Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  የጌዲዮኖች ስምምነት – ኢትዮጵያና እስራኤል
NewsOPINION

የጌዲዮኖች ስምምነት – ኢትዮጵያና እስራኤል

Ethioreview newsEthioreview news—May 28, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኢትዮጵያና እስራኤል የቢዝነስ ፎረም ከግንቦት 5 እስከ 6 ቀን 2025 “የሁለትዮሽ ግንኙነትን በፈጠራ ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ያለውን ዘላቂ አጋርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ታሪካዊ ክስተት ነበር። በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሞሼ ሳኣር መሪነት የተካሄደው ይህ ፎረም በንግድ፣ በግብርና፣ በውሃ አስተዳደር፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና በደህንነት ላይ ያተኮረ ከፍ ባለ ልዕልና ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ያጠናከረ መድረክ ነበር።

የእነዚህ ሁለት ጌዲዮኖች የጋራ ራዕይ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ትስስርን ከዘመናዊ ፈጠራ ጋር በማዋሃድ ጠንካራ የሁለትዮሽ ጥምረት በመፍጠር የሁለቱንም ሀገራት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ገጽታዎችን ለመለወጥ ቃል የተገባበት አዲስ የጋራ ትብብር መጀመሩን አመልክቷል።

በፎረሙ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳኣር ባሰሙት ንግግር “እስራኤል የኢትዮጵያን አስደናቂ የኢኮኖሚ እድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አንስተዋል። ኢትዮጵያ በእስራኤል የፈጠራ እና የዕድገት ጉዞ እንድትሳተፍ በመጋበዝም እስራኤል የኢትዮጵያን ራዕይ ለማሳካት በምታደርገዉ ርብርብ ላይ እስራኤል አስተዋጽኦ ማድረግ እንደምትፈልግ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸው የኢትዮጵያን ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል እና የተደረጉትን ስርነቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በማብራራት ኢትዮጵያ ለአለም አቀፍ ባለሀብቶች ተመራጭ መዳረሻ መሆኗን አስገንዝበዋል። ሁለቱ ሚኒስትሮች በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በሽብርተኝነት እና በውሃ አስተዳደር ላይ ያሉ የትብብር እድሎችን በጥልቀት በመወያየት ለወደፊቱ ሁለቱም አገራት ለዘላቂ ልማት እና ብልፅግና አብሮ ለመስራት ተስማምተዋል።

More stories

“በተካድኩ” ስሜት መከላከያ አማራ ክልልን ለቆ ሊወጣ ነው?

April 10, 2023

” ከሩስያ ጋር በዩክሬን ምድር አንዋጋም፣ የኔቶ አባል አገራትን ግን ኢንች እንዳይነኩ እንከላከላለን ” አሜሪካ

February 25, 2022

ኮንስበርግ አምስት ገድሎ ሁለት ያቆሰለው ዴንማርካዊ ሃይማኖት ከአክራሪነት ጋር እየተያያዘ ነው

October 14, 2021

ጦርነቱ ገና አልተጀመረም!የትግላችንን መዳረሻ እንዳንዘነጋ!

August 26, 2021

የእስራኤሉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉብኝታቸዉ የመጀመሪያዉ ቀን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ መስኮች ላይ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ውይይቶችን አካሂደዋል።

ይህ ጉብኝት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እ.አ.አ በመጋቢት 2025 ወደ እስራኤል ያደረጉትን ጉዞ ተከትሎ የመጣ ሲሆን ሁለቱም ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። በአዲስ አበባ በተካሄደዉ በዚህ ፎረም ሁለቱ ሚኒስትሮች እያንዳንዱ ሀገር የራሱን ጥንካሬ በመጠቀም የአየር ንብረት ለውጥን፣ የምግብ ዋስትናን እና ኢኮኖሚያዊ አለመመጣጠንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን መፍታት ላይ ያተኮረ ፈጠራን፣ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማምጣት በአጋርነት ለመስራት ተግባብተዋል።

                                                       ዛሬን ያጋመደዉ ታሪካዊ ዳራ

የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት እልፍ አመታትን የተሻገረ ታሪክ አለዉ። ይህም በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ እንኳን ብንገልጠዉ ወደ ንግስተ ሳባ ዘመን ይመልሰናል። ንግሥቷ ንጉሥ ሰሎሞን ለመጠየቅ በኢየሩሳሌም ያደረጉት ጉብኝት የመጀመሪያዉ የአገራቱ ታሪካዊ መሰረት እንደሆነ ታሪክ ያሳያል። በቆንስላ ደረጃ ግንኙነት የተጀመረው በ1956 እ.ኤ.አ. ነበር። ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረዉ ግን በ1961 እ.ኤ.አ. ሲሆን የእስራኤል ኤምባሲ በአዲስ አበባ ተከፈተ።

በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት አልፎ አልፎ መስተጓጎል ቢኖርም የአገራቱ ግንኙነት እየተሻሻለ በመምጣት በ1989 እ.ኤ.አ. የእስራኤል ኤምባሲ በድጋሜ ተከፈተ። ይህን ተከትሎ በ1992 እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ በቴል አቪቭ ኤምባሲ በመክፈቷ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ተጠናከረ።

የኢትዮጵያ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በ2004 እ.ኤ.አ. ወደ እስራኤል ያደረጉት ጉብኝት፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በ2017 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ጉዞ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሮቭን ሪቭሊን በ2018 እና 2019 እ.ኤ.አ. ያደረጓቸውን የጋራ ጉብኝቶች ጨምሮ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ግንኙነቶች እንደማሳያ ሊጠቀሱ ይችላሉ። እነዚህ ግንኙነቶች በግብርና፣ በውሃ አስተዳደር፣ በጤና፣ በመከላከያ ቴክኖሎጂ እና በትምህርት መስኮች ላይ የእዉቀት ሽግግሮችን እና መስተጋብሮችን በመፍጠር አጋርነትን አፅንተዉ ቆይተዋል።

በኢትዮጵያ በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር አካባቢ የአይሁድ ማህበረሰብ በብዛት ለአመታት ይኖራሉ። ይህም ማለት እነዚህ ህዝቦች የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክ፣ ማህበረሰባዊ ስሪት በጥልቀት የተረዱ በመሆናቸዉ የሁለቱን ህዝቦች ለማቀራረብ እና የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ትልቅ ሚና አለዉ። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይህንን ሲገልፁ “ኢትዮጵያና እስራኤል በታሪካዊ ትስስር እና በጋራ እሴቶች ላይ የተመሠረተ ጥልቅ ግንኙነት ያላቸው ህዝቦች ሲሆኑ ይህም በተለያዩ ዘርፎች ወደ ዘመናዊ ትብብር እያደገ ነው” ብለዋል።

ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስም ይህንን አስተጋብተዋል። “ሁለቱ አገራት ከጥንት ዘመን ጀምሮ ሥር የሰደደ፣ በጋራ እሴቶች የተጋመደ እና በዘመናዊ ትብብር ለዳብር የሚችል ግንኙነት አላቸዉ” ሲሉ ገልጸዋል። አምባሳደር አብርሃም እንደገለፁት የአማርኛ ቋንቋ በእስራኤል መገናኛ ብዙሃን አንዱ የስራ ቋንቋ ስለሆነ የአገራቱን ግንኙነት እና የባህል ልውውጥን በማመቻቸት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን በማጠናከርና የጋራ ስሜትን ለመፍጠር ከፍ ያለ ሚና አለዉ።

                                         ግብር እና ፈጠራ – ለዘላቂ እድገት እና ብልፅግና

መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስራኤል ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ የመስኖ ቴክኖሎጂን፣ በሽታ የሚቋቋሙ ሰብሎችን እና ተጓዳኝ የእርሻ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር እና በመጠቀም በረሃማ መሬትን ወደ ምርታማ እርሻ በመቀየር በግብርና ፈጠራ ዓለም አቀፍ መሪ ናት። የውሃ እና የማዳበሪያ አጠቃቀምን በማመቻቸት የምርት ጥራትን እና መጠንን በማሻሻል ምሳሌ የምትሆን አገር ናት።

እ.ኤ.አ. በ2005 የእስራኤሉ MASHAV እና የአሜሪካው የእርዳታ ድርጅት/USAID/ በኢትዮጵያ የሆርቲካልቸር ፕሮጀክት በማቋቋም በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ከእስራኤል የመስኖ ቴክኖሎጂዎች እና ከፍተኛ ምርት ከሚሰጡ የአቮካዶ ዝርያዎች ጋር በማስተዋወቅ የሆርቲካልቸር ልማት ልምዶችን አብዮታዊ በሆነ መንገድ አለማምደዋል። ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የዚህን ተግባር ዉጤታማነት በፎረሙ ላይ አስታዉሰዋል። “የእስራኤል የቴክኒክ እውቀት የኢትዮጵያን የሆርቲካልቸር ዘርፍ ለውጦታል፣ በመሆኑም የአቮካዶ ኤክስፖርት ጭማሪ አሳይቷል፣ ይህም ኢትዮጵያን በዓለም ገበያ ቁልፍ ተጫዋች አድርጓታል” ብለዋል።

በፎረሙ ላይ ጌዲዮን ሳኣር የእውቀት ሽግግርን፣ የስልጠና ፕሮግራሞችን እና የቴክኖሎጂ ልውውጥን በማድረግ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለመደገፍ እስራኤል ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። በዚህም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን መጠን እና ብቃት መጨመር ላይ ያተኮረ የእዉቀት ሽግግር እንደሚሆን ገልፀዋል። የእስራኤል መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግብርና ባለሙያዎች መሰረታዊ ልምዶችን በአፈር አስተዳደር እና ሰብል ጥራት ላይ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ሰጥተዋል። ይህ የቢዝነስ ፎረም ይህንን አጋርነት በማስፋት፣ የላቁ የመስኖ ስርዓቶችን፣ የግሪን ሃውስ ቴክኖሎጂዎችን እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ የእርሻ ዘዴዎችን በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ በር የከፈተ ነዉ ተብሏል።

                            የውሃ አስተዳደር፡ በውሃ እጥረት ውስጥ እድገትን ማስቀጠል

እስራኤል ከ60% በላይ የሚሆነው ግዛቷ በረሃ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህን የተፈጥሮ ችግር ለመፍታት የመስኖ እና የላቁ የውሃ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ የውሃ አስተዳደር መፍትሄዎችን ለዓለም ያስተዋወቀች አገር ናት። እነዚህ ስርዓቶች ውሃን በቀጥታ ወደ ተክሎች ሥር በማድረስ ቅልጥፍናን ከፍ በማድረግ እና አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች የግብርና ምርትን ለማገኘት ያስቻሉ ፈጠራዎች ናቸዉ።

ኢትዮጵያ “የአፍሪካ የውሃ ማማ” የሚል ቅጽል ስም ቢኖራትም የሚታወቁ የውሃ እጥረት ችግሮችም አሉባት። ሁሉም ወንዞቿ ድንበር ተሻጋሪ ሲሆኑ አስቸጋሪ መልክዓ ምድሯም የተትረፈረፈ የከርሰ ምድር ውሃ ስርዓትን ይገድባል። በየካቲት 4 ቀን 2025 በተፈረመ ታሪካዊ ስምምነት ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለመለወጥ የእስራኤልን የላቀ የውሃ አስተዳደር እና እውቀት ለመጠቀም ስምምነት ፈርማለች። ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ይህ ትብብር በኢትዮጵያ የውሃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች የስንዴ ምርትን ለማሳደግ እና የምግብ ዋስትና ግቦቿን ለማሳደግ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት እና ውስን የከርሰ ምድር ውሃ አቅርቦት ተግዳሮቶችን ለመቀነስ አስችሏታል።

በፎረሙ ላይ እስራኤል አቅም ግንባታን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና በውሃና በኃይል ልማት የጋራ ፕሮጀክቶችን በመተግበር ቀጣይ ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብታለች። ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ አቅም፣ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ወሳኝ አስተዋፆ እና አሁን ላይ የተፈጠሩ ምቹ አሰራሮችን በመጥቀስ ለትብብር ቁልፍ ቦታ እንደሆነች ለአቻዎቻቸዉ ነግረዋቸዋል። ጌዲዮን ሳኣር በበኩላቸዉ ዘላቂ የውሃ አስተዳደርን አስፈላጊነት አጽንኦት በመስጠት “የእስራኤል ፈጠራዎች ኢትዮጵያ የግብርና አቅሟን እንድታውቅ እና የአካባቢ ጥበቃን እንድታሳድግ ሊረዷት ይችላሉ” ብለዋል። ፎረሙ የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም አቅም ለማሳደግ የፀሐይ ኃይልን የሚጠቀሙ የመስኖ ስርዓቶችን እና የውሃ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ፕሮጀክቶችን እድሎችም ዳሷል።

                                    ቱሪዝም፡ የጋራ ቅርስ ለጋራ እድገት

በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ለዘመናት የቆየው ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትስስር የጠበቀ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲኖር አስችሏል። አምባሳደር አብረሃም እንደገለፁት ብዙ ኢትዮጵያውያን ለፀሎት ወደ ኢየሩሳሌም እና ጎልጎታ ይጓዛሉ። እስራኤላውያን ደግሞ ኢትዮጵያን በታሪኳ እና በቅርስ ሀብቷ ምክንያት እንደ ሁለተኛ ቤታቸው ስለሚቆጥሯት የመጀመሪያ ምርጫቸዉ ኢትዮጵያ ናት። በቅርቡ የወጣዉ የዓለም ባንክ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶች፣ ጥንታዊ የክርስትና ታሪኮች እና ልዩ የባህል ቅርሶች ባለቤት በመሆኗ በየዓመቱ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች ይጎበኟታል። በመሻሻል ላይ ያሉት መሠረተ ልማቶች፣ የተሻለ የቅርስ አያያዝ፣ የተሻሻለ ደህንነት እና ዲጂታል የቲኬት ሥርዓቶችን ጨምሮ እየተደረጉ ያሉ ለዉጦች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ እያሳደጉ መሆናቸዉን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

በፎረሙ ላይ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የእስራኤል ቱሪስቶች ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እስከ አክሱም ጥንታዊ ሐውልቶች ድረስ ያሉትን የኢትዮጵያን ቅርሶች እንዲጎበኙ ጋብዘዋል። ጌዲዮን ሳኣር የጋራ ቅርስን ሚና በማጉላት “የጋራ ታሪካችን የብዙ ገፅታ ጥረታችን መሰረት ሲሆን ቱሪዝምንና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ያሳድጋል” ብለዋል።

ለቱሪዝም ዘርፉ ማደግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቴል አቪቭ እና በአዲስ አበባ በየቀኑ የሚያደርጋቸውን ሁለት በረራዎች ትልቅ ሚና እንዳላቸዉ ጌዲዮን ሳኣር አስምረዉበታል። ይህ አገልግሎት የተሳፋሪዎችን ፍላጎት እና የጭነት አገልግሎት ትስስርን በማሳደግ የጋራ ግብይት እድሎችን፣ የባህል ልውውጥ ፕሮግራሞችን እና የተቀላጠፈ የቪዛ አሰጣጥ ሂደቶችን በማሳለጥ የሁለትዮሽ ቱሪዝምን ለማሳደግ ትልቅ ድርሻ እንዳለዉ በዉይይቱ ተገልጧል።

                ንግድና ኢንቨስትመንት፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ መግቢያ በር

ኢትዮጵያ እና እስራኤል ጠንካራ የንግድና የኢንቨስትመንት አጋርነትን እያዳበሩ የመጡ አገራት ናቸዉ። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ በመጠቀም እስራኤል አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቴክኖሎጂ ስነ-ምህዳርን በመጨመር ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚ መግቢያ በር እያደረጓት እንደሆነ በፎረሙ ተዳሷል። ኢትዮጵያ ለዋና ዋና የባህር ላይ የንግድ መስመሮች ቅርብ መሆኗ፣ እያደገ የመጣው መሠረተ ልማቷ እና ለአፍሪካ ገበያዎች ተደራሽ መሆኗ ለአለም አቀፍ ባለሀብቶች ተመራጭ መግቢያ በር እንደሚያስመርጣት የቀጠናዊ እና ትስስር መረጃ ያመላክታል።

የእስራኤል የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር እንደገለፁት አገራቸዉ በዲጂታል ፈጠራ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በፊንቴክ ዘርፎች ያላት እውቀት የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመለወጥ ተዘጋጅታለች። የኢትዮጵያ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትርም ኢትዮጵያ በመንግስት ቁጥጥር ከተማከለዉ ሞዴል ወደ ግለሰባዉ ማዕከል የተሸጋገረ የኢንቨስትመንት ስርኣት መግባቷን አስረድተዋል። ይህም ለባለሀብቱ ተስማሚ ሲሆን የግብር ማበረታቻዎችን፣ የተቀላጠፉ ደንቦችን እና የተሻሻሉ የደህንነት እርምጃዎችን ያካተቱ ድጎማዎች በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ መኖራቸዉን ጠቅሰዉ እስራኤላዊያን እድሉን በመጠቀም መዋእለ ነዋያቸዉን በዘርፉ እንዲያፈሱ ጠይቀዉ የመንግስት ድጋፍ እና ማበረታቻም እንደማይለያቸዉ ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኢኮኖሚ መግቢያ በር በማድረግ የ120 ሚሊዮን ወጣት ህዝቧን፣ ተለዋዋጭ ገበያዋን እና የሰለጠነ የሰው ኃይሏን የቀጠናዉ ትልቅ የንግድ ማበረታቻዎች መሆናቸውን አስታዉሰዋል። ጨምረዉም “የተደረጉት ማሻሻያዎች እና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ኢትዮጵያን ለዘላቂ ልማት እና ለቀጠናዊ መስተጋብር መግቢያ በር ያደርጓታል” ብለዋል።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳኣር የኢትዮጵያዉ አቻቸዉ ያነሱትን በማጠናከር አቋማቸዉን ገልፀዋል። “ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ላይ ያደረገቻቸዉ ማሻሻያዎች እና አቀማመጧ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወሳኝ መግቢያ በር ያደርጓታል። በኢትዮጵያ መንግስት እናምናለን፣ እና በቅርቡ ጠንካራ የገበያ ኢኮኖሚ እንደምትገነባ እርግጠኞች ነን” ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ የሚያደርጋቸውን ሁለት በረራዎች በማወደስ ይህም ትስስራቸዉን እንደሚያሳድገዉ እና ኢትዮጵያን ለአፍሪካ ንግድ የሎጂስቲክስ ማዕከል እንደሚያደርጋት ተናግረዋል። የእስራኤል አስተዋፆዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ እና በኢትዮጵያ አቪየሽን ማዕከል ቀደም ብሎም የታየ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በፎረሙ ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ(ዶ/ር) እስራኤል የኢትዮጵያ አየር መንገድን በማጠናከር ረገድ ያላትን ሚና አስታዉሰዉ ይህም የኢትዮጵያ የመግቢያ በርነት ደረጃ ወሳኝ አካል ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ እና እስራኤል የቢዝነስ ፎረም ላይ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የእስራኤል ልዑክ በኢትዮጵያ ለባለሀብቱ ተስማሚ ማሻሻያዎች በተደረጉበት ኢንቨስትመንት ላይ ማብራሪያዎች የተሰጡ ሲሆን በዚህም ስኬታማ የንግድ ሥራዎችን ለማካሄድ እድሎችን የከፈተ መሆኑ ተስተዉሏል።

          ሰላም እና ደህንነት፡ ሰላምን እና ደህንነትን በጋራ ማስጠበቅ ለጋራ እድገት

በፎረሙ ላይ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) እና ጌዲዮን ሳኣር ሽብርተኝነትን በመዋጋት ላይ በማተኮር ለሰላም እና ደህንነት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። ሁለቱ መሪዎች የሑቲ አማጽያን እና በሑቲዎች የሚደገፈው አል-ሻባብ የጋራ ስጋቶቻቸዉ መሆናቸዉን ለይተዋል። ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) “በቀጠናዎቻችን ደህንነትን ለመጠበቅ እና መረጋጋትን ለማረጋገጥ በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ ፀረ- ሽብርተኝነት ትብብርን ለማስፋት ከፍተኛ እምቅ አቅም እንዳለን እናምናለን” ብለዋል።

ጌዲዮን ሳኣር በበኩላቸዉ “ሽብርተኝነት ለአገሮቻችን እና ለሰው ልጆች ሁሉ የጋራ ስጋት ስለሆነ በጠንካራ ትብብር ልንዋጋዉ ይገባል” ብለዋል። የደህንነት ትስስርን ለማጠናከር በገቡት ቃል የስለላ መረጃ ልውውጥን፣ የጋራ ስልጠናን እና የየቀጠናቸዉን ተግዳሮቶች ለመፍታት የተቀናጁ ስትራቴጂዎችን ያካተተ ሲሆን ይህም የሁለትዮሽ እምነትን እና የአካባቢዎች መረጋጋትን እንደሚያሳድግ ተሰምሮበታል።

                                 ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ፡ የወደፊቱን ማጎልበት

ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን እና በቴክኖሎጂ ለማደግ እያደረገች ያለችዉ ጥረት እስራኤል በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈጠራ መሪነት ካላት ሚና ጋር በሚገባ ይጣጣማል። እስራኤል እ.ኤ.አ. በ2030 40 በመቶ የፀሐይ ኃይልን ለማመንጨት ያቀደችው ፈጠራ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዛፎችን ለመትከል ያለመው አረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነትን ይደግፋል።

በትምህርት ኢትዮጵያ ከእስራኤል በቴክኖሎጂ ላይ ካተኮረው ሞዴል በመነሳሳት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ላይ አፅንዖት በመስጠት ሥርዓተ ትምህርቷን እያሻሻለች ትገኛለች። ጌዲዮን ሳኣር የእስራኤልን እውቀት ለማጋራት ቁርጠኝነታቸውን በመግለጽ “የእኛ እውቀትና ክህሎት የኢትዮጵያን ወጣቶች ብሔራዊ ተግዳሮቶቻቸዉን በፈጠራ እንዲወጡ ሊያበረታታቸው ይችላል” ብለዋል። ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸዉ በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ ትውልድ በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ልማትና ዓለም አቀፍ መስተጋብርን ለማፋጠን ትልቅ ሚና አለዉ ብለዋል።

እስራኤል ለአነስተኛ የውሃ ሀብት እና አምራች የእርሻ መሬት እጥረት ተግዳሮቶች የሰጠችው የፈጠራ መፍትሄዎች ለኢትዮጵያ ወጣቶች ትልቅ አርአያ በመሆን ብሔራዊ ችግሮችን በፈጠራ ለመቅረፍ ያበረታታል። ፎረሙ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ የስራ ፈጠራን ለመደገፍ እና ዘላቂ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የጋራ ምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ እና የፈጠራ ማዕከላት ለመገንባት የሚያስችሉ እቅዶችን ዘርዝሯል።

                  የኢኮኖሚ ሽግግር፡ ከእስራኤል ጥንካሬን እና ችግር ፈቺነትን መቅሰም

እ.ኤ.አ. በ1983 ከፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ከከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና አነስተኛ ህዝብ ሀብት ጋር ስትታገል የነበረችዉ አሁን ላይ ግን በኢኮኖሚያዊ እድገቷ ወደ አለም አቀፍ ሀያልነት የተሸጋገረችው የእስራኤል ለውጥ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ተሞክሮዎች አሉት። እስራኤል ስረ-ነቀል ማሻሻያዎችን፣ የገበያ መረጋጋትን እና ፈጠራ ላይ ያተኮረ ቀጣይነት ያለው ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሀብት እጥረትን እና ቀጠናዊ ፈተናዎችን አሸንፋለች።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን “የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ ሞተር” ሲሉ አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል። በገለፃቸዉም የገበያ እድሎችን ያሰፉ፣ ኢንቨስትመንትን የሳቡ እና ኢኮኖሚውን ወደ ግል ሴክተር መር ሞዴል ያሸጋገሩ ማሻሻያዎችን አስታዉሰዋል። ጌዲዮን ሳኣር የኢትዮጵያን እድገት በማወደስ “ኢትዮጵያ የወሰደቻቸዉ ማሻሻያዎች በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ማዕከል ያደርጓታል፣ እናም በዚህ ጉዞ ላይ አጋር በመሆናችን ኩራት ይሰማናል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛቷ፣ በዉብ የተፈጥሮ ሀብቷ እና ስትራቴጂካዊ መገኛዋ ቴክኖሎጂን፣ ፈጠራን እና የሰው ኃይል አጠቃቀምን በግምባር ቀደምትነት ከእስራኤል ተሞክሮ መማር አለባት። በፎረሙ ላይ የነበረው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የእስራኤል ልዑክ የንግድ መሪዎችን፣ ፖሊሲ አውጪዎችን እና የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን ያካተተ ሲሆን ኢትዮጵያ እንደ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ያላትን እምቅ አቅም እንዲረዱ በማድረግ የኢኮኖሚ ትብብርን ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

                                                   ለዘመናት የሚዘልቅ አጋርነት

የሁለቱ ጌዲዮኖች አመራር የኢትዮጵያ እና እስራኤል የቢዝነስ ፎረም የጥንት ትስስርን ከዘመናዊ ምኞቶች ጋር በማዋሃድ ለትብብር ትልቅ በርን ከፍቷል። የእስራኤልን የቴክኖሎጂ የበላይነት እና የኢትዮጵያን ሰፊ ሀብት በመጠቀም ይህ አጋርነት ተግዳሮቶችን ወደ ዘላቂ የእድገት እድሎች ይለውጣል። ከግብርና እና የውሃ አስተዳደር እስከ ቱሪዝም፣ ንግድ፣ ደህንነት እና ፈጠራ ድረስ የጌዲዮኖች ራዕይ የወደፊት ጊዜን የጋራ ብልጽግናን የሚያሳይ ሲሆን ሁለቱም አገራት ለትውልድ የሚዘልቅ ስኬት እንዲገነቡ ያነሳሳል።

በመቅደስ ታዬ (ፒ ኤች ዲ) አዲስ ዘመን


NEWSOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ብልጽግና ጃዋር መሐመድን በክብር ይሸልመው!” አገልግሎቱ ከብልጽግና ከካድሬዎች ይልቃል
የኳስ ምትሃት እያሳየ ያለው ላሚን ያማል እስከ 2031 ፈረመ፤ ከፍተኛ ተከፋይ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2