በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩ ጨፌው ወሰነ። ኢዜአ እንዳለው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩና ማንኛውንም አገልግሎት ሲፈልጉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) የወሰነው ዛሬ ነው።
ዛሬ በተጀመረው የጨፌው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እውቅና መስጠት የሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ፀድቋል።
አፈ ጉባኤዋ በማብራሪያቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ መሆኑን ገልጸዋል።በሰሜን ኢትዮጵያ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን የአገር ሉዓላዊነት የመድፈር ወንጀል ሰራዊቱ በከፍተኛ ጀግንነትና መስዋእትነት ጭምር መቀልበሱን ጠቅሰዋል። “በዚህም ለአገር መከላከያ ሰራዊት እውቅና መስጠት አስፈልጓል” ብለዋል።
በውሳኔ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላ ከላቸው ማንኛውም ማዕርግ በተጨማሪ ” ጅግና” የሚል የክብርና ተጋድሏቸውን የሚያደነቅ የክብር ስያሜ ይኖራቸዋል። ምክር ቤቱ ይህን ውሳኔ መወሰኑ ለሁሉም ምሳሌ እንደሚያደርገው ይገመታል።
ኦሮሚያ ክልል አሸባሪውን ሃይል “ለህልውናችን ያሰጋናል” ሲል ወደ ግዳጅ ቀጠናው ሰራዊት ማሰማራቱ ይታወሳል።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






