ዐቃቤ ሕግ በእነ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ጀነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሣኤን ጨምሮ በ74 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን በይፋ ማህበአዊ ገጹ ይፋ አድርጓል። ሰነዶችንም አያይዟል።
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተዉ ተከሳሾች የፌዴራል መንግስትን በሀይል ለመለወጥ በማሰብ በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ጥቃት ለማድረስ የሚችል የትግራይ ማእከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ በማደራጀትና በመምራት በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣በፌዴራል ፖሊስ እና በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ላይ እንዲሁም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በተጨማሪም በኤርትራ ላይ ጥቃት በማድረሳቸዉ ነዉ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በ 1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣33፣35፣38 እና የሽብርን ወንጀል ለመከላከል ለመቆጣጠር በ2012 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 3(2) የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዉ በመገኘታቸዉ የሽብር ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡
ዐቃቤ ህግ ክስን ያስረዱልኛል ያላቸዉን ከ500 በላይ የሰዉ ምስክሮችን፣ ከ5ሺህ ገፅ በላይ የሆነ የሰነድ ማስረጃዎችን እንዲሁም የቴክኒክና የቪዲዮ ማሰረጃዎችን አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ክሱ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 272829 የሽብር መዝገቡ ተከፍቶ ጉዳዩን እየተመለከተዉ ይገኛል፡፡
ሰነዶቹን እዚህ ላይ ይመልከቱ ፊስ ቡክ ገጽ
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






