Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  ECONOMY  የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች አንዱን መግዛት ይፈልጋል
ECONOMY

የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች አንዱን መግዛት ይፈልጋል

Ethioreview newsEthioreview news—May 22, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ “ቅርንጫፍ ለመክፈት ወይም አዲስ ለማቋቋም” ሳይሆን በሥራ ላይ ከሚገኙት አንዱን መግዛት ይፈልጋል። በታኅሳስ 2018 ገደማ የውጪ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። መጪዎቹ ወራት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ በርከት ያሉ ለውጦች የሚያይበት ይመስላል።

ኬንያዊው ፖል ሩሶ ባለፈው ሣምንት በአዲስ አበባ የተገኙት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የሚመሩት ኬሲቢ ግሩፕ አዲስ ወደሚከፈተው ገበያ ለመግባት እንደቆረጠ ለማሳወቅ ጭምር ነበር። ኩባንያቸው በሥሩ በሚገኙ ድርጅቶች በኩል በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በኢንቨስትመንት እና በባንክ ሥራ ላይ የተሠማራ ነው።

ኬሲቢ ግሩፕ ባለፉት ዓመታት ዐይኑን በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ጥሎ ቆይቷል። ፖል ሩሶ “እዚህ የተገኘሁት ኬሲቢ በኢትዮጵያ እንደሚገባ ለመግለጽ ነው” ሲሉ ኩባንያቸው ያሰበውን የሚያሳካበት ጊዜ ለመድረሱ ጥቆማ ሰጥተዋል። በቀጠናው ትልቁ አበዳሪ የሆነው ኬሲቢ ግሩፕ 15.5 ቢሊዮን ዶላር ጥሪት ያለው ግዙፍ ኩባንያ ነው። በችርቻሮ የባንክ ሥራ ከደንበኞቹ በተጨማሪ ለግዙፍ የመሠረተ-ልማት እና ኢንዱስትሪ ግንባታዎች፣ ለንግድ እና ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ብድር ያቀርባል።

ፖል ሩሶ የሚመሩት ኬሲቢ ግሩፕ በአሁኑ ወቅት የኬንያ ንግድ ባንክ እና የኬንያ ብሔራዊ ባንክን ያስተዳድራል። በደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ርዋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ታንዛኒያ የባንክ ሥራዎች የሚያከናውኑ ኩባንያዎችም በሥሩ ይገኛሉ። ኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤቱ በሚገኝበት በኬንያ፣ በርዋንዳ እና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዳደረገው ሁሉ በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች አንዱን መግዛት ይፈልጋል።

More stories

ኢትዮጵያና ሩሲያ የብርና የሩብል የቀጥታ የምንዛሪ ልዉዉጥ ማድረግ ጀመሩ

July 14, 2025

አዲሱ ህዳሴ ማዳበሪያ ፋብሪካ፤ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ከአፍሪካ አንደኛ!

March 20, 2025

አይኤምኤፍ እና ኢትዮጵያ በተራዘመ የብድር አቅርቦት የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ ደረሱ፣ 345 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች

September 28, 2024

የተሟላ የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ በህግ የሚገደዱ ግብር ከፋዮች  የተሟላ የሂሳብ መዝገብ በመያዝ ካልመጡ በስተቀር አይስተናገዱም

May 5, 2025

“ቅርንጫፍ ለመክፈት ወይም አዲስ ለማቋቋም እንደማንፈልግ ግልጽ ነን። በተደነገጉት ደንቦች መሠረት ግዢ ለመፈጸም እያሰብን ነው” ሲሉ የኪሲቢ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፖል ሩሶ ተናግረዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ገበያ የሚሰጠውን ዕድል እየተመላለሱ መታዘባቸውን የገለጹት ፖል ሩሶ “ለውጥ አይቻለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢትዮጵያ የባንክ ገበያዋን የምትከፍትበት መጪው ጊዜም ብሩህ እንደሚሆን በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።

እንደ ኬሲቢ ግሩፕ ያሉ ኩባንያዎች ወይም ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚፈቅደው የባንክ ሥራ አዋጅ የጸደቀው ታኅሳስ 8 ቀን 2017 ነበር። የውጪ ባንኮች በኢትዮጵያ ተቀጥላ በማቋቋም፣ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች ድርሻ በመግዛት፣ ቅርንጫፍ በመክፈት አሊያም የውክልና ጽህፈት ቤት ከፍቶ መሥራት በአዋጁ ተፈቅዶላቸዋል። 

“ብሔራዊ ባንክ በልዩ ሁኔታ በአግባቡ የተቋቋሙ፣ መልካም ሥም እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ አቋም ያላቸው የውጪ ባንኮች በግዢ አማካኝነት ነባር የሀገር ውስጥ ባንኮችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲይዙ ሊፈቅድ ይችላል።” ይህ የሚሆነው “ለኢኮኖሚው ጠቀሜታ ያላቸው ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ እና ወይም ችግር ውስጥ ላለ ባንክ እልባት ለመስጠት የፋይናንስ መረጋጋትን ለማስጠበቅ” እንደሆነ በአዋጁ ሠፍሯል። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጪ ባንኮች ፈቃድ የሚሰጥበት መመሪያ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የገለጹት የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ዘርፍ ከፍተኛ አማካሪ ጆቴወርቅ ጉደታ “እጅግ በቅርቡ ይጸድቃል” ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ጆቴወርቅ ባለፈው ሣምንት በተካሔደው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ እንዳሉት የሀገሪቱ ባንኮች አጠቃላይ ትርፍ ባለፉት ዓመታት ከ10 እስከ 20 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። ከኢትዮጵያ ሕዝብ የባንክ ተጠቃሚው 65 በመቶ ብቻ ቢሆንም ባለፈው ዓመት ኢንዱስትሪው 1.2 ቢሊዮን ዶላር እንዳተረፈ ጆቴወርቅ አስረድተዋል።

የውጪ ባንኮችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት የብሔራዊ ባንክ ሹማምንት የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ፈጠራ እና ቅልጥፍናን ማፋጠን እንዲሁም የኢትዮጵያን ገበያ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ጋር ማስተሳሰር ይፈልጋሉ።

ኢትዮጵያ በገበያዋ የውጪ ባንኮችን ለማስተናገድ ስትዘጋጅ ተቆጣጣሪው ብሔራዊ ባንክ የብድር አሰጣጥ እና የኮርፖሬት አደረጃጀትን ጨምሮ በበርካታ የባንክ ሥራ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል። ብሔራዊ ባንክ ከዓለም እንኳ ባይሆን ቢያንስ በአፍሪካ ምርጥ ከሚባሉ የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ተቋማት አንዱ ሆኖ ለመገኘት ራሱን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ምክትል ገዥው ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል።

የባንኩ ባለሙያዎች በሥመ-ጥር ተቋማት ስልጠና ማግኘታቸውን የገለጹት ሰለሞን የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባልደረቦች እያማከሯቸው መሆኑን ተናግረዋል። የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ  ሰለሞን ደስታ “መሠረቶቹ ጠንካራ ናቸው፤ ዘርፉም በስሏል። ጥቅማችንን በማሳደግ እና ጉዳቱን በመቆጣጠር ማሻሻያውን በጥንቃቄ ተግባራዊ ማድረግ የእኛ ፋንታ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

መጪዎቹ ወራት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ በርከት ያሉ ለውጦች የሚያይበት ሊሆን እንደሚችል የመንግሥት ባለሥልጣናት ባለፈው ሣምንት ጥቆማ ሰጥተዋል። ብሔራዊ ባንክ የሚከተለው የገንዘብ ፖሊሲ በመስከረም 2018 በዋጋ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እስከ ታኅሳስ 2018 ባለው ጊዜ የመጀመሪያውን ፈቃድ ለውጪ ባንክ ይሰጣል ተብሎ ይጠቃል።

ኢትዮጵያ የውጪዎቹን ባንኮች ስትጠብቅ የዓለም ባንክ የፋይናንስ ዘርፍ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት (FSSP) ባለፈው ሣምንት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። በዚህ ፕሮጀክት ዓለም ባንክ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት 700 ሚሊዮን ዶላር ብድር ይሰጣል። በፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ ከተፈቀደው ብድር አብዛኛው ኢሕአዴግ ልማታዊ መንግሥትን ፋይናንስ ለማድረግ የተጠቀመበትን የንግድ ባንክ ከገባበት ቀውስ ለመታደግ የተደለደለ ነው።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገቢራዊ የሚደረግ ነው። ሦስቱን የመንግሥት ተቋማት በማጠናከር የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ መረጋጋት ለማሳደግ የተዘረጋው ፕሮጀክት አራት አላባዎች አሉት።

የባንክ ዘርፉን የቁጥጥር እና አስተዳደራዊ ማዕቀፍ እንዲሁም የብሔራዊ ባንክን ተቋማዊ አቅም ማጠናከር የመጀመሪያው ዓላባ ነው። ሁለተኛው የፕሮጀክቱ ዓላባ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለማሻሻል፣ መልሶ ለማዋቀር እና የመሥሪያ ካፒታሉን ለማሳደግ የታቀደ ነው።

ባለፈው ሣምንት በተካሔደው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጉባኤ ላይ በዓለም ባንክ ከተፈቀደው ብድር ውስጥ 253 ሚሊዮን ዶላር ወደ ንግድ ባንክ ገቢ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ ተናግረዋል። “ከሰኔ መጨረሻ በፊት ተጨማሪ 400 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይለቀቃል ብለን እንጠብቃለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

ንግድ ባንክ ተሸክሞት የቆየውን 845 ቢሊዮን ብር የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዕዳ በአስር ዓመታት ውስጥ ግብር ሰብስቦ ለመክፈል ገንዘብ ሚኒስቴር ተረክቧል። ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የዕዳ ሠነድ አማካኝነት የንግድ ባንክን የመሥሪያ ካፒታል ለማሳደግ 316 ሚሊዮን ብር ገደማ መድቧል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢራዊ የሚደረገው የዓለም ባንክ ፕሮጀክት ክፍል በሦስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን ባንኩ የተፈቀደለትን የገንዘብ መጠን ከእጁ ለማስገባት ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅበታል። አቶ አቤ ሳኖ በፕሬዝደንትነት የሚመሩትን ባንክ አስተዳደር ማሻሻል ቀዳሚው ሥራ ነው።

በሁለተኛው ምዕራፍ የተበላሹ ብድሮችን ለማስወገድ እና የሥጋት ተጋላጭነትን ለመቀነስ የባንኩን የሒሳብ መዝገብ መልሶ ማዋቀር ያስፈልጋል። ሦስተኛው እና የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ካፒታል ማሳደግ ይሆናል። ዓለም ባንክ በፕሮጀክቱ ለንግድ ባንክ የሚሰጠው ገንዘብ ለሌላ የብድር አገልግሎት መዋል እንደማይችል መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው አበዳሪ ተቋም ስለ ፕሮጀክቱ ያሠፈረው ማብራሪያ ይጠቁማል።

ዓለም ባንክ በዚህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ 700 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያበድር የተገለጸው በሐምሌ 2016  የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ባደረገበት ወቅት ነው። በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር የሚደጎመው የተራዘመ የብድር አቅርቦት መርሐ-ግብር መንግሥት የሚከተለውን የገንዘብ ፖሊሲ በማዘመን የዋጋ ግሽበትን የመግታት ዓላማ ጭምር አለው። በዚህም መሠረት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደውን የቀጥታ ብድር በዚህ ዓመት ሙሉ በሙሉ ለማቆም ወስኗል።

በምትኩ መንግሥት የሚገጥመውን የበጀት ጉድለት ለመሙላት ፊቱን ከሀገር ውስጥ አማራጭ የብድር ምንጮች ወደ ማፈላለግ አዙሯል። በብሔራዊ ባንክ በኩል ለሽያጭ የሚቀርበው የግምዣ ቤት ቤት ሰነድ ወይም ትሪዠሪ ቢል አንዱ የመበደሪያ መሣሪያ ነው። እስካሁን በነበረው አሠራር ባንኮች እና የጡረታ ፈንዶች ይህን የዕዳ ሠነድ ሲገዙ ቆይተዋል።

ባለፈው ሣምንት የመንግሥት የመዋዕለ-ንዋይ ክንድ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሰባት ቢሊዮን ብር የግምዣ ቤት ሰነድ መግዛቱ ይፋ ተደርጓል። ተቋሙ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጸመውን የግምዣ ቤት ሠነድ ግዢ “የበጀት ጉድለትን ለመሙላት የዋጋ ግሽበት ወደ ማያስከትሉ የብድር ምንጮች” መዘዋወሩን እንደሚያሳይ የገለጹት አቶ ማሞ “እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ታሪካዊ” እንደሆነ ገልጸዋል።    

ባንኮች የግምዣ ቤት ሠነድ በመግዛት ለመንግሥት እንዲያበድሩ የተጣለባቸው ግዴታ በሰኔ ወር ይነሳል። አቶ ማሞ ምኅረቱ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (Central Securities Depository) በቅርቡ ሥራ ላይ መዋሉን አስታውሰው ዘመናዊ የፋይናንስ መሠረተ ልማት እንዳላቸው ሌሎች ሀገሮች “ወደፊት” የግምዣ ቤት ሰነድ ለግለሰብ ኢንቨስተሮች ለሽያጭ መቅረብ እንደሚጀምር ይፋ አድርገዋል።  

እርምጃው “እጅግ ጠቃሚ” መሆኑን የገለጹት አቶ ማሞ መንግሥት እንደ ከዚህ ቀደሙ ከባንኮች እና የጡረታ ፈንዶች ብቻ ሳይሆን ከመንግሥት የንግድ ኩባንያዎች፣ የኢንሹራንስ ተቋማት እና የችርቻሮ ኩባንያዎች ጭምር ለመበደር እንደሚፈቅድለት አስረድተዋል።

ባንኮች የግምዣ ቤት ሠነድ በመግዛት ለመንግሥት እንዲያበድሩ የተጣለባቸው ግዴታ በሰኔ ወር ይነሳል። ገንዘብ ሚኒስቴር የብሔራዊ ባንክን የቀጥታ ብድር ቢያቆምም መንግሥት የሚገጥመውን የበጀት ጉድለት ለመሙላት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በተጨማሪ ሌሎች አበዳሪዎች ያስፈልገዋል። አቶ ማሞ ከባንኮች እና የጡረታ ፈንዶች በተጨማሪ ወደፊት የግምዣ ቤት ሠነድ ለመንግሥት የንግድ ኩባንያዎች፣ የኢንሹራንስ ተቋማት እና ግለሰቦች እንደሚሸጥ ተናግረዋል።

DW amharic

ECONOMY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

ራማፎሳና ትራምፕ በነጩ ቤተመንግስት – ሌላው ዘለንስኪ?
የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳዋ – 36.2 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ECONOMY

ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

March 29, 20260
ECONOMY

“የስምምነቶች ሁሉ እናት” ህንድ እና የአውሮፓ ህብረትታሪካዊ የንግድ ስምምነት አደረጉ

January 27, 20260
ECONOMY

በኢትዮያ ከ21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በርላይ የጋዝ ክምችት ተገኘ

October 30, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news