Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ኢትዮጵያ ግዢ እንዳትፈጽም ተቆለፈባት፤ “ከዚያስ” እያለች ነው!
News

ኢትዮጵያ ግዢ እንዳትፈጽም ተቆለፈባት፤ “ከዚያስ” እያለች ነው!

Ethioreview newsEthioreview news—June 30, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደበት የሚወጡት ቃላቶች ቀስ በቀስ ትንፋሼን አሳጠሩብኝ። በርካታ ንግግሮችን ሰምቻለሁ። አሳዛኝ መግለጫዎችን ተከታትያለሁ። በዘመኔ ግን እንደ አሁኑ ልቤን ያራደ፣ ሰውነቴን ያንዘፈዘፈና የማደርገውን ያሳጣኝ መድረክ ገጥሞኝ አያውቅም። ያለ ምንም ማጋነን ለሚሰማ ሁሉ፣ ለሚያስተውል ዜጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚገባ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በራስዋ ገንዘብ መገበያየት እንዳትችል አሜሪካና ጀርመን ያሉት አካውንቶቿ መዘጋቱን ሲናገሩ ብጮኽ አልኩ። ኢትዮጵያ ይህ ሁሉ የሚደርስባት ለምን ይሆን?” ከተሳታፊዎቹ አንዱ በስልክ የገለጸው።

“አንድ ቦታ ላይ ህዝቡ መከላከያ ገብቶ ይጠብቀን ብሎ ጥሪ አቅርቦ መከላከያ በቦታው ከገባ በኋላ ሁኔታውን ለማስተካከል የተወሰኑ ወታደሮችን በቦታው አስቀምጦ ወደሌላ ስፍራ ለዘመቻ ሄደ፡፡ ነገር ግን ማታ ላይ በቦታው የቀረውን ወታደር ይጠብቀን ብሎ የጠራው ህዝብ መሳሪያም ገጀራም ይዞ ወጥቶ ጨፍጭፎታል”

“የአገር መከላከያ ሰራዊት እየተጠቃ ያለው በህዝብ ነው።ራሳችን በምንቀልበው ህዝብ የምንጠቃ ከሆነ በእልህ አንዴ ገብተንበታል በሚል በዚያ መቆየት ፋይዳ የለውም!ጦሩ በህዝብ ነው እየተገደለ ያለው፡፡ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ጦሩ እንዲቆይ ካደረገን ጦሩ ወዳልተፈለገ እርምጃ ሊገባ ይችላል!”

“መጀመሪያ የገጠመን የተደራጀ፣ የታጠቀ እና ዩኒፎርም የለበሰ ሀይል ነበር፡፡እሱን በሁለት ሶስት ሳምንታት ውስጥ አስወግደናል፡፡ከዚያም የተወሰነ የጎሬላ ውጊያ ነበር፡፡አሁን ግን በየመንደሩ ስንሄድ የሚገጥመን ጦር የለም፡፡የምናገኘው ህዝብ ነው፡፡በቃ ሰላም ነው ብለን ስናልፍ ግን ከጀርባችን ህዝብ ነው ባልነው አካል እንጠቃለን!”

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ትናንት አመሻሹን ከጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተው ነበር፡፡ሚዲያው በምርጫው ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለማመስገን በተዘጋጀው በዚህ መርሀ ግብር ላይ እግረ መንገዳቸውን ወቅቱን ሊያስረዳ የሚችል መረጃ ሰጥተዋል።ካነሷቸው ነጥቦች መካከልም የተወሰኑትን በግርድፍ ኤቢ ቤላ ያቀረበው ሙሉ በሙሉ ከታች ሰፍሯል።

– “በምርጫው እኛም ሆነ ተቃዋሚዎች የተመኘነውን ያህል ቡራቡሬ ፓርላማ አላገኘንም!”

– ” ተቃዋሚዎች በምርጫው ውጤት ደስተኛ ባይሆኑም በምርጫ ቦርድ ፥ በፍርድ ቤት እና በሚዲያ ላይ ቅሬታ እንደሌላቸው ተስማምተናል!”

– “ሚዲያው የትርክት ለውጥ ላይ በደንብ መስራት አለበት፡፡ኢትዮጵያዊ አንድነትን ከዚህም በላይ መሰበክ አለበት!”

– “በትግራይ ባካሄድነው ዘመቻ ተይዘውብን የነበሩትን መሳሪያዎች በሙሉ አስመልሰናል፡፡ማስተካከል የምንፈልገውንም አስተካክለናል”

-“መቀሌ ከዘመቻው በፊት የነበራትን የስበት ማእከልነት አጥታለች፡፡ስለዚህ ከመቀሌ መውጣት ከሌሎች ቦታዎች ከመውጣት የተለየ ፋይዳ የለውም!”

-” ከዘመቻው በፊት ጁንታው የነበረው ወታደራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ አቅም አሁን የለም፡፡ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል እና በሌሎች ክልሎች መሀከል የነበረው ልዩነት ሰፊ ነበር፡፡አሁን ግን እኩል ሆኗል ወይም ከዚያ በታች ወርዷል!”

– “በዚህ ጦርነት ወደ 100 ቢሊየን ብር ገደማ አውጥተናል፡፡ይህም ለትግራይ ከምንመድበው አመታዊ በጀት ከ13 እጥፍ በላይ ነው፡፡ከአሁን በኋላ ግን በዚህ ደረጃ እያወጣን ለመቀጠል ፍላጎት የለንም!”

– “ጦሩ እየተጠቃ ያለው በህዝብ ነው፡፡ራሳችን በምንቀልበው ህዝብ የምንጠቃ ከሆነ በእልህ አንዴ ገብተንበታል በሚል በዚያ መቆየት ፋይዳ የለውም!”

– “ጦሩ በህዝብ ነው እየተገደለ ያለው፡፡ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ጦሩ እንዲቆይ ካደረገን ጦሩ ወዳልተፈለገ እርምጃ ሊገባ ይችላል!”

– “መጀመሪያ የገጠመን የተደራጀ ፥ የታጠቀ እና ዩኒፎርም የለበሰ ሀይል ነበር፡፡እሱን በሁለት ሶስት ሳምንታት ውስጥ አስወግደናል፡፡ከዚያም የተወሰነ የጎሬላ ውጊያ ነበር፡፡አሁን ግን በየመንደሩ ስንሄድ የሚገጥመን ጦር የለም፡፡የምናገኘው ህዝብ ነው፡፡በቃ ሰላም ነው ብለን ስናልፍ ግን ከጀርባችን ህዝብ ነው ባልነው አካል እንጠቃለን!”

– “የትግራይ ህዝብ የጽሞና ጊዜ እንዲኖረው እና ነገሮችን በትክክል እንዲያገናዝብ እድል ሰጥተነዋል!”

– “አሁን ትኩረታችን ትግራይ ሳትሆን የህዳሴው ግድብ ነው፡፡ስለዚህ ጦሩ ትኩረቱ ወደዚያ ነው!”

– “እኛ ትግራይን ተቆጣጥሮ እንደ ቅኝ ገዢ የመቆየት አላማም አልነበረንም፡፡የሚስተካከለውን አስተካክሎ ወደ ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች መመለስ ነበር አጀንዳችን!”

– “የጁንታው አላማ ማሸነፍ ፥ ስልጣን መያዝ ፥ ወዘተ አይደለም፡፡እኔ አመድ ስለሆንኩ ኑ አብራችሁኝ አመድ ሁኑ ነው፡፡እኛ በተቀደደልን ቦይ አንፈስም፡፡ነገሮችን ቆም ብሎ አይቶ የራስን አካሄድ መምረጥ አስፈላጊ ነው፡፡ስለዚህ ቆም ብለን አይተን ነው የወሰንነው!”

-“በሳውዲ የነበሩ 45ሺ ኢትዮጵያውያንን የማንገላታቱ እንቅስቃሴ ክህዳሴ ግድቡ ጋር የተያያዘ ጫና የማድረግ ሂደት ነው!!

– “አማራ ክልል ከሁለት አመት በፊት ያለበት ስጋት የለበትም፡፡ተክዷል የሚሉ ሀይሎች ህዝቡን እየናቁ ነው፡፡የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም ዛሬ ለ30 አመታት ዱላ እየወረደበት እንኳን ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ነው ዝቅ ሲል የበጌ ምድር ሰው ነው”

– “ጦሩ ከዚያ እንዲወጣ ከወሰንን በኋላ ትናንት እስከ እኩለ ሌሊት ብዙ የአለም መሪዎች ስልክ እየደወሉ ጦሩን ማውጣታችንን ሲቃወሙ ነበር!”

-“ጦራችን ተሸንፎ አይደለም የወጣው ነገር ግን ባለበት ቦታ ባእድ እንዲሆን ከተደረገ ደጀን ወደሚለው አካባቢ መሄዱ አግባብ ነው!”

– “አሁንም ቢሆን ጦራችን መያዝ የሚገባው ቦታም ሆነ ሌላ ነገር ካለ ለመያዝ ከበቂ በላይ አቅም አለው!”

– “እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ መቀሌ የገባ አንድም የጁንታው ወታደር የለም!”

– “አንጻንድ ነገሮችን መግዛት ፈልገን በገዛ ገንዘባችን እንዳንገዛ በአሜሪካ እና በጀርመን ያለን አካውንትን ዘግተውብናል!”

– “ባለፉት ወራት ወጣቱ መከላከያን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበን ያገኘነው ሰው ብዛት ግን 5 ሺ ብቻ ነው!”

– “የዚህ ጦሩን የማውጣት እርምጃን ውጤት በጥቂት ጊዜ ውስጥ እናየዋለን፡፡ነገር ግን ዳግማዊ ድሉ የኢትዮጵያ እንደሆነች በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ!”

(ንግግሮቹ ቃል በቃል የተወሰዱ ሳይሆኑ በግርድፍ የጻፍኳቸው ናቸው)

በመቶዎች የሚቆጠሩ ከፌደራል እና ክልል ሚዲያዎች የተሰባሰቡ የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት በዚህ ፕሮግራም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው ሁኔታዎችን ባብራሩበት ወቅት አዳራሹ ውስጥ የነበረው ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆን የሸራተን ሆቴል የመስተንግዶ ባለሙያዎች እንኳን ስራ አቁመው በትኩረት አዳምጠዋል፡ባላጋንነው ለብዙ ደቂቃዎች አዳራሹ ውስጥ ሰው ያለ እስከማይመስል ድረስ ጸጥታ እና ሙሉ ትኩረት ነበር፡፡፡በተለይ ጦሩ ባለፉት ሳምንታት በህዝብ ደረጃ የደረሰበትን ክህደት በገለጹበት ወቅት ብዙዎች ሲናደዱ ይታይ ነበር፡፡

“አንድ ቦታ ላይ ህዝቡ መከላከያ ገብቶ ይጠብቀን ብሎ ጥሪ አቅርቦ መከላከያ በቦታው ከገባ በኋላ ሁኔታውን ለማስተካከል የተወሰኑ ወታደሮችን በቦታው አስቀምጦ ወደሌላ ስፍራ ለዘመቻ ሄደ፡፡ ነገር ግን ማታ ላይ በቦታው የቀረውን ወታደር ፥ ይጠብቀን ብሎ የጠራው ህዝብ መሳሪያም ገጀራም ይዞ ወጥቶ ጨፍጭፎታል ” ብለው ሲናገሩ በተለይ ብዙ ሰው ስሜቱ በንዴት በጣም ግሎ ነበር፡፡

በጥቅሉ ጦሩን ያወጡበት ፖለቲካዊ ፥ ዲፕሎማሲያዊ ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ምክንያት ለብዙዎች አሳማኝ ሆኗል ማለት እችላለሁ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእልህ ጦሩን መማገድ እንደማይፈልጉ እና ከዚህ ቀድም በነበሩ አገዛዞች የተሰራውን ስህተት መድገም እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል፡፡ከኢኮኖሚያዊ ፥ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካው ምክንያት ባሻገር የጦሩን የጦር ሜዳ ሰሙናዊ ቆይታ ሲያብራሩ የነበረው ሁኔታ ሳውዲ እና UAE በየመን ከነበራቸው ዘመቻ ጋር አመሳስለውታል፡፡እኔ ደግሞ Black hawk down የተሰኘው ፊልም ጥሩ ምሳሌ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

በጥቅሉ ግን ያለው ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደርግን ስህተት መድገም እንደማይፈልጉ ፥ በተዘረጋላቸው ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብለው መግባት እንደማይፈልጉ ፥ ትኩረታቸውን ወደ ሌሎች አጣዳፊ ጉዳዮች ለማድረግ እንደመረጡ የገለጹበት ሲሆን በትግራይ ጉዳይ ይህ ውሳኔያቸው ውጤታማ እንደሚሆንም እርግጠኛ ሆነዋል፡፡በንግግራቸው ውስጥ ስለ ድርድር ያነሱበት አጋጣሚ ግን አልነበረም፡፡

Viai Ab Bela ነው እናመስግናለን ይሄው ነው እውነቱ ።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“መቀሌ ለወታደራዊ ስትራቴጂነት የቀራት ነገር የለም፤ በተራዘመ ጦርነት ላለመድቀቅ የታክቲክ ለውጥ ተደርጓል” አብይ አሕመድ
በበጀት ዓመቱ ከ7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በሰነድ አልተወራረደም
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2