አቶ ደመቀ መኮንን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃላፊነታቸው በተጨማሪ ደርበው እየሰሩ ላሉበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጣፌ መታጨታቸው ተሰማ። ክልሉና በውጭ አገር ያሉ የክልሉ ተወላጆች በዜናው ደስተኛ አይደሉም።
የአብዲሌ ወንበር ላይ ከተቀመጡ ጀምሮ እጅግ በሚገርም ሁኔታ በመላው አገሪቱ ተቀባይነት ያገኙት ሙስጣፌ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት የታጩት ገዢው ፓርቲ ብልጽግና በምርጫው ካሸነፈ አዲስ በሚዋቀረው ካቢኔ የሚካተቱ እንዲሆን ታስቦ ነው።
በሚመሩት ክልል ሁሉም ብሄረሰቦች እኩል ሆነው የሚስተናገዱበትን፣ ቋንቋውን ከቻሉ በሃላፊነት የሚመደቡበትንና ልዩነት የሌለበትን አሰራር በማስፈን ሰላም ያወረዱት ሙስጣፌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሆን መታጨታቸውን አስመልክቶ የክልሉን ተወላጅ ዲያስፖራ አባላትን አናገረን ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የሜኖሶታ ነዋሪ የሆኑ የሶማሌ ተወላጅ ” ዜናውን ሰምተናል፤ ደስተኛ አይደለንም” ብለዋል። በሙስጣፌ ሹመት ሳይሆን ክልሉ ላይ የጀመሩትን ተግባር እንዲያጠናክሩ ከመመኘት አንጻር ባሉበት እንዲቀጥሉ ምኞታቸው እንደሆነም አስታውቀዋል። ክልሉ አካባቢም ተመሳሳይ እምነት እንዳለ ለማወቅ ችለናል።
በሌላ ዜና የሜኖሶታ ነዋሪ የሶማሌ ተወላጆች አሁን አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ የያዝቸውን አቋም እንዲላዘብ እየሰሩ መሆናቸው ታውቋል። ሰፊ የሶማሌና የኦሮሞ ማህበረሰብ ባለበት ሚኖሶታ የሶማሌ ድምጽና ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ በአካባቢው ያሉትን ሴናተር ማሳመናቸውም ታውቋል። ትናት ወደ ሜኖሶታ ያቀናው የክልሉ ሉዑል ቡድን ከባለስልታኑ ጋር እንዲገናኝ መመቻቸቱንም ጠቁመውናል።
ሙስጣፊ በትህነግና በትህነግ ደጋፊዎች ዘንድ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቀጥለው የሚጠሉ፣ በመላው አገሪቱ ደግሞ ተቀባይነትን ያገኙ የለውጡ ቱርፋት የሆኑ አዲስ መሪ መሆናቸው ይታወቃል።
- የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?VOE OPINION | ADDIS ABABA | July 31, 2026 – በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከሐምሌ 13… Read more: የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?
- የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁቪኦኢ ዜና | Addis Ababa | July 30, 2026 ራሱን የትግራይ የሰላም ኃይሎች ብሎ የሚጠራው ቡድን ትህነግን… Read more: የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁ
- Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water UseVOE | Addis Ababa | July 30, 2026 – Ethiopia’s Minister of Water and Energy, Habtamu Itefa,… Read more: Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water Use
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘBy VOE News ADDIS ABABA – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 የሥራ ዘመን ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ… Read more: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
- Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical EngineeringVOE NEWS | ADDIS ABABA | July 29, 2026 Egyptian politicians have repeated the same familiar refrain for… Read more: Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical Engineering






