Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በሱዳን ካርቱም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በራሳቸው ገንዘብ ነዳጅ እና ዳቦ እንኳ ለመግዛት በመከልከላቸው መቸገራቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
News

በሱዳን ካርቱም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በራሳቸው ገንዘብ ነዳጅ እና ዳቦ እንኳ ለመግዛት በመከልከላቸው መቸገራቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

Ethioreview newsEthioreview news—February 27, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ቢቢሲ ያነጋገራቸው በካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንዳስረዱት በአለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የስደተኛ እውቅና አግኝተው ለረዥም ዓመታት በከተማው የኖሩ ቢሆኑም የአገሪቱ ፖሊስ እንግልት እያደረሰባቸው መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል።

እነዚህ ስደተኞች እንደሚናገሩት ከሆነ በተለይም ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ይገባኛል የተነሳ ውዝግብ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ በብዙ ፍራቻና ስጋት ውስጥ እንደሚኖሩ ይናገራሉ።

ስደተኞቹ ከኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት የወጡና ለአመታትም ሱዳንን መኖሪያቸው ያደረጉ ናቸው።

በአገሪቱ ፖሊስ የሚደርስባቸውን እንግልት በመጥቀስ ለጥያቄያችን መልስ አልተሰጠንም ያሉት ስደተኞቹ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሥደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን /ዩኤንኤችሲአር/ ግቢ ውስጥ ለሶስት ወራት ከኖሩ በኋላ በመኪና ተወስደው የካርቱም የከተማው ቆሻሻ የሚደፋበት ስፍራ ላይ እንዲቆዩ መደረጋቸውንም ይናገራሉ።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ስደተኞቹ አክለውም አሁን እንዲኖሩበት የተደረገው ይህ ስፍራ ከካርቱም ውጪ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርስቲ በስተጀርባ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በስፍራው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ብቻ ከ700 በላይ አባወራዎች እንደሚገኙ ገልፀው የኮንጎ፣ ብሩንዲ፣ ኤርትራ እና ሌሎች አፍሪካ አገራት ስደተኞች ይገኛሉ ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው በሱዳን ካርቱም የሚኖሩት ስደተኞች እያጋጠማቸው ባለው ችግር ሴቶችና ሕጻናት የበለጠ ተጎጂ መሆናቸውን ይናገራሉ።

እነዚህ ስደተኞች የተሟላ የስደተኛ ሰነድ ያላቸው ቢሆንም ችግር እየደረሰባቸው መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል።

በጎዳና ላይ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የአገሪቱ ፖሊስ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚያደርስባቸውም ይገልጻሉ።

ቢቢሲ ካነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከልጆቻቸው ጋር እየተቸገሩ መሆኑን የገለፁት የአራት ልጆች እናት የሆኑት ኩለኒ በየነ ላለፉት 28 ዓመታት በሱዳን ካርቱም ኖረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ስር ተመዝግበው የስደተኛ እውቅና ቢሰጣቸውም አሁን ግን የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ኩለኒ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ከተነሳ ወዲህ የሚደርስባቸው እንግልት መጨመሩን ያስረዳሉ።

ሌላዋ ቢቢሲ ያነጋገራቸውና የሰባት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ የሺ ከበደ ደግሞ “ልጆችን ይዤ መንገድ ላይ እየተቸገርኩ ነኝ፤ ባለቤቴ ብቻ ነው እየሰራ ያለው፤ ልጆቻችንን የምናሳድግበት አጥተን እየተቸገርን ነው” ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

አቶ ዮሐንስ ሳሙዔል በምስራቅ ሱዳን ከሰላ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ ለስድስት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ካርቱም ገብቶ ሁሉንም የስደተኝነት መስፈርት በማሟላቱ ረዥም ዓመታት ቢኖሩም በአሁኑ ሰዓት ግን መብታቸው እየተገፈፈ መሆኑን ይናገራሉ።

“በምሽት ፖሊሶች መጥተው በብዙ መኪና ጭነውን ከከተማ አውጥተውን ካርቱም ከተማ ቆሻሻ የሚጣልበት ስፍራ ጥለውን ተመለሱ። . . . የምንጠለልበት የለም፤ የሚሰጠን ድጋፍም የለም፤ አሁን የግል ኮንቴይነር አግኝተን በጋራ እየኖርን ነው” ብለዋል አቶ ዮሐንስ።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከስድስት አገራት የመጡ ስደተኞች በዚህ ስፍራ እንደሚገኙም አቶ ዮሐንስ ጨምረው አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ አንዳንድ ዜጎች የሚደርስባቸውን ሲናገሩም “ዳቦ ለመግዛት በምንሰለፍበት ከሰልፉ ያባርሩናል፤ ነዳጅ ለእኛ አይሸጡም። የድንበር ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ደግሞ ከመኪና ውስጥም ያስወርዱናል” ብለዋል።

በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስደተኞች ያላቸውን ስጋት እንደሚያውቅ ገልፆ፣ በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ በተለየ በአገሪቷ መንግሥት እውቅና የደረሰ ችግር ባይኖርም “ውስጥ ውስጡን ጉዳት እየደረሰ መሆኑን እናውቃለን” ብሏል።

ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራዎች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሚካኤል ጦብያስ በከተማ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለአገሪቷ መንግሥት አሳውቀው መፍትሄ እንዲያገኝ እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

አቶ ሚካኤል በካርቱም ከተማ ውስጥ በተለያየ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ችግሮች እንደሚገጥማቸው እንደሚያውቁ ለቢቢሲ አስረድተዋል።

የሱዳን ፖሊስም በእነዚህ ስደተኞች ላይ የመብት ጥሰትን እየፈፀመ እንደሚገኝ በመናገር ‘በድፍረት እንዳንጠይቅ ወይንም እንዳንከራከር ብዙዎቹ ከሕግ ውጪ ወደ አገሪቷ መግባታቸውን’ እንዳገዳቸው ይገልጻሉ።

የአገሪቷ የሰብዓዊ መብቶች እና የፍትህ አሰጣጥ ሂደት ደካማ ስለሆነ ፖሊስ በሰጠው ማስረጃ እና ቃል ብቻ ፍርድ ቤቱም ፍርድ ሲሰጥ እንደቆየ ጨምረው አስረድተዋል።

በዚሁ አካሄድ ብዙ ሰዎች ከአገር እንዲወጡ ተደርጓል ሲሉ አቶ ሚካኤል ተናግረዋል።

“ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥብቻ በዚህ መንገድ 220 የሚሆኑ ሰዎች ተይዘው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፤ ሌሎች ሰዎችን ደግሞ ያለፈቃድ ሰርታችኋል በማለት ፖሊስ ሲቀጣቸው ቆይቷል።”

አቶ ሚካኤል እንደሚሉት የኢትዮጵያ ስደተኞችም ሆነ ሌሎች በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ጊዜ በእስር የሚቆዩበት ሁኔታ የጤናና ምግብ አገልግሎት ችግር እንዳለበት ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩልም በሕገወጥ ወደ አገሯ የገቡን የተወሰኑትን እያሩሌሎቹ ደግሞ እየመለሰች መሆኑን ተስተውሏል።

የኢትዮጵያ ስደተኞች ስጋት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የመጣው በሁለት ምክንያት መሆኑን የዲያስፖራ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ሚካኤል ያብራራሉ።

የመጀመሪያው የአገሪቷ ምጣኔ ኃብት መዳከም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያጋጠመ ሲሆን የሚቀርበው ዳቦ እና ነዳጅ ከፍተኛ እጥረት ማጋጠሙን ገልፀዋል።

ከዚህም የተነሳ የአገሪቷ ዜጎች ስደተኞች ናቸው ስራ እየቀሙን በማለት እንደሚቃወሙ ይናገራሉ።

ሌላኛው ምክንያት ብለው የሚጠቅሱት በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ ሲሆን ‘ድንበር ላይ ሰዎቻችንን ትገድላላችሁ፤ እዚህ ደግሞ ዳቦችንን እየተሻማችሁ ትበላላችሁ’ በማለት ጫና አያደረጉ መሆናቸውን መስማታቸውን ተናግረዋል።

በሳምንት ቢያንስ ወደ አስር የሚሆን አውቶብስ ስደተኞች በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አቶ ሚካኤል ጨምረው አስረድተዋል።

በዩኤን ኤችሲአር ስር ተመዝግበው ያሉ ስደተኞች ወደ ኤምባሲ ስለማይመጡ መርዳት እንደማይችሉም አሳስበዋል።

“ቢሆንም ግን ዜጎቻችን ስለሆኑ መብቶቻቸው እንዲከበሩ የአገሪቷን መንግሥት ስናሳስብ ቆይተናል” ብለዋል።

በእነዚህ ስደተኞች የቀረበውን ቅሬታ ይዘን የዩኤን ኤች ሲአር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

bbc Amharic

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ዳንኤል ክብረት በግሉ ምርጫ ይወዳደራል ፤ ብልጽግና ታዋቂ ሰዎችን ለእጩነት ለማቅረብ እየጣረ ነው
Response of the Eritrean Delegation to the Oral Report of the High Commissioner of the OHCHR
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2