ለአሸባሪው ህወሀት ቡድን በተለያየ መንገድ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 28 ግለሰቦችና ንብረቶቻቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በሶማሌ ክልል የሚገኙ የጁንታው ተላላኪዎች ለቡድኑ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለፁት የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር መሀመድ አሊ ሐሰን፥ 28 ግለሰቦች፣ አስር የሲኖትራክ መኪና እና ሌሎች ንብረቶቻቸው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ በተደረገ ከፍተኛ ክትትል መያዛቸውን ገልፀዋል።
ግለሰቦቹ በክልሉ ብጥብጥ ለማስነሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውንም ነው ረዳት ኮሚሽነሩ የገለፁት። ለዚህ ተግባር እንዲያብሩ ከዚህ ቀደም የነበረው አመራር አባላትና ደጋፊዎች የሆኑ የክልሉ ተወላጆችን በማስተባበር ሲሰሩ ቆይተዋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ።
በተለይ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ወደ ግዳጅ ማምራቱን ተከትሎ በክልሉ የሚገኙ የጁንታው ተላላኪዊች ይህንን ሀገራዊ ሀላፊነት ሌላ ቅጥያ ስም በመስጠትና በማህበራዊ ሚዲያ ለፕሮፖጋንዳነት በመጠቀም ሂደቱን ለማስተጓጎል ሲጥሩ ነበርም ብለዋል።
የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ የሀገሪቷን ሉዓላዊነት እና ህገ መንግስት ለመጠበቅ የገባውን ቃለ መሀላ ለመተግበር ዛሬም ሆነ ነገ ዝግጁ ነው ያሉት ረዳት ኮሚሽነሩ፥ ጁንታው ስርዓተ ቀብሩ እስኪፈፀም ድረስም ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በመሆኑም በእንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ እጃቸውን በማስገባት ለጁንታው ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙ ግለሰቦችና በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና ንብረቶቻቸውን በመሸሸግ እየተባበሩ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ሲሉ ረዳት ኮሚሽነሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከዚህ በኋላ በእንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ የተገኘ ግለሰብም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ረዳት ኮሚሽነሩ ማስታወቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
- የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?VOE OPINION | ADDIS ABABA | July 31, 2026 – በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ በይፋ የተጀመረውና በአሁኑ ወቅት… Read more: የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?
- የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁቪኦኢ ዜና | Addis Ababa | July 30, 2026 ራሱን የትግራይ የሰላም ኃይሎች ብሎ የሚጠራው ቡድን ትህነግን ከመቀሌ በማስወጣት ከተማዋን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን አጠቃላይ ዝግጅት ማጠናቀቁን የቡድኑ ወታደራዊ… Read more: የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁ
- Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water UseVOE | Addis Ababa | July 30, 2026 – Ethiopia’s Minister of Water and Energy, Habtamu Itefa, has argued that Egypt should compensate Ethiopia for using the… Read more: Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water Use
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘBy VOE News ADDIS ABABA – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 የሥራ ዘመን ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ (9.1 ቢሊዮን ዶላር) ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ። ገቢው ከቀደሙት ዓመታት… Read more: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
- Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical EngineeringVOE NEWS | ADDIS ABABA | July 29, 2026 Egyptian politicians have repeated the same familiar refrain for years that Ethiopia is acting unilaterally over the Grand Ethiopian… Read more: Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical Engineering






