የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን በተደጋጋሚ ” አሸባሪ ቡድን” እያሉ የጠሩት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አስራ አራት ደቂቃ በፈጀው ንግግራቸውን ሲቋጩ የኢትዮጵያን ታሪክ በመረዳትና በማክበር ” ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቼ ” አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በስም ጠርተው ” አብረንዎት ነን” የሚል ማረጋገጫ ሰጡ። የተዘጋጀው የቪዛ ማእቀብ የሚፈይደው አንዳችም በጎ ነገር እንደሌለ አመልክተው ይልቁንም መርዳት እንደሚሻል፣ አብይ አህመድም ሰላሟ የተተበቀ አንድ አገር እየገነቡ እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ አመለከቱ።
” የማይገባ፣ እጅግ ስህተት የሆነ፣” ሲሉ የገለጹትን የአሜሪካ አቋም ” በፍጹም ተቀባይነት የሌለው” በማለት አራክሰው እንደማይቀበሉት ይፋ ካደረጉ በሁዋላ ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከጎንዎት ነን” ሲሉ በአደባባይ መናገራቸው ይህን ኢትዮጵያን ለሚወዱ ሁሉ ብስራት ሆኗል።
በንግግራቸው ከኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም ጀመሮ የነበረውን አስተዳደር የቃኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ” የተማሩና ብልህ መሪ” ሲሉ አድነቀዋቸዋል። አያይዘውም ” በአፍሪካ እንደ እሳቸው ያለ መሪ አላየሁም” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ “የሽብር ቡድን” ሲሉ የጠሩት ትህነግ በርካታ ክፉ ተግባራትን ሲያከናውንና መንግስትን ሲያውክ መኖሩን አውስተው፣ በመቸረሻም ራሱን አግልሎ በኮቪድ ምክንያት ምርጫ ሲራዘም በማፈንገጥ የራሱን ምርጫ ያከናወነና ማዕከላዊ መንግስትን የማይታዘዝ ቡድን እንደነበር ጠቁመዋል።
ሴናተሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የበለጸገች፣ አንድነቷን የጠበቀች፣ ሰላማዊ አገር ለመገንባት እየሰሩ መሆኑንን አመልክተው፣ ወደ ስልጣን ሲመጡ ቃል የገቡትን በመፈጸማቸው ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል። እስረኞች ፈተዋል። ጋዜተኞችን ለቀዋል። የፖለቲካ ምህዳሩን አስፍተዋል ሲሉ በሽግግር ጊዜ ውስጥ ተሰሩ ያሉዋቸውን ዘርዝረዋል።
“አሸባሪው ህወሓት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደስተኛ አልነበረም፤ ከመንግስትም ጋር አብሮ ለመስራት እንቢተኛ ሆነ፤ ተቃውሞውንም አገሪቷን በማወክ መግለጽ ጀምሮ ነበር፤ በዚህ የህወሓት ሽብር የተሞላበት አካሄድ የተነሳ የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፤ ይህንን አሸባሪ ድርጅት የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እኩል ማየት መጀመሩ ስህተት ነው፣ ተቀባይነት የለውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ጥረት እያደረጉ ነው” ሲሉ የተደመጡት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አብይ አህመድ አምላካቸውን የሚፈሩ መሆናቸውንም አክለዋል።
ትሀንግ ካፈነገጠ በሁዋላ ሚሊሻ አደረአጅቶ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ማጥቃቱንና መሳሪያ መዝረፉን ያስታወሱት ታዋቂው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል እና የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማእቀብ ከቶውንም ፍትሃዊ ሊባል እንደማይችል አስምረውበታል። ሲቀጥሉም ኢትዮጵያ የብሄራዊ መከላከያ ሃይሏ ከተጠቃ በሁዋላ ምላሽ መስጠቷን ” እውነታው ይህ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






