Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የዐድዋ ድል – ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለማለያየት፣ ለማበጣበጥና ለማባላት፣ የተደረጉት ሙከራዎች ሁሉ የከሸፉበት…
News

የዐድዋ ድል – ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለማለያየት፣ ለማበጣበጥና ለማባላት፣ የተደረጉት ሙከራዎች ሁሉ የከሸፉበት…

Ethioreview newsEthioreview news—March 1, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

እንኳን ለ125ኛው የዐድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የዐድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የጀግነት፣ የሀገር ፍቅር ስሜትና የጦርነት ጥበብ ውጤት ነው። ጎራዴ ታጥቆ መድፈኛን ለመጣል ከመንደርደር የበለጠ ጀግንነት የለም። ልዩነትን ወደ ጎን ጥሎ በጋራ ለአንድ ሀገር ግንባርን ለባሩድ፣ አንገትን ለካራ ከማቅረብ በላይ የጠለቀ የሀገር ፍቅር ከየትም አይመጣም። ሰፊ ጊዜ ወስዶ ራሱን በሴራና በስትራቴጂ ሲያዘጋጅ እና ከሌሎች በሚያገኘው እገዛ ሲደራጅ የከረመ ኃይልን ጥቃት መክቶ መልሶ በማጥቃት ማሸነፍ በቀላል ብልሃት የሚሆን አይደለም።

በደምና በላብ የወዛ፣ በሥጋና በአጥንት የቆመ፣ በጥበብና በመደመር የደመቀ የዐድዋ ድላችንን እኛ ለኢትዮጵያውያን የተለየ ትርጉም ሰጥተን እንድናከብረው የሚያደርጉን ብዙ ምክንያቶች አሉ። ከእነዚህ መሐል አንዱ፥ የዐድዋ ድል ሀገራችንን ማንም ሊያወርዳት ከማይችልበት ከፍታ ላይ የሰቀላት በመሆኑ ነው። ሀገራችንን ከዚህ ከፍታ ላይ ገፍትሮ ለመጣል ባለፉት ብዙ ዘመናት አያሌ ጥረቶች ተደርገዋል። በቅርቡ ታሪካችንም እንዲሁ። ግን አልተቻለም። ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለማለያየት፣ ለማበጣበጥና ለማባላት፣ የተደረጉት ሙከራዎች ሁሉ የከሸፉት በዚህ የተነሣ ነው።

ዐድዋ በከፍታ ላይ ከሰቀላቸው የኢትዮጵያ ዕሴቶች አንዱ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ነው። ከምዕራብና ከምሥራቅ፣ ከሰሜንና ከደቡብ የዘመቱ፤ በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በመልክና በሞያ ኅብር የሆኑ፤ ነገር ግን ኢትዮጵያን ከቅኝ ግዛት የማዳን የአንድነት ዓላማ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያስገኙት ድል ነው። በዐድዋ ዘመቻ ከ10 ዓመት ሕጻን እስከ 90 ዓመት አዛውንት ተካፍለዋል። ማየት የቻሉት ብቻ ሳይሆኑ ዓይነ ሥውራንም ዘምተዋል። ሴቶች ከስንቅ አዘጋጅነት እስከ ጦር መሪነት ተሰልፈዋል። የእስልምናና የክርስትና የሃይማኖት አባቶች ከጸሎት እስከ ግንባር ተሳትፈዋል። አዝማሪዎች በአንድ በኩል የሠራዊቱን ሞራል እየገነቡ፣ በሌላ በኩል ታሪኩን በግጥምና በዜማ እየከተቡ ዘምተዋል። ሌላው ቀርቶ ሽምጥ ጋላቢዎቹ ፈረሶቻችን በወኔ እሳቱ መሐል ሲገኙ፣ የጭነት አጋሰሶች በፈርጣማ ትከሻዎቻቸው ስንቅ ተጭነው፣ ሌሎችም እንስሳት መሥዋዕት ሆነው ዐድዋን የድል ቦታ፣ ኢትዮጵያን የድል ባለቤት አድርገዋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ዛሬ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ብንገባ፣ የትኛውንም የብሔር ብሔረሰብ ታሪክ ብናጠና፣ በየትኛውም የሀገሪቱ አቅጣጫ ሄደን ብንጠይቅ፣ አያቶቹ ወደ ዐድዋ ያልዘመቱ ሕዝብ አናገኝም። መንገድና መገናኛ ባልተስፋፋበት፣ ዘመናዊ መጓጓዣ ባልነበረበት በዚያ ዘመን፣ ከመቶ ሺህ በላይ ሠራዊት ጫካዎቹንና ተራሮቹን በእግሩ እያቋረጠ የመጣው ኢትዮጵያን ብሎ ነው። መንግሥታዊ ሥርዓቱ ተመችቶት፣ አገዛዙ ተስማምቶት አልነበረም። ኢትዮጵያ የምትባል፣ አያት ቅድመ አያቱ የነገሩት ሀገር ስለተነካችበት ነው። በትራንስፖርትና በመገናኛ እጥረት ሀገሩን ዞሮ ባያያትም፣ ሁሉም ግን ሀገሩ በልቡ ነበረች፤ ኮርታና ታፍራ የኖረች ብርቅዬ ሀገሩ በደም ሥሩ ውስጥ ትዘዋወራለች።

ይህ ሁሉ ኅብረ ብሔራዊ ሠራዊት የተለያየ ቋንቋ እየተናገረ፣ የተለያየ እምነት እያመነ፣ የተለያየ ዓይነት ምግብ እየተመገበ፣ የተለያየ ዓይነት ልብስ ለብሶ፣ የተለያየ ዓይነት ባህል ይዞ፣ በምን እየተግባባ ዘመተ? የሚለውን መጠየቅ ተገቢ ነው። የተግባባው በኢትዮጵያዊነቱ ነበር። ኢትዮጵያዊ ኅብረ ብሔራዊነታችን መግባቢያ ቋንቋ ነውና። አንድነታችን የሚሠራበት ሰበዝ፣ ጥንካሬያችንን የሚገነባው ቅመም፣ ውበታችን የሚኳልበት ቀለም የሚቀዳው ከሌላ ሳይሆን ከኅብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊነታችን ነውና።

ልዩነትን የማግባቢያ ፍቱን መድኃኒቱ የላቀ ዓላማ መሆኑን የዐድዋ ዐርበኞች ነግረውናል። ማንም ከማይደርስበት ማማ ላይ የሰቀሉት ሌላው ዕሴታችን ይሄ ነው። ከግል ጥቅም፣ ከራስ ዝናና ከጊዜያዊ ሥልጣን የበለጠ፣ ዘለዓለማዊ የሆነ፣ ትውልድን የሚታደግ፣ ሀገርን የሚገነባ፣ የላቀ ዓላማ ካለ ልዩነቶች ሁሉ ውበት ብቻ ሳይሆኑ ጥንካሬ መሆናቸው የዐድዋ ዐርበኞች አስመስክረዋል። ልዩነቶች ለሀገር አንድነትና ለሕዝቦች መስተጋብር ፈተናዎች የሚሆኑት ሊያግባባቸው የሚችል የላቀ ዓላማ ከሌለ ብቻ ነው።

የዐድዋ ዘመቻ ኢትዮጵያውያንን ከጥንቱ በተሻለ ያስተሣሠረ ዘመቻ ነበረ። ኢትዮጵያውያን ከአራቱም ማዕዘን፣ ከሁሉም ብሔሮች፣ ከሁሉም እምነቶች፣ ከሁሉም ዓይነቶች ለአንድ ዓላማ፣ በአንድ ቦታ በዚህ መልኩ መገናኘታቸው ያጠራጥራል። ይብዛም ይነሥም ዛሬ ያለችውን ኢትዮጵያ የሚወክሉ ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ወረኢሉ ላይ ተገናኝተዋል። ዐድዋ ላይ ዘምተዋል። ለዚህም ነው ብዙ ምሁራን ዐድዋ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሠረት ነው የሚሉት። እኛ ሁላችን የዐድዋ ልጆች ነን የምንለውም ለዚህ ነው።
በውጊያው ጊዜ ከቅድመ አያቶቻችን መካከል አንዳቸው ጎድለው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ዐድዋም፣ የዐድዋ ልጅነትም ከእናካቴው ባልኖሩ ነበር። የሀገርን ጥሪ እኩል ሰምተው በጋራ ባይዘምቱና ዐድዋ ላይ የድል ሰንደቅ ባይተክሉ ኖሮ፥ ዛሬ የምናከብረው የድል ቀን መሆኑ ቀርቶ እንደሌሎች አፍሪካውያን የነጻነት ቀን በሆነ ነበር። በድል ቀንና በነጻነት ቀን መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለ። ዐድዋ ከእኛ የድል ሰንደቅነት አልፎ ተርፎ ለብዙ የነጻነት ቀኖች እንደ ምንጭ ሆኖ ያገለገለ፣ ለጸረ ቅኝ አገዛዝ እንቅስቃሴዎች ፋና የለኮሰ፣ በሁለት ዘሮች በጥቁሮችና በነጮች መካከል የተገነባውን የበታችነትና የበላይነት ግንብ የፈረካከሰ፣ ባለ ብዙ መልክ ትዕምርት ነው።

ኢትዮጵያውያን ብዙ ጥፋቶችን ይታገሣሉ። መሪዎችና ቡድኖች የሚፈጽሟቸውን ስሕተቶች ይታገሣሉ። የመታረሚያና የመስተካከያ ጊዜ ይሰጣሉ። የመሪዎችና የቡድኖች ስሕተቶች ሀገራቸውን እንዲያፈርሱ ግን አይፈቅዱም። ይሄን የኢትዮጵያውያን ዕሳቤ የማይረዱ አካላት ተደጋጋሚ ስሕተት በታሪክ ውስጥ ሠርተዋል። ኢትዮጵያውያን ነገሮችን ሲታገሡ የደከሙ፤ የተከፋፈሉ፤ አንድ ሆነው መቆም የማይችሉ ይመስሏቸዋል። በዐድዋ ዘመቻ ጊዜ ጣልያኖች ይሄንን ስሕተት ሠርተውታል። በኢትዮጵያ የአካባቢ መሪዎች መካከል የነበረው ትግል የሕዝቡ መለያየት የፈጠረው መስሏቸዋል። ሕዝቡ ነገሮችን በትዕግሥት እየተመለከታቸው መሆኑን አላወቁም። የመሪዎቹ እና የቡድኖቹ ስሕተቶች ሀገር የሚያፈርስ መስሎ ሲሰማው እንደ በረሐ ንብ ሆ ብሎ ተነሥቶ ሀገሩን እንደሚያድን አላወቁም።

በቅርቡም ጁንታው የጣልያንን የመቶ ሃያ አምስት ዓመት ስሕተት ደግሞ ተሳስቷል። ኢትዮጵያውያን በትዝብት ዝም ሲሉ፤ ጥቂቶች በየሚዲያው ኃይለ ቃል ሲወራወሩ፤ እዚህም እዚያም በሚፈጠሩ ግጭቶች ወገኖቻችን መከራ ሲቀበሉ፤ ውጥረት የነገሠ ሀገር የተተራመሰ ሲመስለው – ኢትዮጵያን የማፍረሻ ጊዜው አሁን ነው ብሎ ተነሣ። ኢትዮጵያውያን ጁንታውን የታገሡት የመታረሚያና የመስተካከያ ጊዜ ለመስጠት መሆኑን ረሳው። ‹ሲተኙ እንደ ሬሳ፣ ሲነሡ እንደ አንበሳ› የተባለላቸው መሆናቸውን ዘነጋው። ሀገራቸው አደጋ ላይ ወደቀች መሆኑን ሲያረጋግጡ ሁሉን ነገራቸውን ትተው፣ በኢትዮጵያዊነታቸው ተግባብተው እንደሚዘምቱ አላወቀም። የሆነው ግን ይሄው ነበር።

ዐድዋ የዕርቅንና የይቅርታን ኃይል ያሳየ ድል ነው። በየአካባቢው በነበሩ ግጭቶችና ውጊያዎች የተቀያየሙ መሪዎች ነበሩ። ጣልያኞችም እነዚህን ቅያሜዎች አስፍተው ኢትዮጵያውያንን ማንበርከክ እንደሚችሉ ገምተው ነበር። ሂሳባቸው ግን የተሳሳተ መሆኑን ያወቁት ወዲያው ነው። ኢትዮጵያውያን ቅሬታቸውን በዕርቅ፣ ቅያሜያቸውን በይቅርታ ሻሩት። ‹ሁሉም ከሀገር አይበልጥም› በሚለው የኢትዮጵያውያን የቆየ መርሕ መሠረት ከመንግሥት ጋር የተጣሉት ሳይቀሩ ለሀገራቸው ለመሞት መጡ። ሀገርና መንግሥት የተለያዩ መሆናቸውን የሚያውቁት ኢትዮጵያውያን፣ ሀገርን የሚያድነው ዕርቅና ይቅርታ መሆናቸውን አምነው ንቃቃቱን ዘጉት። በተለያዩ አካባቢዎች አኩርፈው የሸፈቱ ሳይቀሩ ዕርቅና ሰላም እያወረዱ ከዐድዋው ዘማች ጋር ተቀላቅለዋል።

ዐድዋ የኢትዮጵያውያን የአመራር ጥበብ የታየበት ድል ነው። ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ በአራት መንገድ ሠራዊቱን አደራጅተዋል። የኋላ ኋላ ዕውን የሆነው ድል በአንድ ጀንበር የመጣ ድል አልነበረም። ብርቱ የሀገር ልጆች በተለያዩ መንገዶች መሣሪያ በማሰባሰብ፣ ስንቅ በማዘጋጀት፣ ጥቂት ጊዜ መግዛት የሚያስችል የዲፕሎማሲና በመረጃዎች የመራቀቅ ሥራዎችን በማከናወን እና ሠራዊቱን አደራጅተው በመዝመት ያንን ድል አሳክተዋል። በየምዕራፉ የነበረውን ፈተና በልኩ እየተጋፈጡ፣ ጥቃቅን ችግሮችን እየታገሡ፣ በጸና ዲስፕሊን እየተመሩ፣ ብልጫ ሊገኝበት የሚቻልበትን መንገድ እየተጠቀሙ፣ የጠላት ጓዳ ጎድጓዳ ውስጥ ገብቶ ጠቃሚ መረጃዎችን እየመነተፉ በመታገል የተገኘ ድል ነው። ይህ የመሪዎችን የአመራር ብልሃትና የሠራዊቱን መርሕ ጠባቂነት ያሳየ ነበር። የአመራር ብልሃት፣ የመሣሪያ አጠቃቀም፣ የሠራዊት ብቃትና የመልክአ ምድር አያያዝ ተባብረው ያስገኙት ድል ነው።

በአጠቃላይ የዐድዋ ድል የማይቻል የሚመስለው የተቻለበት፣ የማይቀየረው የተቀየረበት ታሪካዊ ድል ነው። ያልዘመነ ጦር የታጠቀ አፍሪካዊ ኃይል ልዩ ልዩ የዘመኑ የጦር መሳሪያዎችን እስከ አፍንጫው የታጠቀ አውሮፓዊ ኃይል ድባቅ መትቶ የጣለበት ውብ አጋጣሚ ነው። የማይቀየር የሚመስለው የነጮች የበላይነት ታሪክ በጥቋቁር አናብስት የተሸነፈበት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ጥቁር ፈርጥ ሆና ብቅ ያለችበት ድንቅ ጊዜ ነው። ዛሬ እንደ ተዓምር የምናያቸው ጉዳዮች፣ ከበለጸጉት ሀገራት ተርታ የመሰለፍ ጉዟችን በእርግጥም የሚሳኩ ስለመሆናቸው፣ የድህነት ታሪካችን በብልጽግና የማይሸነፍበት ምንም ምክንያት ስላለመኖሩ ከዐድዋ በላይ ምስክር ፈልጎ ማግኘት አይቻልም።
እናም ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የምንጓዝበት መንገድ ከዐድዋ ዕሴቶች መቀዳት አለበት። ዐድዋ ድል ብቻ አይደለም። ዐድዋ የኢትዮጵያ መለያ ‹ብራንድ› ነው። የኢትዮጵያውያን ከፍታ እንዴት ሊመጣ እንደሚችል የሚያሳይ ፍልስፍና ነው። ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከመተንተን ይልቅ ዐድዋን ማሳየት በሚገባ ለመረዳት ያስችላል። መሪና ተመሪ ተናቦና ተገናዝቦ ከሠራ ውጤቱ እንዴት ዓለምን እንደሚቀይር ዐድዋ የዘለዓለም ማሳያ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካና ለዓለም የሚተርፍ ሐሳብ እንዳለን ዐድዋ ትልቁ ምስክራችን ነው፤ ለወደፊትም ዐደዋን የመሰሉ፣ እንደ ዐደዋ የገዘፉ ምስክሮች እንደሚበዙልን አልጠራጠርም።

ጉዟችን ኢትዮጵያን ወደ ቀጣዩ ከፍታ ማሻገር ነው። የዐድዋን ሪከርድ መስበር ነው። እንደምንችል አረጋግጠናል፤ እንደምንችል ማሳየት ግን ይቀረናል። ሰንኮፎቻችን ሁሉ ቀስ በቀስ እየተነቀሉና መንሳፈፊያ ክንፎቻችን እየተዘረጉ ሲመጡ ያለ ጥርጥር ዘመናችን ብሩኅ ይሆናል፤ ጉዞውን ጀምረናል። ወደ ዐድዋ መድረሻው መንገድ ፈታኝ ነበር፤ የዐድዋ ድል ግን ጣፋጭ ነው። ወደ ብልጽግና መድረሻ መንገዳችን ፈታኝ ይሆን ይሆናል። ብልጽግናችን ግን እንደ ዐድዋ ሁሉ አይቀሬ ድል ነው። ኢትዮጵያ ከዐድዋ በታች አትወርድም። ከዐድዋ በላይ ወዳለው ከፍታ ደግሞ አንድ ሆነን እኛ እናወጣታለን።

መልካም የድል በዓል ለሁላችንም ይሁን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
የካቲት 22፣ 2013 ዓ.ም PM Abiy Ahemed

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
First Russian warship enters Port Sudan ahead of plans to open naval base: Interfax
Archdiocese of EOC Says Imposter Amnesty International Witness Not Follower of Church
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2