Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  አዲስ አበባ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
News

አዲስ አበባ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

Ethioreview newsEthioreview news—February 3, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልዕኮ በመቀበል አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የዲፖሎማሲ ተቋማት መቀመጫ የሆነቸውን  የአዲስ አበባን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን 15 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር  እንዲውሉ ማድረጉን አስታውቋል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ  ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የተደራጀ የህቡዕ ቡድን መስርተውና ከሽብር አቀነባባሪዎች የውጭ ተልዕኮ ተቀብለው  በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ የቆዩት አሸባሪዎች ለጥቃት  ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችና ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶችና  የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል።

የህቡዕ ቡድኑ በአዲስ አበባው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት፣ የጥናትና የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ሲያካሂድ እንደቆየ የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች መገኘታቸውን የጠቆመው መግለጫው፤ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከህዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ  ከሌሎች የሀገር ውስጥና የውጭ መረጃ ተቋማት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትልና የመረጃ ልውውጥ በማድረግ  የታቀደውን የሽብር ጥቃት ማክሸፍ ችሏል።

በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ በህቡዕ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል ጥቂቶቹ ከመያዛቸው በፊት በኤምባሲው ህንጻ አካባቢ ከፍተኛ የጦር መሣሪያ ይዘው ለድብቅ ሴራቸው ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም በክትትል መታወቁን መግለጫው አትቷል።\

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቡድኑን አባላት ሲመራ የነበረው የ35 ዓመቱ አሊ አህመድ አርዳይቶ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ለአሊ አህመድ አርዳይቶ ለሽብር ጥቃቱ ማቀነባበሪያነት እንዲውል  በአሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር እንደተላከለት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማረጋገጥ እንደተቻለ  የጠቆመው መግለጫው፤ ከዚህ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበረውና የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡህ  ሲያሴር የቆየው መሃሙድ አብዱልቃኒ የተባለ ሌላ ተጠርጣሪም ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት በመኖሪያ ቤቱ የጦር መሣሪያዎች፣ ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶችና ሰነዶች መያዛቸውን  አስታውቋል።

ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶች

ሌላ ተመሳሳይ ተልዕኮ የተሠጠው ህቡዕ ቡድንም በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ  የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የጠቆመው መግለጫው፤ መረጃውን  ቀድሞ ያገኘውና  ክትትል ሲያደርግ የቆየው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የግንኙነት መረቡን ለመበጣጠስ እንዲሁም ተጠርጣሪዎችን አድኖ ለመያዝም  ከሱዳን የመረጃና የደህንነት ተቋም ጋር በቅንጅት መሰራቱን  ጠቁሟል።

ለህቡዕ የሽብር ቡድኑ መሪ ከውጭ አመራር የሚሰጠው ኑሮውን በስውዲን ያደረገው አህመድ እስማኤል የተባለ ግለሰብ ሲሆን፤ የሽብር ጥቃት ዕቅድ በማውጣትና ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአዲስ አበባ የተባበሩት  አረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ የደህንነት መረጃዎች እንዲሰበሰቡ አቅጣጫ ሲሰጥ ቆይቷል። የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በህቡዕ የተደራጀው የሽብር ቡድን እንቅስቃሴን በተመለከተ ከአውሮፓ፣አፍሪካና እስያ የመረጃና ደህነንት ተቋማት ጋር የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥና ብርቱ ክትትል በማድረግ አህመድ እስማኤል በስውዲን ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ሊቃጣ የነበረው የሽብር ጥቃት የከሸፈው አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከውጪና ከሀገር ውስጥ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ጋር የተቀናጀ ክትትልና የመረጃ ልውውጥ በማደረጉ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተቀነባበረው የሽብር ሴራ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያና ከስዊድን በተጨማሪ  በሌሎች ሀገራትም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አመልክቷል። ሌሎች ከሴራው ጋር ግንኙነት  ያለቸውና በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ 21 ተጠርጣሪ ግለሰቦችንም  በቁጥጥር ሥር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን መግለጫው አመልክቷል። በአገር ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሽብር ቡድኖቹ አባላትና ግብረ አበሮቻቸው በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርምራ ቢሮ ጉዳያቸው በመጣራት ላይ እንደሚገኝ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የብሔራዊ  መረጃና ደህንነት አገልግሎት  ለመገናኛ  ብዙሃን  በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ አባላትን በመመለመል፣ የሽብር እቅድ በማውጣትና ኢላማዎችን በመለየት አዲስ አበባና ሱዳን በሚገኙት የተባበሩት አረብ  ኢሚሬትስ ኤምባሲዎች ላይ  ጥቃቶችን ለመፈጸም ስምሪት ወስደው  እንቅስቃሴ  በማድረግ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪ የሽብር ቡድኖቹ አባላት እንዲያዙ ሲደረግ፤ህብረተሰቡ ያደረገው ተሳትፎም ከፍተኛ እንደነበር ጠቁሟል።

በቀጣይም ህዝባችን ይሄን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደረግና የተለየ ነገር ሲመለከትም በአካባቢው ላለ የፀጥታ አካል መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል አገልግሉት መስሪያ ቤቱ  ጥሪ አቅርቧል።

FBC

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ …illegal foreign interference in the internal affairs of states has only led to chaos”Russian Senator
Biden signs orders on migrant family separations, asylum
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2