ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውና በወታደራዊ መስክ ያላቸው ውለታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና ምክትላቸው ደመቀ መኮንን ፕሬዚዳንት ፑቲንን ካናገሩ በሁዋላ ይበልጥ ማደጉ ተወስቷል። ውይይቱ ወታደራዊ ቴክኒክ ድጋፍ መስጠትን አስመልክቶ አጀንዳ አጽድቆ ውይይቱን መጀመሩን ኢቢሲ አስታውቋል።
የሁለቱን ሀገሮች ወታደራዊ ትብብር ማጠናከርን ዓላማ ያደረገው 11ኛው የኢትዮ – ሩሲያ ወታደራዊ የቴክኒክ ትብብር የጋራ ውይይት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። ውይይቱ 10ኛውን የወታደራዊ ቴክኒክ ፕሮግራም አጀንዳ በማጽደቅ መጀመሩን ተነግሯል።
በመኮንኖች ክበብ እየተካሄደ የሚገኘው ምክክር፣ የኢትዮጵያን እና የሩሲያን ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ፣ ክህሎት እና እውቀት ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ፣ ሁለቱ ሀገሮች ከ1898 ጀምሮ በዲፕሎማሲ፣ በወታደራዊ ፣ በኢኮኖሚ ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ መስክ ታሪካዊና ጠንካራ ግንኙነት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው ከመከሩ ወዲህ የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት በጣም ጥብቅ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ዘመቻ ስታደርግ ሩሲያ የውስጥ ጉዳያችን እንደሆነ አቋም ይዛ በመንቀሳቀሷ፣ ባደረግነው 6ኛው ምርጫ፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በሌሎችም ሀገራዊ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጎን ቆማ ወዳጅነቷን በማሳየቷ ሚኒስትር ዴኤታዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የዚህን ስብሰባ ውጤትንም የሁለቱን ሀገሮች የጋራ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በሩሲያ ፌዴሬሽን የወታደራዊ የቴክኒክ ትብብር ምክትል ዳይሬክተር ፑንቹክ አናቶሊ፣ የቆየ ወዳጅነት አለን፤ በወታደራዊ መስክ ብዙ የኢትዮጵያ መከላከያ አባላት በሩሲያ ስልጠና ወስደዋል፤ ይህ ስብሰባም የሁለቱን ሀገሮች የቆየ ወዳጅነት የሚያሳድግ እንደሚሆን አመልክተዋል።
የመከላከያ ኢንዱስትሪ እና ደጀን አቭዬሽንን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ እየተደረገ ያለውን ስራ በጋራ እንደሚያጎለብቱም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በኢትዮጵያ በኩል የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ አየር ሀይል እና የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በውይይቱ ተሳታፊ ሲሆኑ ፣ በሩሲያ በኩሉ ደግሞ ፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተሬከሂን ኢቭጌኒ እንዲሁም በሩሲያ መከላከያ ቴክኒካል ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች፣ ኤክስፐርቶች እና ሌሎች አባላት መሳተፋቸው ታውቋል።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች







