Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ECONOMY  የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳዋ – 36.2 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል
ECONOMY

የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳዋ – 36.2 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል

Ethioreview newsEthioreview news—May 22, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አሜሪካ በዓለም ላይ ከፍተኛው የብሔራዊ ዕዳ መጠን ያላት ሀገር ነች። የአሜሪካ ያለባት ዕዳ 36.2 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ከአሜሪካ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) አንፃር 122 በመቶ ሆኗል።

የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳ በየሦስት ወሩ በ1 ትሪሊዮን ዶላር ይጨምራል። ከ36.2 ትሪሊዮን ዶላሩ የአሜሪካ ዕዳ ውስጥ ሦስት አራተኛው ከሀገር ውስጥ የቀረበ ሲሆን፤ ከአሜሪካ የግል ባለሀብቶችና ተቋማት፣ ከአሜሪካ መንግስት ኤጀንሲዎች እንዲሁም ከፌደራል መጠባበቂያ የመጣ ነው።

ከግለሰቦች መካከል ዋረን በፌት፣ በኩባንያቸው በርክሻየር ሃዛዌይ አማካኝነት፣ የ314 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸውን የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሰነዶችን በመያዝ መንግሥታዊ ያልሆነ ብቸኛው ትልቁ ግምጃ ቤት ሰነዶችን የያዙ ባለሃብት መሆናቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።

አሜሪካ ካለባት አጠቃላይ ብድር ውስጥ አንድ አራተኛውን የያዙት ደግሞ የውጭ ሀገራት ባለሀብቶች ናቸው።

ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በውጭ ሀገራት ባለሃብቶች የተያዘው የአሜሪካ ዕዳ ድርሻ በአምስት እጥፍ ጨምሯል። እ.አ.አ. በ1970 በውጭ ሀገር  ባለሀብቶች የተያዘው የብድር አቅርቦት 5 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ይህ አኃዝ ወደ 25 በመቶ ከፍ ብሏል።

የውጭ ባለሀብቶችና ተቋማት ከአሜሪካ የግምጃ ቤት የገዙት የ9.05 ትሪሊዮን ዶላር ሰነድ አላቸው። ከዚህም ውስጥ የጃፓን 1.13 ትሪሊዮን ዶላር፣ የዩናይትድ ኪንግደም 779.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም  የቻይና ባለሃብቶች 765.4 ቢሊዮን ዶላር በመያዝ ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ትራምፕ በተለያዩ ሀገራት ላይ ለጣሉት የቀረጥ ዕርምጃ ምላሽ፣ ጃፓንና ቻይናም ያላቸውን ከፍተኛ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሰነዶች ክምችት ለመደራደሪያነት እንደሚጠቀሙበት አመልክተዋል።

የአሜሪካ ዕዳና ኮንግረሱ

መንግሥት በየዓመቱ ከሚሰበስበው ገቢ በላይ ወጪ ሲያወጣ የበጀት ጉድለት ይከሰታል። ጉድለቱን  ለመሸፈን ደግሞ ብድር ስለሚወስድ የዕዳ መጠኑ እያደገ ይገኛል።

አሜሪካ ብድረ  በሕግ አውጪው አካል ይሁንታ እንዲያገኝ ለማድረግ ደግሞ የአሜሪካ ኮንግረስን ገደብን መከተል ይኖርባታል። ኮንግረሱ የአሜሪካን መንግስት እንደ ሶሻል ሴኩሪቲ፣ የጤና እንክብካቤ እና መከላከያ ያሉ ነባር ግዴታዎችን ሸፍኖ መስራት እንዲችል ምን ያህል ገንዘብ መበደር እንደሚችል ገደብ ያስቀምጣል።

ይህ ገደብ “የዕዳ ጣሪያ” በመባል ይታወቃል። ጣሪያው ላይ ሲደረስ፣ ኮንግረሱ ገደቡን ካላነሳው ወይም ለጊዜው ካላገደው በስተቀር መንግሥት ተጨማሪ መበደር አይችልም።

ከ1960 ጀምሮ ኮንግረሱ የዕዳ ጣሪያውን 78 ጊዜ አሻሽሏል፤ ይህም አሜሪካ ተጨማሪ ገንዘብ እንድትበደር አስችሏታል።

ለብድሩ የግምጃ ቤት ሰነዶች ጠቀሜታ

አሜሪካ ገንዘብ መበደር ስትፈልግ የምታማትረው የፌደራል መንግሥቱ የገንዘብ (ፋይናንስ) ጉዳዮች መምሪያ ወደ ሆነው ግምጃ ቤት (Treasury) ነው። ገንዘብ ለመበደር፣ ግምጃ ቤቱ የተለያዩ የሰነደ ሙዓለ ንዋኖችን ወስዶ ለባለሀብቶች ይሸጣል።

እነዚህ የዕዳ ሰነዶች በመሠረቱ ባለሀብቶች ለአሜሪካ መንግሥት የሚያበድሩት ገንዘብ ሲሆን፣ መንግሥትም ከወለድ ጋር መልሶ ለመክፈል ቃል ይገባል። የተለያዩ የዕዳ ሰነዶች በተለያየ ጊዜ ለባለሃብቶቹ የሚከፈሉበት ጊዜ አላቸው።

ለመንግስት ብድር የሚያስፈልጉ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ (ግምጃ ቤት ሰነድ) አይነቶች የአጭር ጊዜ የግምጃ ቤት ሰነዶች (T-bills) የአጭር ጊዜ ሲሆኑ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብድሩ ከነወለዱ  የሚከፈልባቸው የግምጃ ቤት ሰነዶች ናቸው።
የመካከለኛ ጊዜ የግምጃ ቤት ኖቶች (T-notes)  ከ2 እስከ 10 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ብድሩ ከነወለዱ  የሚከፈልባቸው የግምጃ ቤት ሰነዶች ናቸው።
የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንዶች (T-bonds)  ከ20 እስከ 30 ዓመታት ውስጥ የብድር ክፍያቸው የሚጠናቀቅና በየ6 ወሩ የወለድ ክፍያቸው ይፈጸማል።  መንግሥት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘትና ብሔራዊ ዕዳውን ለመክፈል ግብር ሊጨምር ይችላል፤ ይህም ሕዝቡ ላይ ወጪን ይጨምራል።

እየጨመረ የሚሄድ ዕዳ ለከፍተኛ የወለድ ምጣኔዎች ሊዳርግ ስለሚችል፣ የቤት መግዣ ብድሮች፣ የመኪና ብድሮች እና የክሬዲት ካርድ ዕዳዎች የበለጠ ውድ እንዲሆኑ ያደርጋል።

በጌትነት ተስፋማርያም ኢቲቪ

ECONOMY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች አንዱን መግዛት ይፈልጋል
በትህነግ ውስጥ የ1967ቱን ዘመነ “ወይን” እያለመ ያሉ መኖራቸው ተሰማ፤ ነዳጅ ወደ ኤርትራ እየተጋዘ ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ECONOMY

ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

March 29, 2026
ECONOMY

“የስምምነቶች ሁሉ እናት” ህንድ እና የአውሮፓ ህብረትታሪካዊ የንግድ ስምምነት አደረጉ

January 27, 2026
ECONOMY

በኢትዮያ ከ21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በርላይ የጋዝ ክምችት ተገኘ

October 30, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2