Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ፖሊስ አባይ ወልዱ ቀሚስ ለብሰው መያዛቸውን፣ከባንክ ገንዘብና ወርቅ ተዘርፎ እንዲታደል መደረጉን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረዳ
News

ፖሊስ አባይ ወልዱ ቀሚስ ለብሰው መያዛቸውን፣ከባንክ ገንዘብና ወርቅ ተዘርፎ እንዲታደል መደረጉን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረዳ

Ethioreview newsEthioreview news—January 29, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዛሬ ባስቻለው ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ተደብቀውና ራሳቸውን ቀይረው መያዛቸውን ፖሊስ ሲያስረዳ ” እየተተኮስ መደበቀ አልነበረባቸውም” ሲሉ ጠቆ ላቀረቡት ተቃውሞ ምላሽ ሲሰጥ የቀድሞ የትግራይ ክልል ሊቀመንበር አብይ ወልዱ ራሳቸውን ቀይረው፣ የቄስ ቀሚስ ለብሰውና የራሳቸው ያልሆነ መታወቂያ አዘጋጅተው መያዛቸውን ተሰምቷል። ከስር ሙሉ ሪፖርቱን ከፋና በውመውሰድ አትመነዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በፌፌራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው ጉዳያቸው የታየው ፡፡ የቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የቄስ ልብስ ለብሰው መታወቂያቸውን ቀይረው ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ፖሊስ ለችሎት ገለጸ።በሀገሪቱ ሁከት በመቀስቀስ ሰዎች እንዲገደሉ እና እንዲፈናቀሉ ከማድረግ ጀምሮ የነዳጅ ዲፖ ዘረፋ መፈጸማቸውን የሚያመላክት ማስረጃ መሰብሰቡን መርማሪ ፖሊስ ለችሎት ገልጿል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መርመሪ ቡድን የቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ከንግድ ባንክ በርካታ ገንዘቦችን እና ወርቆችን አውጥተው ወደ ደደቢት ማይክሮ ፋይናነስ ተቋም በማስገባት ከተጠርጣሪ ቤተሰቦች ጀምሮ እስከ በየበረሃው ለነበሩ አመራሮች ሲያከፋፈሉ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷል።

መርማሪ ቡድኑ ይህን የገለጸው ዛሬ በእነስብሀት ነጋ ፤ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ስም በተደራጀ ሶስት መዝገብ የተካተቱ 21 ተጠርጣሪዎችን ፍረድቤት ባቀረበበት ወቅት ነው።በእነ ስብሀት ነጋ፤ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ስም የተዘጋጁ ሶስት መዝገቦች የተካተቱ አጠቃላይ 21 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ በፍርድ ቤት ታይቷል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በቀዳሚነት በስብሀት ነጋ መዝገብ የቀረቡ አጠቃላይ 9 ተጠርጣሪዎችን በቀዳሚነት ተመልክቷል።በዚህ መዝገብ አንደኛ ስብሀት ነጋ፤ አምባሳደር አባዲ ዘሙ፤ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ፤ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ናቸው ጉዳያቸው በቀዳሚነት መዝገብ የታየው።በሁለተኛ መዝገብ ደግሞ አባይ ወልዱ ፤ዶክተር አብርሃም ተከስተ፤ ዶክተር እረዳይ በርሄን ጨምሮ የ9 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ታይቷል።

በሶስተኛ መዝገብ በችሎቱ ጉዳያቸው የታየው የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚያብሔርንም ጉዳይን ችሎቱ ተመልክታል።የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቡድን በቀዳሚነት መዝገብ 1ኛ ስብሀት ነጋ፤ ለፍርድ ቤቱ ባለፈው በተሰጠው የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ያከናወነውን የምርመራ ስራዎች አብራርቷል።

በዚህም የተጠርጣሪዎችን የወንጀል ተሳትፎ በምርመራ የመለየት ስራ ማከናወኑን ገልጿል።ተጠርጣሪዎቹ ከመንግስት መዋቅር ውጪ ተደራጀተው በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ ጊዜያት ሁከትና ገጭት እንዲነሳ ሲያደርጉ አንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን አብራርቷል።ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በሃገሪቱ የብሔር እና የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ የተለያዩ የወንጀል ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎችን ከተለያዩ ክልሎች በመመልመል ወደትግራይ በመላክ አበል በመክፈል ንጹሃን ዜጎች እንዲገደሉና ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ ሲያደረጉ እንደነበር የሚገልጽ ማሰረጃ መሰብሰቡን ለችሎቱ አብራርቷል።

በተለይ 3ኛ፣ 7ኛ፣ 8ኛ እና 9ኛ ተጠርጣሪዎች የህዋሀት ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ እነዚህ ተጠርጣሪዎቹ ካልተያዙ ግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ ዞኖች በመዘዋወር ሌሎች ወጣቶች ለጦርነት እንዲነሳሱ ሲያሰተባብሩና ሲቀሰቅሱ እንደነበረም ማሰረጃ መሰብሰቡንም መርማሪው አክሏል።ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሰሜን ዕዝ ጦር እንዲመታ እና ግጭት እንዲፈጠር እንዲሁም የጦር መሳሪያ አንዲዘረፍ በማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ጦርነት አስነስተው ሲመሩ እንደነበር የሚገልጽ ማስረጃ መሰብሰቡን አመላክቷል።

በተጨማሪም በዚህም ምርመራው የቀድሞ የአዲስ አባባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ እና የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ የነዳጅ ዲፖን ሲያዘርፉ እንዲሁም ምሽግ የሚቆፍሩ መኪኖችን ሲያዘጋጁና ሲያስቆፍሩ አንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሶ የነዳጁ መጠኑን እያጣራ መሆኑን ገልጿል።በስዩም መስፍን የሚመራ ቡድን ተቋቁሞ ለጥፋት ተልዕኮ ሲሰሩ እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ ማሰባሰቡንም የምርመራ ቡድን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ሌሎችም ማስረጃዎችን መሰብሰቡን የገለጸው የምርመራ ቡድኑ በሰው ምስክር ደረጃ 15 ምሰክር ቃል መቀበሉንም ለችሎቱ አብራርቷል፡፡

በክልሉ የፈጠረውን ችግር ተከትሎ ሃገሪቱ ለተለያዩ ሀገራት ስታቀረብ የነበረውን የሃይል ሽያጭ አቅርቦት መጠን እያጣራ መሆኑንም አመላክታል።የደረሰውን የመሰረተ ልማት ውድመት ከኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት እና ከሌሎች ተቋማት የደረሰው ውድመት በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጠው ለየተቋማቱ መላኩን የምርመራ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ጉዳዩን የሚያጣራ ተጨማሪ ቡድን ወደትግራይ ክልል መላኩን እና ሌሎች የሰው ምስክሮችን ቃል ለመቀበል እና የተጠርጣሪዎችን የስልክ ልውውጥ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ምላሽ ለማግኘት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠውም ጠይቋል፡፡በሁለተኛ መዝገብ በተካተቱት የቀድሞ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አባይ ወልዱ ፤ዶክተር አብርሃም ተከስተ፤ ዶክተር እረዳይ በርሄን ጨምሮ 9 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በተሰጠው 14 ቀን ወስጥ የሰራወን በርከታ ምረመራ አብራርታል።የወንጀል ተሳትፎ ነበራቸው ሲል የሰበሰበውን ማሰረጃ ከምርመራ መዝገቡ ጋር ማያየዙን ጠቅሷል።

ከዚህ ውስጥም በተለይም የቀድሞ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ከንግድ ባንክ በርካታ ገንዘቦችን እና ወርቆችን አውጥተው ወደ ደደቢት ማይክሮ ፋይናነስ ተቋም በማስገባት ከተጠርጣሪ ቤተሰቦች ጀምሮ እስከ በየበረሃው ለነበሩ አመራሮች ሲያከፋፈሉ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሳል።እንዲሁም ለምሽግ ቁፋሮ መኪኖቸን ሲያዘጋጁ አንደነበር ፖሊስ በምርመራ ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷልበሶስተኛ መዝገብ በችሎቱ ጉዳያቸው የታየው የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ የወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚያብሔርንም ጉዳይን ችሎቱ ተመልክታል።

እነዚህ ተጠርጠሪዎች በዞን የጦርነቱ ቅስቀሳ በማድረግ በሃሳብና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ መጠርጠራቸውን ተከትሎ ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷል፡፡በዚህ መልኩ ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸወን ቀይረው አለባበሳቸወን ቀይረው ተደብቀው ሲቀሳቀሱ ነበር ብሏል ፖሊስ ለችሎቱ ሲያብራራ፡፡የተጠርጣሪ ጠበቆች ማንነታቸውን ደብቀው ሲርመሰመሱ ነበር ማለቱ አግባበነት የለውም ብሎ ላቀረቡት መቃወሚያ መርመራ ፖሊስ ምላሽ ሰጥቷል።

በዚህም ምላሹ የቀድሞ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የቄስ ልብስ ለብሰው መታወቂያቸውን ቀይረው ከነ መታወቂያቸው መያዛቸውን ፖሊስ ለችሎት አብራርቷል።የተጠርጣሪ ጠበቃም ከባድ መሳሪያ ሲተኮስባቸው ቤታቸው ቁጭ እንዲሉ ነው ወይ የሚፈለገው ሲል መደበቃቸው ተገቢነት እንዳለው ሲከራከር ተደምጧል።በዚህ መልኩ ጠበቆቻቸው ከዶ/ር ሰለሞን እና ከዶ/ር አብርሃም ውጪ ባሉት ተጠርጣሪዎች ላይ የያንዳንዳቸው የወንጀል ተሳትፏቸው በግልጽ ተለይቶ አልቀረበም የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።

ባለፈው ካቀረበው የምርመራ ውጤት የተለየ ነገር ይዞ አልመጣም ፤ የተጠቀሱትም በአገሪቱ በስፋት ሲነገሩ የነበሩ የፖለቲካ ይዘቶች ናቸው በዚህ መልኩ በዚህ ችሎት ሊገለጽ አይገባም ፤ እኛም መከላከል አያስችለንም ስለዚህ በዚህ ችሎት የፖለቲካ ጉዳዮች መቅረብ የለባቸወም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።ፍርድ ቤቱም እናንተም ጠበቆቸም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሃሳቦች እያነሳቸሁ ነው በሁለታችሁም በኩል ሊነሱ አይገባም ሲል አጽንኦት ሰጥቷል።

ተጠርጣሪዎቹም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ምስላቸው መታየቱ ተገቢነት የለውም፤ በመገናኛ በዙሃን ሚዛናዊ ዘገባ ሊቀርብ ይገባል የሚሉ አቤቱታም አሰምተዋል።በተጨማሪም ወ/ሮ ኬሪያና ወ/ሮ ሙሉ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ከብዙ ቀናቶች በኋላ ፍርድቤት መቅረባቸው ተገቢ አደለም የሚሉ መቃወሚያዎች እና የፖሊስን ምላሽ አጠቃላይ የግራ ክርክርሩን ያደመጠው ችሎቱ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል ለተባለው በሰጠው ገለጻ በመከላከያና በፌዴራል እየተያዙ የነበሩ በመሆኑ የሌሎችም ተጠርጣሪዎች እስኪለዩ መቆየታቸውን ከግምት ወስጥ መግባቱን ጠቅሷል።ይሀን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሁለቱ ተጠርጣሪዎች ምርመራ በተፋጠነ መልኩ እንዲከናወን አዟል።በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ 14 የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለየካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በማይካድራ እስከአሁን 117 መቃብሮች ተገኝተዋል፤ ጋዜጠኖች በነጻነት እንዲዘግቡ ተፈቀደ
የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የመጥፋት አደጋ! የአባያና ጫሞ ሀይቆች በደለል መሞላትና በእምቦጭ አረም መወረር
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2