Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በመስከረም ወር በትምህርት ቤቶች አመጽ ለማነሳሳት በጀት መመደቡ ተሰማ፤ “ኦሮሚያ ሕዝብ አልነሳም ብሎናል”
NewsNews2

በመስከረም ወር በትምህርት ቤቶች አመጽ ለማነሳሳት በጀት መመደቡ ተሰማ፤ “ኦሮሚያ ሕዝብ አልነሳም ብሎናል”

Ethioreview newsEthioreview news—June 28, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በመጪው አዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን ማዕከል ያደረገ አመጽ ለማቀጣጠል በጀት መመደቡ ተሰማ። ኦሮሚያ ሕዝብ በተከታታይ በሚሞከሩ የአመጽ ጥሪዎች ተሳታፊ ባለመሆኑ ” ኦሮሚያ ሕዝብ አልነሳም ብሎናል” በሚል ግምገማ መደረጉም ታውቋል።

መረጃውን ያካፈሉን በቅርቡ “ትክክለኛ ነው” የተባለውንና መንግስትን ጨምሮ በርካቶች የደገፉትን ጥያቄ ይዘው የተነሱትን የህክምና ባለሙያዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ በመጥለፍ ወደ አመጽ እንዲሸጋገር በመናበብ ሲሰሩ የነበሩ ቡድኖች ናቸው ዕቅዱን የነደፉት።

የኢትዮሪቪው የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪ እንዳለው በመጪው አዲስ የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን የአመጽ ማዕከል ለማድረግ ኃላፊነቱን ወስደው የሚሰሩትን የሚያስተባበሩት መቀመጫቸውን በውጭ አገር ያደረጉና ሰላማዊ ትግል የሚሉ ቡድኖች ናቸው።

አመጹን ለማነሳሳት አዲስ አበባ የሚገኙ የሻዕቢያ ብር አስተላላፊዎች ተሳታፊ እንደሆኑም ተመልክቷል። ለዚሁ የአመጽ ማስፋፊያ ይሆን ዘንድ በጀት የተመደበ ሲሆን፣ ስራውን የሚያከናውኑ የየአካባቢ ኃላፊዎች ተመልመለዋል።

More stories

ኦሮሚያ – ከ7 ሺህ በላይ አመራሮችና ሠራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን መዉሰዱን አስታወቀ

March 30, 2022

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- “በምክክር ችግሮቻችንን እንፈታልን ጀምረናል፤በዘላቂነት እናሳካዋልን”

January 7, 2022

“ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ያላችሁን ፍቅር በራስ ተነሳሽነት ለመግለጽ ያሳያችሁት አንድነት የሚበረታታና የሚደገፍ ተግባር ነው” -አቶ ሙስጠፌ

February 7, 2021

በስድስት ወራት 2 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል

February 21, 2023

ትምህርት ሲጀመር ትምህርትን ከማስተጓጎል በተጨማሪ ቤተሰብ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤቶች እንዳይልክ ጫና የሚፈጥሩ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊትና የመንደር ተዋናዮች መዘጋጀቱና ወጥ የሆነ ቅስቀሳ እንዲያካሂዱ ዝግጅት እየተደረገ ነው። ስራው በመናበብ የሚሰራና ከአንድ የፕሮፓጋንዳ ማዕከል የሚቀዳ ነው ተብሏል።

በጀቱ ከሚታወቁ ሁለት የውጭ መንግስታት መገኘቱ የተመለከተ ሲሆን፣ የሚውለውም አገር ቤት ሆነው አመጹን ለሚያስተባብሩና ይህንኑ አመጽ በዩቲዩብና በተለይም በፌስቡክ ለሚያሰራጩ እንደሆነ ተባባሪያችን አመልክቷል።

ተባባሪያችን እንዳለው አመጹን እንዲያስተባብሩና አገር አቀፍ እንዲያደርጉት የመምህራን ማህበርን አሳምኖ ለማስገባት ሙከራ ተጀምሯል። እንቅስቃሴው ቢጀመረም የመምህራን ማህበር ኃላፊዎችን ለማግባባት አለማቻሉ ተሰምቷል። ከዚያም በላይ በቅርቡ ከመምህራንና ከመምህራን ማህበር አመራሮች ጋር በተደረጉ ውይይቶች የተደረሰው ስምምነት እንቅፋት እንደሚሆን ተመልክቷል። በሁሉም አግባብ ካልተሳካ በገንዘብ ማህበሩን ለመክፈል ጥረት ሊደረግ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ከሁሉም አቅጣጫ ጦርነት ለመክፈት በሲዳማ ጃዋር በገሃድ አደራጅቶ ሲረዳቸውና በሚዲያዎቹ ሲያስተዋቃቸው የነበረውን ኢጀቶ የተሰኘ ሴል፣ በሶማሌ ክልል አብዲሌ አደራጅቶት የነበረውን ጽነፈኛ የሂጎ ሴል፣ በደቡብ እስከ ወላይታ ወጣ ገባ የሚለውን እንቅስቃሴ ዳግም ለማደራጀት ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን በሌላ መልኩ የአመጽ ማዕከል ለማድረግ የታሰበው።

“በኦሮሚያ ሕዝብ አልነሳም አለ” በሚል የገመገሙት እነ ጃዋር አስቀድሞ በኦሮሚያ ብልጽግና ውስጥ መከፋፈል እንዲፈጠር የተጀመረውን አመራሮችን እየለዩ ማጥቃት እስከ መስከረም ድረስ እንዲቀጥል መክረዋል። የዲሲ ተባባሪ የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው የኦሮሚያ ብልጽግና ውስጥ መለያየት እስካልተፈጠረ ድረስ ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ ስለሆነ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲሰራ ዕቅድ ተይዟል። በዚሁ መሰረት አሁን ከተሰሙት በላይ ለማመን የሚቸግሩ መረጃዎች ውጭ ባሉ በሚታወቁ ሚዲያዎች እንዲሰራጭ ይደረጋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጥሎ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ላይ ዘመቻው እንደሚያነጣጥርም ተሰምቷል። ምልክቶችም እየታዩ ነው።

በዚሁ ዕቅድ መሰረት ሕዝብ ሊያምናቸው የሚችሉ የብልጽግና አመራሮች ወይም አብረው ሲሰሩ የነበሩ በገሃድ ወጥተው መረጃ የሚሰጡና አመራሮችን ሊከፋፍል በሚችል መልኩ ቃለ ምልልስ ካደረጉ በቂ ድጎማ ለነሱና ለቤተሰቦቻቸው እንደሚሰጥ ታውቋል። ክፍያውንና ለቤተሰብ የሚሰጠውን ድጎማ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው በዶላር አጠባ የሚሰሩ እንደሚፈጽሙላቸው አመልክተዋል።

አመጽን ለማነሳሳትና ብልጽግናን ለመከፋፈል የሚሰሩ ፕሮፓጋንዳዎችን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ለሚያሰራጩ በሚፈለገው መጠን ገንዘብ ለመክፈል ችግር እያጋጠመ መሆኑን እነ ጃዋር በስጋት የቀረበላቸው መረጃ ሰለመኖሩ በምክክራቸው ወቅት አንስተዋል። የዚህ ችግር ደግሞ የመንግስት የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲና ቁጥጥር አንዱና ዋና መሆኑ ተመልክቷል። ለጊዜው ሻዕቢያ በአዲስ አበባና በውጭ አገራት በተለይም ከአሜሪካ ዶላር እየለቀመ አዲስ አበባ ባሉ ኤጀንቶቹ በሚፈጽመው የክፍያ ኔት ዎርክ ለመጠቅም አቅደዋል።

ከዚህ በዘለለ ግን መንግስት ገንዘብን ዲጂታላይዝድ በሆነ ሲስተም እንዲዛወር የዘረጋቸውን ሲስተም እየከረረና ሕዝቡም አዳዲስ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ስልቶቹን መጠቀሙ በተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ ጫና ማሳደሩን አንስተዋል። በዚህም ሳቢያ ችግሩን ለማስወገድ ኃይማኖታዊ ሽፋን መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ አቋም ተይዟል። እንደ መረጃ አቀባዮቹ ይህንኑ እንዲሰሩ “የትግሉ መንፈሳዊ ክንፍ” በሚታወቁ ሰባኪያን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጂታላዜሽን እንቅስቃሴ ከክፉ መንፈሳዊ አሰራር ጋር በማያያዝ በዘመቻ እንዲያወግዙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ አቋም ተይዞበታል። አንዳንድ ወንጌል እናስተምራለን የሚሉ ትምህርቱን መስጠት እንደጀመሩ ለማወቅና ለመመልከት ተችሏል።

በዘመናዊ ዓለም በዲጂታል መታወቂያ፣ በዲጂታል የባንክ ሲስተምና አሰራር የሚንቀሳቀሱ ሆነው ሳለ ኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ማዘጋጀቷን የሚቃወሙት ወገኖች የማንነት ችግር ያለባቸው፣ በተለያየ ማንነት የሚንቀሳቀሱ፣ በተለይም ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ በኢትዮጵያ ፓስፖርት የሚጠቀሙ መሆናቸውን ጠቅሰው ኃላፊዎች ማብራሪያ መስጠታቸው አይዘነጋም።

ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ስታጠናቅቅ ብቻ የአገሪቱ አማካይ የነብስ ወከፍ ገበያ በሁለት ዲጂት እንደሚጨምር መገለጹ የሚታወስ ነው። ከምንም በላይ ደግሞ ወንጀልና ወንጀለኞችን ለመከታተል የሚኖረው ፋይዳ እጅግ የሰፋና በዓለም ላይ በተግባር የታየ በመሆኑ የሚቃወሙት ከወንጀል ጋር ንክኪ ያላቸው ቡድኖች እንደሆኑ መገለጹ አይዘነጋም።

ከአመጹ ጋር በተያያዘ አቶ ልደቱና አቶ ጃዋር ስለሚገኙበት በግል የዋትስ አፕ ስልካቸው አማካይነት ለማነጋገር በተደጋጋሚ ቢደውልላቸውም ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም።

homeNEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
” ፅንፈኛው ቅማንት ” የተባለ ታጣቂ በርካታ ሾፌሮችን ገደለ፤ አግቶ የወሰዳቸውም አሉ
Ethiopia leads East Africa’s hydropower surge, reflecting global trends in renewable energy expansion
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2