Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  law  አስፈራርተው ጥፍጥፍ ወርቅ ወስደዋል የተባሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ
law

አስፈራርተው ጥፍጥፍ ወርቅ ወስደዋል የተባሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ

Ethioreview newsEthioreview news—April 16, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከግለሰብ ከግለሰብ አስፈራርተው ጥፍጥፍ ወርቅ ወስደዋል የተባሉ ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የግራ ቀኝ ሚስረጃ መርምሮ የቅጣት ውሳኔውን አሳልፏል።

የቅጣት ውሳኔ የተወሰነባቸው ተከሳሾቹ÷ 1ኛ ተከሳሽ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ አባልና የቀድሞ ወታደር የነበረው ሻለቃ ፀጋዬ ሀይሉ፣ 2ኛ ደበበ ገመዳ፣ 3ኛ ሰናይት ብርሃኑ እና 4ኛ አለማየሁ ደነቀ ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቢ ህግ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ በተከሳሾቹ ባቀረበው ዝርዝር  ክስ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾቹ በየካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም የግል ተበዳይ ከትግራይ ይዞት የመጣውን 1 ሺህ 611 ግራም ጥፍጥፍ ወርቅን ለማሰራት ወደ ፒያሳ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር አብረው ሲጓዙ  ወርቁን እንዲወስዱበት ለማድረግ 3ኛ ተከሳሽ ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ጋር መስማማቷ ተጠቅሷል።

በስምምነታቸው መሰረት 3ኛ ተከሳሽ  ቃተና ተብሎ ወደ ሚጠራ ምግብ ቤት ምሳ እንብላ በማለት  የግል ተበዳይን ወደ ምግብ ቤቱ በመውሰድ ምግብ ቤት  እንደደረሱ  1ኛ ተከሳሽ የወታደር ልብስ በመልበስ ራሱን ወታደርና የፀጥታ አካል አስመስሎ  የግል ተበዳይ ወደነበረበት ተሽከርካሪ በመቅረብ ተበዳይ ተቀምጦበት ወደ ነበረው የሹፌር  ወንበር እንዲወርድና ከኋላ እንዲቀመጥ ካደረገው በኋላ ራሱ ተከሳሹ ወደ መኪናው ገብቶ ጋቢና ከተቀመጠ በኋላ መኪናው በህገወጥ መንገድ ሀገር ውስጥ የገባ  ነው በማለትና መኪናውን በጂፒኤስ እየተከታተሉት መሆኑን በመግለጽ፤ መኪናው ይታሰራል በማለት እንዳስፈራራው በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።

2ኛ ተከሳሽ ደግሞ የመኪናው የኋላ ወንበር ላይ ገብቶ በመቀመጥና ሽጉጥ አውጥቶ የግል ተበዳይ ጭንቅላት ላይ በመደቀን የግል ተበዳዩ ይዞት የነበረውን 10 ሚሊየን ብር የሚገመት 1 ሺህ 611 ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ  ነጥቆ መውሰዱ በክሱ ተመላክቷል።

ወርቁን ከነጠቁት በኋላ ተበዳዩን ከመኪናው በማስወረድ በ3ኛ ተከሳሽ አሽከርካሪነት ጥፍጥፍ ወርቁን ይዘው በርቀት ሆኖ ሲጠብቃቸው ከነበረ ከ4ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ወርቁን ፒያሳ አካባቢ በመውሰድ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ለሌለው ነጋዴ በ3 ሚሊየን 415 ሺህ በመሸጥ እና ገንዘቡን በተለያየ መጠን በመከፋፈል ለግል ጥቅም አውለዋል በማለት ዐቃቢ ህግ  ክስ አቅርቦባቸዋል።

በዚህ መልኩ የቀረበባቸውን ክስ ዝርዝር  ተከሳሾች በወቅቱ  መደበኛ ችሎት ዝግ ስለነበር በተረኛ ችሎት ቀርበው ክሱ ከደረሳቸው በኋላ የክስ ዝርዝሩ በችሎት በንባብ ተሰምቶ ነበር።

ከዚህም በኋላ ተከሳሾች በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው÷ የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቢ ህግ የግል ተበዳይን ጨምሮ  ምስክሮችን አቅርብ አሰምቶ ነበር።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቢ ህግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ቢሆንም፤ ተከሳሾች የዐቃቢ ህግ ማስረጃን ማስተባበል አለመቻላቸው ተጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶባቸዋል።

በዚህም በተለይም 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በ1ኛ ክስ ማለትም በወንጀል ህግ አንቀጽ 670 በወንብድና ወንጀል እና በ2ኛ ክስ በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ማለትም በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጸሰ 29 ንዑስ ቁጥር 1 ስር ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን፣

4ኛ ተከሳሽ ግን በ2ኛ ክስ ብቻ በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 ንዑስ (1) ስር በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ጥፋተኛ ተብሏል።

ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ አጠቃላይ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት በመመርመርና በመያዝ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በነበረ ቀጠሮ÷ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን እያንዳንዳቸው በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ30 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል፡፡

4ኛ ተከሳሽን ደግሞ በ2ኛ ክስ ብቻ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

በታሪክ አዱኛ fana

law
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
18 “የአብን” የፓርላማና ክልል ተመራጮች ለምን ከአንድ አካባቢ ብቻ ተወከሉ? በለጠ ሞላ “ዝም አንልም” አሉ
አሜሪካ በኤርትራ ጨምሮ በሌሎችም ሀገራት ያሉ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
law

የአዲስ አበባ የከንቲባ ፅ.ቤት ፕሮቶኮልን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌብነት ተከሰው ተፈረደባቸው

July 23, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2