በትግራይ ክልል አፈሳ መጀመሩን ተከትሎ የክልሉ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተገለጸ። ሕዝብ ጦርነት እንደማይፈልግ በተደጋጋሚ እየገለጸ ነው። የሕዝብን ጩኸት ወደ ኋላ በማለት አፈሳ የጦርነት ዝግጅትና አፈሳ የተጀመረው ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር አዲስ ጥምዶ/ ቅንጅት ከፈጠረ በሁዋላ ነው።
በትግራይ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣው የፖለቲካ አለመግባባት ስጋት በመፍጠሩና ለጦርነት ባለው ዝግጅት ሳቢያ አፈሳ ተጀምሯል። አፈሳውንም ተከትሎ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እየወጡ ነው። መሆኑን “እኛ ጦርነት አንፈልግም” ያሉት ወጣቶቹ፤ “ከየትኛውም በኩል ኢትዮጵያዊነታችንን ለመግፋት የሚደረግ ጫና ተቀባይነት የለም” ሲሉ ለአሐዱ አስታውቀዋል።
እነዚሁ ወጣቶች “ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ስጋት ስላሳደረብን፤ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ቦታ ለቀን እየወጣን ነው” ሲሉ ለአሐዱ አስታውቀዋል። ባለፈው ሳምንት ሕዝብ የፌደራል መንግስት ትግራይ ድረስ በመምጣት እንዲያነጋግራቸው መጠየቃቸው አይዘነጋም።
“በክልሉ እስር፣ ግድያና ማስፈራራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መጥቷል” የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ወጣቶች “ችግሩን የሚፈታ ሳይሆን እየተባባሰ በመሄዱ ስጋት ፈጥሮብናል። በዚህም ምክንያት ሕይወታችንን ለመታደግ ስደትን እየመረጥን ነው” ሲሉ ስሜታቸውን አጋርተዋል።
“እኛ በአሁኑ ወቅት ወደ ጦርነት የሚያስገባን ጉዳይ የለንም። ችግር ካለም በንግግር መፍታት ነው የምንፈልገው” ሲሉ ተናግረዋል። ጦርነት በምንም መልኩ እንደማይቀበሉ ገልጸዋል።
ሰሞኑን በስፋት በሚሰራጭ የቪዲዮ መረጃ አንድ እናት ” እንኳንም አልሞትን፣ ከሻዕቢያ ጋር ገጥማችሁ እንኳን አየን፣ እንኳንም አልሞታችሁ። ከሻዕቢያ ጋር ገጥማችሁ …” በማለት ሸዕቢያ በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን እያስታወሱ አንብተዋል።
እለአሃዱ ቃላቸውን የሰጡት ወገኖች ሰላም እንዳይፈጠር ችግር የሚፈጥሩ አካላትለሰላም የሚያደርጉትን ጥሪ አልተቀበሏቸውም፣ በዚሁ ምክኛት በስጋት እነሱ ወዳገኙበት ሲሰደዱ “በቂ ገንዘብ ያላቸው ጓዳኞቻችን ተመቻችቶላቸው ከሀገር አስቀድመው ወጥተዋል” በማለት በድሃ ሕይወት ላይ እንዴት እየተፈረደ እነደሆነ ተናግረዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማናገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት የገለጸው ለአሐዱ፣ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሕዝቦች (ኢህአፓ) ፓርቲ ዋና ሥራ አስኪያጅና የትግራይ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ወኪል ይሳቅ ወልዳይን እና የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃንን አነጋግሯል።
የኢሕአፓ ዋና የሥራ አስፈፃሚ አባሉና የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ተወካይ የሆኑት አቶ ይሳቅ ወልዳይ በሰጡት ምላሽ፤ ህወሓትና የፌደራሉ መንግሥት ወደ ጦርነት በመግባታቸው የትግራይ ወጣት ከኢትዮጵያዊን ወንድም እና እህቶቹ ጋር እንዲዋጋ ሆኗል” ሲሉ አስታውሰዋል።
“እንደ በፊቱ የትግራይ ወጣት ጦርነት አይፈልግም” ያሉት የሥራ አስፈፃሚ አባሉ፤ “አሁን የሚፈልገው ስደት ሳይሆን መማር እና መስራት ወደቀደመው ሕይወቱ መመለስ ነው” ብለዋል።
“የትግራይ ወጣቶች በአሁኑ ሰዓት ለስራ አጥነት፣ ለከፋ ችግር፣ ለጦርነት እና ለግጭት በመጋለጡ ስደትን እየመረጠ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃነ በሰጡት ምላሽ፤ “በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ወታደራዊ አመራሮችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል በተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመግባባት ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠትም ተግዳሮት ሆኗል” ሲሉ ገልጸዋል።
“ወጣቱ ትውልድ በአሁኑ ወቅት ወደ ሳዑዲ አረቢያና በሌሎች ሀገራት በባህር እየተሰደደ ነው፡፡ ይህን ደግሞ እልባት ሊሰጠው ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል። “አሁን ላይ የክልሉ ሕዝብ የሚፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰብዓዊ አቅርቦት እንዲሟሉለት ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
ለአሐዱ ቅሬታቸውን የገለጸት የትግራይ ክልል ወጣቶች በበኩላቸው፤ “የሚመለከተው አካል በሀገራችን በሰላማዊ መንገድ ሰርተን የምንቀየርበትን መንገድ እንዲፈጥርልን እንጠይቃለን” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ከባለፉት ወራቶች ጀምር በስፋት እንደሚገለጸውና የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በተለያዩ አጋጣሚዎች እንዳመለከቱት ሻዕቢያ የትግራይ ወጣቶችን እያፈሰ ወደ ሳዋ እያጋዘ ነው። ሻዕቢያ ይህን ሲያደርግ ዶክተር ደብረጽዮን የሚመሩት ቡድን ያለው ነገር የለም። አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደም በግልጽ የወሰዱት እርምጃ የለም።
ሻዕቢያ በአፋር አቅጣጫ ጦርነት እንዲጀመር የራያና አካባቢውን አስተዳደር የእነ ደብረጽዮን ቡድን እንዲይዘው መመሪያ መስጠቱን የሚናገሩ ሕዝብ በወሰደው አቋም የአስተዳደሮች ሹም ሽር ለጊዜው ተግባራዊ አልሆነም። ሕዝብም በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞ አሰምቷል።
ሕዝብ “የመረጥነው አስተዳደራችን ይመለስልን ፣ ሰላም እንጂ ጦርነት አንሻም፣ እምቢ ለጦርነት እሺ ለሰላም፣ ዳግም ልጆቻችን ለጦርነት አንማግድም፣ የዘውትር ፍላጎታችን መዝሙርና ፀሎታችን ሰላም ነው” በማለት ተቃውሞ ማሰማቱን ተከትሎ “አላማጣ ውስጥ የደቡብ ትግራይ አስተዳዳሪ የሃብቱ ኪሮስ ወንድም እዮብ ኪሮስ በወያኔ አርሚ 24 አባላት በደረሰበት ድብደባ ትናንት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።


