እ.ኤ.አ በ2022 የሚካሄደውን ሁለተኛውን የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባዔን ለማስተናገድ ፍላጎት እንዳላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ከሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ፎረም ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭን ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል። ውይይታቸው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2022 የሚካሄደውን ሁለተኛውን የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባዔን ለማስተናገድ ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ከሩሲያ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት ለክቡር አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ገልጸውላቸዋል።
አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ስለጽ/ቤታቸው ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የአፍሪካና ሩሲያ ኩባንያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል የኢኮኖሚ ትብብር ማህበር መቋቋሙን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመጪው ክረምት ከአፍሪካ ህብረትና ከአፍሪካ አገራት ጋር ምክክር እንደሚደረግም ገልጸዋል።
ሩሲያ ይህንን መድረክ ለመፍጠር የወሰደችውን ተነሳሽነት አድንቀው ሁለተኛውን የአፍሪካ ሩሲያ ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት አቶ ደመቀ ገልጸውላቸዋል።በሁለቱ አገራት መካከል በደህንነት፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በግብርና፣ በኢነርጂ፣ በጤና እና በስነ-ምድር ምርምር ዘርፎች ያላቸውን ትብብር በተመለከተ ምክክር አድርገዋል።
አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሩስያ ጉብኝት እንዲያደርጉ የሩስያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ የላኩትን ግብዣ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ኢፕድ እንደዘገበው
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






