Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በትግራይ ህዝብን ማእከል ያደረገ የተረጋጋ ህዝባዊ ሰላምና አስተዳደርን ለማረጋገጥ የቀረበ ጥሪ – አብርሃም በላይ
News

በትግራይ ህዝብን ማእከል ያደረገ የተረጋጋ ህዝባዊ ሰላምና አስተዳደርን ለማረጋገጥ የቀረበ ጥሪ – አብርሃም በላይ

Ethioreview newsEthioreview news—May 11, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይን ወቅታዊ ችግር በሁሉም መስክ በዘለቄታ ለመፍታት በሚያግዙ ገንቢና ሰላማዊ እንዲሁም ህጋዊ የአሰራርና የመፍትሔ አማራጮች ካላቸው አካላት ጋር በቅርበት ለመስራት ሙሉ በሙሉ ዝግጅት ያለው መሆኑን ስገልፅ በዚህ የታሪክ ሀላፊነት ወቅት ዜጎች የበኩላቸውን ለማድረግ እንዲረባረቡ የአደራ መልእክቴን በማስተላለፍ ጭምር ነው።

በትግራይ ህዝብን ማእከል ያደረገ የተረጋጋ ህዝባዊ ሰላምና አስተዳደርን ለማረጋገጥ የቀረበ ጥሪ በማስቀደም በአገራችን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ጀምሮ በተከሰተው ግጭት መነሻነት በተፈጠሩት መጠነ ሰፊ ጉዳቶች በወገኖች ላይ የደረሰው የሞት፣ የአካል ጉዳተኝነት ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ፣ መፈናቀሎች ፣ ጥልቅ የስነ ልቡና ጉዳቶች ፣ የንብረት ዘረፋ መጥፋትና ውድመት፣ አላስፈላጊ መገፋፋትና የተካረሩ አመለካከቶች በአጠቃላይም ውጥረት በህዝቦች ዘላቂ ትበብርና በሰላምና መረጋጋት የመኖር ፍላጎት ላይ የጋረጠውን ጉልህ አደጋ በተመለከተ በግልፅ በመተማመን ተገቢውን ፍትህ መስጠት ይፈልጋል።

የሚደርሰው ጉዳትና ቁስልን በመቀነስና በመሻር እንዲሁም መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በተግባር በመቀየር በይቅርታ መንፈስና የቁርጠኛ የሰላም ወዳድነት ማረጋገጫ እርምጃዎችን በመውሰድ አገሬንና ህዝቦችዋን እንዳገለግል በተሰጠኝ በዚህ ትልቅ ሀላፊነት ተመድቤ ስራዬን ስጀምር በክልሉ ህዝብ ፣ በፌደራል መንግስት፣ በመላው የአገራችን ህዝቦች ፣ በዲያስፖራ ኮሚዮኒቲው እና በአለም አቀፋ ማህበረሰብም ጭምር ለዚህ ወሳኝ ተልእኮዬ ስኬት ሙሉ ድጋፍና እገዛ እንደማገኝ ከወዲሁ በሙሉ ልብ በመተማመን ነው።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ በተለይም ችግሮችን ነቅሶ በማውጣትና መፍትሔን በመፈለግ ሒደት የችግሮችን ስሪተ ነገር የመረዳት ፣የተያያዥ መሰረታዊ ጉዳዮችን ተፅእኖ መለየትና ከሙሉ ስእል እይታ ያልጎደሉ ደረጃ በደረጃ የሚተገበሩ የመፍትሔ ሀሳቦችን ማፍለቅና በህዝባዊ ይሁንታ በርብርብና በድፍረት በተግባር የመፈፀም ቁርጠኝነትን የሚጠይቁ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።

ባለፋት ወራቶች በትግራይ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ለመቀየር በተሰሩ በርካታ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ጉልህ ተግዳሮቶች የመኖራቸው እውነታ ለፖለቲካ ትክክለኝነት የማይመቹ ከመሆናቸውም በላይ ቅድሚያ ለሚሰጠው የሰው ልጆች ህይወት ማዳን ሰብአዊ ቀውስ እንዳይባባስ
የመስራት አንገብጋቢ ጉዳይና በአካባቢው የተሻለ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋትን የማረጋገጥ ስራውን ፈታኝ በማድረግ ለተጨማሪ የከፋ ጉዳት የሚዳርጉ ጉልህ ችግሮች መሆናቸውን መገንዘብም አስፈላጊ ነገር ነው።

በህግ ማስከበር ዘመቻ ምእራፍና አንዳንድ ግጭትና ጥቃቶች በንፁሀን ዜጎችና በግፊትና በቆሞ ሞት እምቢተኝነት በርካታ ወጣቶች ሴቶች እድሚያቸው ያልደረሱ ታዳጊዎች ጭምር የሞት የአካል ጉዳት አደጋና የንብረት ውድመትም ጭምር የተጋለጡበትን ሁኔታ መቀየር አስፈላጊና አንገብጋቢ ወቅቱ የሚጠይቀው የአመራር እርምጃ ነው።

እዚህ ላይ በፌደራል መንግስት በህግ የማስከበር ምእራፋ የተወሰዱት ጉልህ እርምጃዎች የመንግስትን ህጋዊ ሀላፊነትና ግዴታዎች ለመወጣት የተፈፀሙና በሰላምና ፀጥታ ሀይላት የተሰሩ ስራዎችም በአገር አንድነት እና ሰላም ላይ የተቃጡ አደጋዎችን ለመቀልበስ አስፈላጊነታቸው ታምኖባቸው የተፈፀሙ
ግዳጆች ናቸው ። በዚህም ምክንያት በክልሉ በአሁኑ ወቅት የተገኘውን አንፃራዊ መረጋጋት በማረጋገጥ ረገድ የውድ ህይወት የመስዋእትነት ዋጋ ጭምር የተከፈለባቸው እና አየተከፈለባቸው የተረጋገገጡ መሆናቸውን በክልሉ ያለውን ጉዳይ ለመከታተል በተሰጡኝ ልዮ ተልእኮዎች ውስጥ ያረጋገጥኩት መሆኑን ግልፅ ለማድረግ እወዳለሁኝ።

ነገር ግን በግጭቶችና ጥቃቶች በእነዚህ የስድስት ወራት ጊዚያቶች በትግራይ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ዜጎች በታጠቂ ሀይሎች የተፈፀሙ ናቸው በተባሉ እርምጃዎች የበርካታ ንፁሀኖች ደም ፈስሰዋል ፣ዜጎች ለአካል ጉዳተኝነት ተዳርገዋል ፣ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል፣ ሴቶችና ህፃናት ተደፍረዋል በቢሊዮን ብሮች የወጣባቸው የግልና የመንግስት የልማት ተቋማት ንብረቶች መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ የጤናና የትምህርት ተቋማትም ጭምር ወድመዋል ተዘርፈዋል ፣ተግዘው ተወስደዋል፣ የአርሶ አደሮች በሬ በጎች ፍየሎች እና የድሆች የእለት ምግብና የቤት መገልገያ ጥቃቅን ንብረቶችን ሳይቀር ጠፍተዋል ተዘርፈዋል።

በትግራይ የተከሰተውን ግጭት በማስቆም ሰብአዊ ቀውሰን የመግታት ጉዳይ ቀደም ሲል እንዳስቀመጥቁት የችግሮችን ስሪተ ነገርን መረዳትንና ሚዛናዊ አቋም መያዝን የሚጠይቅ፣ የችግሮቾን ተያያዥነትና ተፅእኖዎችን በጥንቃቄ መለየትን የሚሻ፣ እንዲሁም የመፍትሔ አሰጣጥንም በተመለከተ የሙሉ ስእል እይታን ግንዛቤ ውስጥ

በተለይ በእኔ እምነት በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊነቶች ላይ እያለሁ ይህ እጅግ አሳዛኝ ጥፋት በህዝብ ላይ ሲደርስ ቀዳሚ የሚሆነው ጉዳቱን በሚቀንሱና ሌላ ተጨማሪ አደጋ በህዝቡ ላይ እንዳይደርስ በሚከላከሉ ህይወት አድን ስራዎች በፍጥነት በመሳተፍ መስራት ፣በአገር ደህንነት ላይ የተጋረጠውን ጉልህ አደጋ መቀልበስና አገሪቱን በአጠቃላይ ወደ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ በሚጠቅሙ ተግባራት ላይ ማተኮር በዚህም በርካቶችን ከተጨማሪ ሞት እና የእጅግ የከፋ ጉዳት ለማዳን አቅም የተቻለውን
ሁሉ ማድረግ መሆኑን ብገነዘብም ፤ ባለፋት ስድስት ወራት በነበሩ እጅግ ፈታኝና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሹ ሁኔታዎች በግሌ ለትግራይ ህዝብና ለመላው ያገራችን ህዝቦች በነበረኝ አገልግሎት ውስጥ በማናቸውም መልኩ ውሱንነቶች መኖራቸውን ባለመካድ መቆሜንና ህዝቡ ለዘላቂ ሰላሙ እና መረጋጋቱ አሁንም ቅድሚያ በመስጠት ከፊታችን ያለውን ወሳኝ የህይወት አድን ስራ ፣ ሰላም ግንባታና መልሶ ማቋቋም ተልእኮ በስኬታማነት እንድወጣ እንዲያግዘኝ በትህትና እማፀናለሁ።

በትግራይ የተከሰተውን ግጭት በማስቆም ሰብአዊ ቀውሰን የመግታት ጉዳይ ቀደም ሲል እንዳስቀመጥቁት የችግሮችን ስሪተ ነገርን መረዳትንና ሚዛናዊ አቋም መያዝን የሚጠይቅ፣ የችግሮቾን ተያያዥነትና ተፅእኖዎችን በጥንቃቄ መለየትን የሚሻ፣ እንዲሁም የመፍትሔ አሰጣጥንም በተመለከተ የሙሉ ስእል እይታን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ፣ ለህይወት ማዳን ሰላምና መረጋጋት ቀዳሚ አጀንዳነት የተለየ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን በሚገባ መረዳት ለዘላቂ መፍትሔ አሰጣጥ ውጤታማ አቀራረብ ሲሆን በዚህ ውስጥም የህዝብ ፍላጎትና ምልአተ ተሳትፎም አስኳል ጉዳይ መሆኑን መገንዘብን የሚጠይቅ ነው።

በአሁኑ ሰአት በትግራይ ክልል ቀደም ሲል በተከሰቱ ችግሮችና በየቦታዉ በሚያጋጥሙ ልዮ ልዮ ጥቃቶች ለዜጎች አስፈላጊውን መሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እና አስተማማኝ ፀጥታና ሰላምን ለማረጋገጥ በህዝብ ተሳትፎ ላይ የተለየ ስራ መስራትን የሚጠይቅ ሁኔታ መኖሩን መረዳት የሚያስፈልግ ነው። በዚህ ረገድ በመንግስት በኩል የህዝቡን ፍላጎት የእለት ተእለት ችግሩንና ሁነኛ ስጋቱንም ጭምር በሚገባ በማድመጥ ሳይውል ሳያድር ለመፍታትና በሒደትም ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት መሰረት የሚጥሉ አፋጣኝ ስራዎችን መስራት ላይ ትኩረት ማድረጉን በመልካም እድገትነት ሊሚወሰድ የሚገባ መሆኑን ሰላም ወዳድ ሀይሎችና በተለይም የሰላሙ ባለቤትና ዋና የሆነው የትግራይ ህዝብ በአስተውሎት እንዲገነዘቡት ያስፈልጋል።

በሌላው በኩል በግጭቶችና የፀጥታ መደፍረስ ጊዜ እነዚህ ጉዳቶች ተጠባቂ ናቸው የሚሉ የአጠቃላይ ድምዳሜዎች አዝማሚያና በወገኖች ላይ ለደረሱ አሳዛኝ ጉዳቶች የተለየ እና አስቸኳይ ትኩረት እንዳልተሰጠ የሚያስመሰሉ ክፍተቶች በፌደራል መንግስትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ በተጨባጭ የተሰሩ
ስራዎችን መና ለማድረግ ለሚሰሩ የውስጥና የውጭ የቅርብና የሩቅ ሴረኞች ምኞት ተጋላጭም የሚያደርጉ በመሆናቸው መለየትና መታረምም ይገባቸዋል።

በትግራይ በተከሰተው ችግር ላይ በግልፅ ወጥቶ ለመናገር እና ሁኔታውን በሚቀይር ስራ በመሳተፍ የመፍትሔው አካል የመሆን ጉዳይ የፖለቲካና የዘር ወገንተኝነትን አይጠይቅም። በመሆኑም ዜጎች በሁሉም ቦታ ለወገኖቻቸው እንዲደርሱ ከጥላቻ ንግግር ሰላባነት ወገኖቻቸውን በስራና በማህበራዊ
አካባቢዎቻቸው በሙሉ እንዲጠብቁ በግልና በቡድን ጭምር ርህራሔና አቃፊነትን በመላበስ ለዜጎቻቸው የሰላም ወዳጅነታቸውን በተግባር እንዲያሳዩ ልዝበት እንዲፈጠር አበክረው እንዲሰሩ በመደበኛና በሶሻል ሚዲያ ከሚቀነቀኑ ተንኳሽ ንግግሮችና በቅርብ የተለመዱ መጠሪያዎችን ከመጠቀም እንዲቆጥቡ ከዚህ የጠብ ገበያ ለማትረፍ ያሰፈሰፋ ሀይላትንም እንዲያሳፍሩ በአጠቃላይ ክልሉን ወደ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሰብአዊ ጥሪዬንም አቀርባለሁ ።

መላው ያገራችን ህዝቦች!

ሰላም የጀግኖች አጀንዳ ነው ! ብዙ መታገስን ፣ አስፈቶ ማሰብን ፣ ብዙ አይቻልሞችን መድፈርን ፣ ነገን ማየትንና በትላንት እውነታዎች ላይ ግልፅ መሆንንና መጨከንን የሚጠይቅ! ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወንድማማች ህዝቦች መካከል ውጥረትን ለመፍጠር ለአመታት የተሰሩ ስራዎችና በቸልተኝነትና በእልህ በተተው ጉዳዮች የሰውን ህይወት ማጥፋትና ከኖረበት ቀዬው ማፈናቀል የመሳሰሉ መራራ የጥላቻ ፍሬዎችን እየተመለከትን ቢሆንም ለአመታት ከተገነባው የአብሮነት እና የመተሳሰብ መልካም ዘመናት የጉዞ ታሪካችን ጋር የማይወዳደር በመሆኑ እንደ ህዝቦች ወደ ማስተዋል እና ስክነት ለመመለስ ሳንውል ሳናድር መስራት በመጀመር ለትውልዶች የምንሰንቀውን ስንቅ ከቂም ከጥላቻና ከበቀል ይልቅ መተማመን ፣ ይቅር መባባል ፣ መደጋገፍንና አብሮነትን ለማጎልበት የሚበጁ መሆናቸውን የማረጋገጥ የትውልድ ሀላፊነት አለብን።

በዚህ አጋጣሚ በትግራይ ፀጥታና ሰላምን በማስፈን ፣ ፍትህን በማረጋገጥና ዘላቂ ሰላምን በማምጣት፣ ሰብአዊ እገዛ በማድረግና መልሶ ግንባታ ሒደት መላው የአገራችን ህዝቦች በተለይም የአጎራባች ክልሎችና የኤርትራ ህዝቦች፣ የፌደራል መንግስት ፣ የዲያስፖራ ኮሚዩኒቲ አባላት ፣ ምሁራን ፣ ባለሀብቶች ፣ የኮሚዮኒቲ ማእከሎች ፣ የሙያ ማህበራት ፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎች፣ ተፅእኖ ፈጣሪ ተቋማትና ግለሰቦች ፣ የሚዲያ አካላት ማህበረሰብ አንቂዎች ፣ የሐይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ የወጣት እና ሴቶች አደረጃጀቶች ፣ በግል አና በመንግስት ስራ የምትተዳደሩ ዜጎች ለዚህ አንገብጋቢ ተልእኮ ልባችሁን ግዜአችሁን ድጋፋችሁን እና አቅማችሁ የሚፈቅደውን ሁሉ በማድረግ እንድትሳተፋ የአደራ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

በመጨረሻም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይን ወቅታዊ ችግር በሁሉም መስክ በዘለቄታ ለመፍታት በሚያግዙ ገንቢና ሰላማዊ እንዲሁም ህጋዊ የአሰራርና የመፍትሔ አማራጮች ካላቸው አካላት ጋር በቅርበት ለመስራት ሙሉ በሙሉ ዝግጅት ያለው መሆኑን ስገልፅ በዚህ የታሪክ ሀላፊነት ወቅት ዜጎች የበኩላቸውን ለማድረግ እንዲረባረቡ የአደራ መልእክቴን በማስተላለፍ ጭምር ነው።

አብርሃም በላይ በርሀ
የትግራይ ብሔራዊ ክልል መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር
ዋና ስራ አስፈፃሚ ግንቦት 3/2013


  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ቀና ልቦና ከበቂ ጥበብ ጋር ስኬታማ ያደርጋልና ጉዟችን በቀና ልቦና እንደተሞላ ይቀጥላል
ኢትዮጵያ “አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካውያን” የሚል የጸና አምነቷን አጸናች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2