የወርቅ ጽዋ ነው። ቅዱስ ላሊበላ የጥፋት ትል ጥርስ ያልነካው ስንዴ ነው ተብሎ ተጽፏል።

በምድር ንጉሥ፣ በሰማይ ቅዱስ ነውና እንደተመሠገነ ይኖራል፤ በትውልዶች ሁሉ ይዘከራል።

አሚኮ

entertainment
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

ኢትዮጵያ ውብ ሀገር ናት፤ ላሊበላ ደግሞ እርሷን ማያ ድንቅ መስኮት! 
የትግራይ ወርቅ – ከጦርነት ማግስት ሌላው የህዝቡ መከራ፤ መርዝ ስጋት ሆኗል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ራስ – በኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች IA መጠቀም የሚያስችለው መተግበሪያ

August 21, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news