አዲስ አበባ በሁለት ሳምንት ለመግባት የሚያግደው አንዳችም ሃይል እንደሌለ በይፋ ያስታወቀውና በቃል አቀባዩ ጌታቸው አማካይነት ትናንት ጎንደርና ወልቃይት በአሸባሪው ትህነግ እጅ መውደቁን ያወጀው ቡድን ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ትቶ ድርድር እንደሚፈልግ ማስታወቁ ተሰማ። ለዚሁ ተግባር አዲስ አበባ የገቡ አሜሪካዊ አማላጆች መኖራቸውን ታውቋል።
ቀደም ሲል ስምንት ቅደመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ የነበረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ” ድል በድል ሆኛለሁ” እያለ ባለበት ሰዓት ለምንና እንዴት ለተኩስ አቁም አስቀምጦት የነበረውን ቅድመ ሁኔታ ለማንሳት እንደወሰነ የታወቀ ነገር የለም።
” ገና ከአማራ ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለ” በሚልና የማዕከላዊ መንግስቱን ለመጣል በኦሮሞ ጽንፈኞች አማካይነት የተለያየ ሙከራ ሲያደርግ የነበረው ትህነግ አቋሙን ቀይሮ መደራደር እንደሚፈልግ ሁለት የአሜሪካ መልዕከተኞች አዲስ አበባ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ተባባሪያችን አመልክቷል።
ወልቃይትና ጎንደር እጅቻእው መግባቱን፣ አዲስ አበባ ለመግባት በሩ ክፍት መሆኑን ባስታወቁ 24 ሰዓት ሳይሞላ፣ ከአዲሱ የድርድር ሃሳብ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ” … have been consistent in our principled position on the need for dialogue to end the crisis peacefully. ትህነግ ቀውሱን በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት አቋማችንና መርሃችን እንደተጠበቀ ነው” ሲል በቲውተር ገጹ ላይ አስፍሯል። በዚህ የቲውተር መልዕክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለንግግር ዝግጁ እንዳልሆኑም አመልክቷል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ በራሱ አነሳሽነት ለቁጥር በሚገርም ደረጃ ወደ ወታደር ማሰለጠኛ ጣቢያዎች መትመሙ፣ የደጀኑ ድጋፍና ወላጆች ልጆቻቸውን መርቀው መላካቸው በሚዲያ ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ አቶ ጌታቸው የሰላምና የንግግር ሃሳብና መርህን ደጋግመው መናገራቸው፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ከተቱን የትግራይ ሕዝብን ለማጥፋት የሚደረግ ዝግጅት አድርገው መሳላቸው የዛሬ ጠዋት መነጋገሪያ ሆኗል።
መንግስት በተደጋጋሚ እንዳስታወቀውና የክልል መንግስታት በይፋ እንደተናገሩት ” ጉዳያችን ትህነግ ከሚባል አሸባሪ ጋር ነው” በማለት እየገለጹ ባለበት ሁኔታ ጌታቸው ጉዳዩን የትግራይን ሕዝብ ከማጥፋት ጋር ማገናኘቱ ” እንደተለመደው የትግራይን ህዝብ ፍርሃት ውስጥ በመጣል በሁለት አማራጭ ውስጥ ሆኖ ውጊያ እንዲመርጥ ለማድረግ ነው” የሚል አስተያየት ተሰጥቶበታል።
አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ መልዕተኞች ምን ላይ እንደደረሱ በይፋ ተባባሪያችን ባያረጋግጥም፣ ወልቃይትን ጨምሮ የድንበርና የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ቦታዎች መፍትሄ እስኪገኝ በፌደራል ስር እንዲሆኑ፣ የፌደራል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ትግራይ እንዲገቡ፣ የመብራት፣ የባንክ፣ የስልክ ወዘተ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ፣ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ልዩ ፕሮግራም እንዲነደፍ… የመሳሰሉት ጉዳዮች ተነስተዋል።
በመንግስት በኩል የተሰጠውን ዝርዝር ምላሽ መረዳት ባይቻልም፤ የተጀመረው ኢትዮጵያን በመከላከያ ሃይል ማግዘፍና ካለችበት ከበባ ባስቸኳይ እንድትወጣ የተጀመረው ንቅናቄ ለአፍታም እንደማይቆም፣ ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማንኛውም ስጋት በጥቂት ወራቶች ነጻ ማድረግ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚነቀሳቀሱ ማናቸውንም ታጣቂዎች ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ያለመ ስለመሆኑ ዘጋቢያችን መረጃ አግኝቷል።
መንግስት በይፋ ለሰላማዊ ንግግር ክፍት መሆኑ፣ ህግ የሚገልጋቸው በህግ እንደሚጠየቁ ደጋግሞ ከመናገሩ ውጭ አሁን ትህነግ ጠየቀ ስለተባለው የሰላም ነግግር በይፋ ያለው ነገር የለም።
የሰሞኑ የሕዝብ ንቅናቄና ወዶ ዘማችነት በመላው አገሪቱ እንደ ማዕበል መነሳቱ አሜሪካንን ጨምሮ በርካታ አገሮችን ማስደንገጡ እየተዘገበ ነው። የሽግግር መንግስት በሚል እነ አቶ ልደቱና ሻለቃ ዳዊት ባዘጋጁት ዕቅድ ውስጥ ስማቸው የሚነሳ ሳይቀር ራሳቸውን እያገለሉ መሆኑ ምን አልባትም ከህዝቡ ቁጣ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






