የሃሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ተራ ተግባር መሆኑን ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፤
ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ንግግር በማስመሰል ተፈብርኮ የተለቀቀውን ድምጽ አስመልክቶ ፓርቲው ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ እንዳሉት፣ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሃሰትና የፓርቲው ፕሬዝዳንት በተለያየ መድረክ ላይ ከተናሩት ንግግሮች ተቆራርጦ የተፈበረከ ነው፡፡
አለማውም ህዝቡን ማደናገርና ህዝብና መንግስት መካከል ያለመተማመን እንዲፈጠር ብሎም ውጥረትና ያለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ቢቂላ፣ ተግባሩንም ተቀባይነት የሌለው ሃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የሚሰራጭ የወረደ ተግባር ነው ብለውታል፡፡
በዚህ ተግባርና ከጀርባ ያለው ድብቅ አጀንዳ ላይ የኢትዮጵያን እድገት የማይፈልጉ የውስጥ እና የውጭ አካላት እጅ እንደሚኖር ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
መሰል የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ባለፉት ቅርብ አመታት እየተለመደ መጥተዋል ያሉት ሃላፊው ህዝቡ መሰረት ከሌላቸውና ምንጫቸው ካልታወቀ መረጃ እንዲጠበቅና መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመርጥ አሳስበዋል፡፡
ebc
[jetpack_subscription_form show_subscribers_total=”false” button_on_newline=”false” custom_font_size=”16px” custom_border_radius=”0″ custom_border_weight=”1″ custom_padding=”15″ custom_spacing=”10″ submit_button_classes=”has-background has-luminous-vivid-amber-background-color” email_field_classes=”” show_only_email_and_button=”true”]
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር።… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው





