Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በማይካድራ ከ1ሺህ 644 በላይ ሰዎች በግፍ መጨፍጨፋቸው ይፋ ሆነ፤
News

በማይካድራ ከ1ሺህ 644 በላይ ሰዎች በግፍ መጨፍጨፋቸው ይፋ ሆነ፤

Ethioreview newsEthioreview news—July 23, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዩኒቨርሲቲው በማይካድራው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ላይ ስድስት ወራት የፈጀ ጥናት ሠርቷል። የጥናቱ ዓላማ ድርጊቱን ለዓለም አቀፍ ማኀበረሰብ ማሳወቅ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተጎዱ ወገኖች እንዲካሱ ማድረግ ነው። በጥናቱ አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለዓመታት በወልቃይት ጠገዴና በጠለምት አካባቢ በአማራዎች ላይ የፈጸመው ግፍ ተዳስሷል።

በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኀላፊና መምሕር ባምላክ ይደግ (ዶ.ር) ጅምላ ጭፍጨፋው በ1968 ዓ.ም አሸባሪው የትህነግ ቡድን ያዘጋጀው ፍኖተ መርህ አካል እንደሆነ ገልጸዋል።

ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በድምጽ አልባ መሳሪያ ጅምላ ጭፍጨፋ ለሚፈጽሙ ወጣቶችና ለፖሊስ አባላት ስልጠና ተሰጥቷል፤ የባለሀብቶችን አስከሬን ለማመላለስ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበርም በጥናቱ ተረጋግጧል።

ከድምጽ አልባ መሳሪያ የሚያመልጡትን በመሳሪያ የሚገድል ቡድንም ተዘጋጅቶ ነበር። ከዚያም በማይካድራ ከተማ የሚኖሩ አማራዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ማሳሰቢያ ተሰጠ፤ መታወቂያና ሲም ካርዳቸውን በመሰብሰብም ማንነታቸውን የመለየት ሥራ ተከናወነ፤ ለቀናት በቂ ዝግጅት ከተደረገ በኋላም ጥቅም 30 እስከ ለሊቱ 9:00 ድረስ በአሰቃቂ ሁኔታ ጭፍጨፋው ተፈጽሟል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ሰነዶችን ዋቢ በማድረግ፣ የአካባቢውን ነዋሪዎች በመጠየቅና የመስክ ምልከታ በማድረግ በተሠራው ጥናት በወልቃይት ጠገዴና በጠለምት አካባቢዎች በርካታ ጅምላ መቃብሮች ተገኝተዋል። የጥናት ቡድኑ አባል ረዳት ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ እንዳሉት በርካታ ወጣቶችና ታሪክ አዋቂዎች ተገድለው በጅምላ ተቀብረዋል።

ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በማይካድራ በተፈጸመ የዘር ጭፍጨፋ ብቻ ከ 1 ሺህ 644 በላይ ሰዎች ሰለባ ሆነዋል። 1 ሺህ 563 ሰዎች በጅምላ መገደላቸው በጥናቱ ተረጋግጧል። 81 ሰዎች ደግሞ አካል ጉዳተኛ ሆነዋል። ከ50 በላይ ሕጻናትም ያለ ወላጅ ቀርተዋል። ከዚህ ውስጥ ዘጠኙ ሴቶች ናቸው።

መረጃ ከተጠናቀረ በኋላ ተጨማሪ 31 ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን የገለጹት ረዳት ፕሮፌሰር ጌታ ይህም የሟችና የተጎጂዎች ቁጥር ከዚያ በላይ እንደሚሆን ማሳያ ነው ብለዋል። የተጨፈጨፉ ሰዎች አማካይ ዕድሜም 31 ነው።

ሌላኛው የሕግ መምህርና የጥናት ቡድኑ አባል ደመወዝ ካሴ (ዶ.ር) የኢትዮጵያን የወንጀል ሕግ፣ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለማቋቋም የወጣውን ስምምነት እና የዘር ፍጅትን ለመከላከልና ለመቅጣት የወጣውን የሕግ ማዕቀፍ ዋቢ አድርገው በሰጡት ማብራሪያ መሠረት ጅምላ ጭፍጨፋው ማንነትን መሠረት ያደረገ ነው።

ድርጊቱ ፍረጃን፣ የጥፋት ዝግጅትን እና የተፈጸመውን ወንጀል መካድን ጨምሮ የተቀመጡ 11 ዓለም አቀፍ ዝርዝር መስፈርቶችንም አሟልቷልም ነው ያሉት። ድርጊቱ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ የሥነልቦና ጉዳት አድርሷል። ዘረፋ ስለተፈጸመባቸውም ማኅበራዊ ሕይወታቸው ለአደጋ ተጋልጧል።

የወንጀሉን ክብደት ያህል ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት አልሰጠውም። ፍትሕ እንዲሰፍን ለበደለኞች አልወገነም። የጉዳቱ ሰለባዎች ለከፋ ማኅበራዊ፣ ስነልቦናዊና ምጣኔ ሀብታዊ ችግር ቢጋለጡም አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ትኩረታቸውን ወደ ሌላ አዙረዋል። ይህም በመረጃ እጥረት ሳይሆን የራሳቸው አጀንዳ ስላላቸው መሆኑን ነው ምሁራኑ ያነሱት። ይህም ተገቢነት የለውም ብለዋል።

ምሁራኑ እንዳሉት ወንጀለኞችን ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባ መክረዋል። ሀገር ውስጥ የሚገኙትን መንግሥት ኀይሉን ተጠቅሞ በቁጥጥር ስር ማዋል አለበት፤ በውጪ ሀገራት ያሉትን ደግሞ ከሀገራት ጋር በመተባበርና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ለፍርድ ማቅረብ ይጠበቅበታል። በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ዘር ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋ ይርጋ ስለማያግደው ወንጀለኞቹ በማንኛውም ጊዜ ተጠያቂ ናቸው።

ተጎጂዎችን ማቋቋምና የሕክምና ድጋፍ መስጠት ይገባል ብለዋል።

የጥናቱ ግኝት የመጀመሪያው ዙር የአማርኛ ጽሑፍ እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል። መረጃው በተለያዩ ዘዴዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው ይደረጋል። ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በመተርጎምም ለዓለም አቀፍ ተቋማት፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የውጪ ሀገራት ኢምባሲዎች እንዲሁም ለልዩ ልዩ ሀገራት እንዲደርስ ይደረጋል ብለዋል። የ41 ዓመታት ችግር በአንድ ጥናት ብቻ ስለማይመለስ ሌሎች ተቋማት ተጨማሪ ጥናት እንዲያደርጉም መምህራኑ ጠይቀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።


Donate Button with Credit Cards
[jetpack_subscription_form show_subscribers_total=”false” button_on_newline=”false” custom_font_size=”16px” custom_border_radius=”0″ custom_border_weight=”1″ custom_padding=”15″ custom_spacing=”10″ submit_button_classes=”has-text-color has-accent-font-color” email_field_classes=”” show_only_email_and_button=”true”]
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም።… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ባይበላስ ቢቀር… ከገዳይ ጋር በፍቅር መውደቅ
አሜሪካ – ኢትዮጵያን እየወጋች ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2