Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ሃምዳን ደጋሎ “ኤርትራን እንበቀላለን” ሲሉ አስጠነቀቁ፤ የትህነግ አርሚ መጨረሻ አዲስ አበባ? 
NewsNews2

ሃምዳን ደጋሎ “ኤርትራን እንበቀላለን” ሲሉ አስጠነቀቁ፤ የትህነግ አርሚ መጨረሻ አዲስ አበባ? 

Ethioreview newsEthioreview news—June 5, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሱዳን ፈጣኖ ደርሽ ሃይል መሪ ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ/ ሄሜቴ  ኤርትራን እንደሚበቀሉ አስታውቀዋል።  ከፊል ሱዳንን የሚቆጣጠሩት ሃምዳን ደጋሎ በቴሌግራም ገጻቸው ባሰራጩት የፊልም መረጃ በሱዳን ጦርነት የተሳተፉትን አገራት ዘርዝረዋል። ኢትዮጵያም አለችበት፡፡ 

ጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ “ኤርትራ ከድርጊቷ የማትቆጠብ ከሆነ እንበቀላታለን” ሲሉ በተድመጡበት ቪዲዮ የሱዳን ጦር ኃይሎችን ይደግፋሉ ሲሉ ግብጽ፣ ኤርትራና ኢትዮጵያን አንስተው ከሰዋል። 

የኤርትራ መንግስት ደጋፊ የሆኑ የፕሮፓጋንዳ አውታሮች ሄሜቴ ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨታቸውን በመጥቀስ ሊያጣጥሉ ሞክረዋል። መረጃ የማይቀርብበት እንደሆነም ገልጸዋል። 

የኤርትራው አገዛዝ በቅጥረኛ የውጭ ፖሊሲው እንደሚታወቅ የሚገልጹ ቅጥረኛነቱ እንደ ዋና የገቢ ምንጩ እንደሚወሰድ ያመልክታሉ። ተገንጣዮችን ማደራጀት፣ ጽንፈኞችንና የጦር አበጋዞችን በማሰልጠን እና በማስታጠቅ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያመርት የሚነገርለት ሻዕቢያ በወኪሎቹ አማካይነት ቢያስተባብልም የሄሜቲ ክስ ሚዛን እንደሚደፋ ይናገራሉ። 

More stories

ኦሮሚያ – ከ7 ሺህ በላይ አመራሮችና ሠራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን መዉሰዱን አስታወቀ

March 30, 2022

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- “በምክክር ችግሮቻችንን እንፈታልን ጀምረናል፤በዘላቂነት እናሳካዋልን”

January 7, 2022

“ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ያላችሁን ፍቅር በራስ ተነሳሽነት ለመግለጽ ያሳያችሁት አንድነት የሚበረታታና የሚደገፍ ተግባር ነው” -አቶ ሙስጠፌ

February 7, 2021

በስድስት ወራት 2 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል

February 21, 2023

ምንም ይሁን ምን በቅርቡ በጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ወታደራዊ ኃይል መቀመጫ በሆነችው ፖርት ሱዳን ለሦስት ተከታታይ ቀናት በድሮን የደረሰው ዓይነት ጥቃት ሊከተል እንደሚችል በመጥቀስ ስጋት የገባቸው ኤርትራዊያን ጥቂት ዓይደሉም። 

ለሦስት ተከታታይ ቀናት ፖእርት ሱዳን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ የሱዳን ጦር ኃይል ተቀናቃኙን የፈጥኖ ደራሽ ጦር የከሰሰ ሲሆን፣ ቡድኑ ግን እስካሁን ጥቃቱን ስለመፈጸሙ ኃላፊነቱን እንዳልወሰደ ይታወሳል።

የፈጥኖ ደራሽ ጦር መሪ የሆኑት ሄሜቴ የኤርትራን ስም ጠቅሰው ጣልቃ ገብነቷን የማታቆም ከሆነ የበቀል እርምጃ እንደሚወስዱ መግለጻቸውን ተከትሎ እየተዘዋወረ ያለው መረጃ ፖርት ሱዳን ላይ የደረሰው ጥቃት ነው፡፡ ዳጋሎ ኤርትራን ከተበቀሉ የሚጠቀሙት አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች በመሆኑ ኤርትራ እንዴት ትቋቋመዋለች የሚለው ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም ማንሳታቸው ዜናውን ከፍ አድርጎታል።

“ይህ ጦርነት የሱዳናዊያን ብቻ አይደለም።ኤርትራና ግብፅም ጣልቃ ገብተው እየተዋጉን ነው ” ካሉ በኋላ “ኢትዮጵያውያን ሳይቀር እየወጉን ነው” ሲሉ “ስለ ማን ነው የሚናገሩት” ሲሉ የጠየቁ ቀደም ሲል ሲወጡ የነብሩ መረጃዎችን ማገላበጥ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡

በሱዳን የሚገኘው የትህነግ ታጣቂ ኃይል ወልቃይትን ከሁለት አቅጣጫ ለማጥቃት ታስቦ ሱዳን እንዲቀመጥ የተደረገ፣ በማይካድራ ንጹሃን ግድያ የተሳተፈና ወደ ሱዳን የሸሸ የወጣቶች አደረጃጀት የተካተቱበት፣ በስደት ካምፕ የነበሩ ተፈናቃዮች ወዘተ በሚል የተለያዩ ስያሜ የሚጠሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ 

ሌተናል ጄነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል በቅርቡ ባካሄዷቸው ቃለ ምልልሶች ትህነግ በሱዳን ሲያሰለጥነው የነበረ አንድ አርሚ እንደነበረው መግለጻቸው ይታውሳል። ሲያብራሩም ይህ አርሚ ትህነግ ጦርነት በከፈተበት ወቅት ተቆርጦ ሱዳን መቅረቱን አምልክተዋል። ይህ ኃይል ከጄነራል አልቡርሃን ጋር ወኞ የአር አር ኤፍ ኃይሎችን መውጋቱ ለኢትዮጵያ በተለይም ለትግራይ ሕዝብ ጥቁር ጠባሳ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ ርዕሰ መስተዳድር ወንበራቸው ከመነሳታቸው በፊት “በሱዳን ያሉ ሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች” ሲሉ የጠሯቸው ታጣቂቅዎች በሱዳን ጦርነት ተሳትፈው የጄነራል አልቡርሃን ኃይሎች ድል ሲያደርጉ አብረው በጭፈራ ደስታቸውን ሲገልጹ የሚያሳይ ቪዲዮ ሲሰራጭ ነበር። እናም ዳጋሎ የኢትዮጵያን ስም ያነሱት የትግራይ አንድ አርሚ ከሱዳን ጦር ኃይሎች ጎን ሆኖ መዋጋቱን ለማመላከት እንደሆነ ዜናውን የሰሙ ተስማምተዋል።

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስና በዩኤስ አሜሪካ እንደሚደገፍ የሚነገርለት የፈጣን ድጋፍ ሃይሎች/ አር ኤስ።ኤፍ  አዛዥ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ኃይላቸው ሳውዲ አረቢያን ለአርቡርሃን ወገንተኝነት ታሳያለች በሚል ወንጅለው የጅዳን የሰላም ድርድር ማቋረጡ መግለጹ ይታውሳል። 

በሱዳን ጦርነት ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ግብጽና ኤርትራ ከሱዳን ጦር ሃይል ጎን በይፋ መሳተፋቸው የሚታወቅ ነው።  ጄነራል አልቡርሃን ጦር  ከግብጽ ያገኘችውን ክሎሪን ጋዝ መጠቀሟን ጠቅሰው ሄሜቲ ከሰዋል፡፡  

“የሱዳን መንግሥት ሁሉንም የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም እንዲያቆም እና የዓለም አቀፍ መርህ ስር ያሉትን ግዴታዎች እንዲወጣ ዩናይትድ ስቴትስ መጠየቋና ማዕቀብ እንደምትጥል ማስታወቋ ይታወሳል።

በሌላ የሱዳን ዜና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በፖርት ሱዳን ተገኝተው ከጄነራል አልብሩሃን ጋር መምከራቸው ሰፊ መነጋገሪያ ነው።  ይህ ምክክር ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ ጎዳና በቀጭን ገመድ የምትራመድ እንደምትመስል የዘገቡም አሉ፡፡

መንግስት ትህነግን ከግራና ከቀኝ ወጥሮ የመያዝና በትግራይ ከተነሳባቸው ተቃውሞ ጋር አዳምሮ ለማክሰም ከጀመረው እንቅስቃሴ ጋር ያያዙትም አሉ፡፡ በተለይም ትህነኝ ወክለው ከሱዳን ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ጌታቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪቃ ቀንድ ኃላፊ ሆነው ወደ ሱዳን ማቅናታቸው ጥርጣሬውን የሚያጎላ ሆኗል። 

ኢትዮጵያ ከሁለቱም የሱዳን ተፋላሚዎች ጋር መጣላት እንደማትፈልግ የሚገልጹ፣ የአቶ ሬድዋንና አቶ ጌታቸው የፖርት ሱዳን ጉዞ የዲፕሎማሲ አጣብቂኝ እንዳለበት ይጠቁማሉ። ኢትዮጵያ ሁለቱንም እንዴት እንደምታስታምም ይፋ የማያደርጉ ክፍሎች ምን አልባትም የተባበሩት አረብ ኢምሬጽ የነሳችውን ዕውቅና እንድትመልስላት የማግባባት ስራ ሊሰሩ እንደሚችሉ ይገምታሉ። በተጨማሪም በምክክሩ ወቅት ኢትዮጵያ በሱዳን ያለው የትግራይ አርሚ ኃይል ተላልፎ እንዲሰጣት ጄነራል አልቡርሃን መጠየቋን ያነሳሉ። 

የትግራይ ሚዲያ ሃውስ /ቲኤምኤች በቅርቡ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሱድን ጉብኝት አስመልክቶ ስጋቱን ገልጿል። በሱዳን ከጄነራል አልቡርሃን ጋር ሆነው የሐመቲን ተዋጊዎች ሲዋጉ የነበሩት የትህነግ ታጣቂዎ ተላልፈው ሊሰጡ እንደሚችል ጠቁሟል። ቲኤም ኤች እነ ዶክተር ከሚመሩት ትህነግ ጋርም ሆነ ከታጣቂዎቹ አመራሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላላው ዜናውን በስጋት ቢያቀርበውም ጉዳዩ ከዚያ በላይ ሊሆን እንደሚችል በርካቶች ያምናሉ። 

 በቅርቡ ከሻዕቢያ ጋር አዲስ ቅንጅት የጀመረው የትህነግ አንድ ስንጣቂ ህገ መግስቱን በመጣስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሤ እንዲያቆም በተደጋጋሚ ጥያቄ እየቀረበለትና እንደሆነ ቢሰማም መንግስት በይፋ ይህ እስከተጻፈ ድረስ ያለው ነገር የለም።

homeNEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ለመጪው የበጀት ዓመት ሁለት ትሪሊዮን የሚጠጋ የበጀት ረቂቅ ቀረበ
ኢትዮጵያ የነዳጅ ጥራት ፍተሻው ላብራቶሪ በድሬደዋ እየገነባች ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2