Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ትህነግን ኢትዮጵያ ግን ምን አድርጋው ይሆን 50 ዓመት የሚያደማት? ” ምን አድርጉ ነው የሚሉን?”
News

ትህነግን ኢትዮጵያ ግን ምን አድርጋው ይሆን 50 ዓመት የሚያደማት? ” ምን አድርጉ ነው የሚሉን?”

Ethioreview newsEthioreview news—August 9, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አሸብር ሲሳይ ሃምሳ ሶስት ዓመቱ ነው። ስለ ትህነግ ሲነሳ ያመዋል። ጫካ በነበሩበት ወቅት ጊንጪ ተወልዶ ያደገውን ወንድሙን አጥቷል። ሁለት የአጎቱ ልጆች እንደወጡ የትግራይ አፈር በልቷቸዋል። እሱ ብሄራዊ ውትድርና ፍርሃቻ እርሻል ልማት ውስጥ የቀን ሰራተኛ ሆኖ የመከራ ህይወት አሳልፏል። በአካባቢው፣ በሰፈሩና ባደገበት ገጠር በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን መክሰራቸውን ያስታወሳል። ስልጣንም ከያዙ በሁዋላ ቤተሰቦቹን በኢንቨስትመንት ስም አፈናቅለውበታል። እዚህ ግባ የማይባል ሳንቲም ሰጥተው ቅርስ አለባ አድርገውበታል። ኦሮምኛ በመናገራቸው ብቻ መከራ የቀመሱ፣ አካላቸው የጎደለና የሞቱ ወገኖች አሉት።” እነዚህ ሰዎች ምን አድርግ ነው የሚሉን? ለምን ከላያችን ላይ አይወርዱም?” ሲል የምሬት አስተያየቱን ይሰጣል።

አልማዝ ሃይሉም በተመሳሳይ በመገረም ነው የምትናገረው። ” ምን እንደሚፈልጉ አይገባኝም?” ትላለች። ጤነኛ ስለመሆናቸው እንደምትጠራጠር ገልጻ ” በሃስብ የማያምኑ፣ ለክርክራ የማይመቹ፣ እንደ ፋብሪካ ምርት አንድ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው፣ በሌላው ሰው ጫማ ሆነው ፣አሰብ የማይፍለጉ፣ አማክንዮ የማያውቁ ” ስትል በትምህርት ቤት ያጋተሟትን የትህነግ ደጋፊዎች ተገልጻቸዋለች። ” እኛ በዩኒቨርስቲ ደረጃ መግባባት ካልቻልን፣ በዚህ ዘመን የሰለጠነ ሃሳብ ማራመድ ካልቻልን ትርፉ ድካም ነው። የሚሰማውም አሳዛኝና ተስፋ አስቆራጭ ነገር ብቻ ነው። የሚያሳዝኑኝ ህጻናቱ፣ አዛውንቱና ደካሞች ናቸው” ትላለች።

ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የትግራይ ልጅ ” እኔ የማስበው ተጠልቻለሁ ብዬ ነው። ይህ ስሜት እንዴት እንዳደገበት አያውቀውም። ግን በምንም መልኩ ከውስጡ የሚወጣ አይመስለውም። አሁን ያለው ትውልድ ተነጋገሮ የሆነ ነገር ይፈይዳል ብሎ አያምንም። አሁን ላይ ምን መፍትሄ እንደሚኖር ጭላንጭል ማየት አልቻልኩም” ያላል። አያይዞም ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በሚሰማውና በሚያየው ሁሉ እንደሚያዝን፣ ከዚህ የባሰ ሊመጣ እንደሚችል ይሰማዋል። ከምንም በላይ ግን በትግራይ ሰዎችና በሌላው ህዝብ መካከል እየተገነባ ያለው የጥላቻ ግንብ አስጊ መሆኑን ይናገራል። ስለ ጥላቻው መነሻ ግን ብዙ መናገር አይፈልግም።

እነዚህን አስተያየቶች ያሰባስብነው አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው የተማረኩ ህጻናት የተናገሩት አስመልክቶ ነው። ሁሉም ማዘናቸውን ይገልጻሉ። ከታየውና ከሚሰማው በላይ ወደፊት እጅግ በርካታ ጉዶች ይፋ እንደሚሆኑ ሁሉም በየፊናቸው አመልክተዋል።

More stories

«የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ» የዲፕሎማሲው መንገድ መቀየር !

August 5, 2021

መልስ የሚሻ ዜግነታዊ ጥያቄ – ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ

May 9, 2021

… ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ …

January 29, 2021

የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ 22

September 12, 2022

“ምርኮኞቹ ከአሸባሪው ሕወሃት ጎን ተሰልፈው አገራቸውን በመውጋታቸው ተጸጽተዋል” ይላል የኢዜአ ዘገባ። በምስል ያሳያቸው ምርኮኞች ከአሸባሪው ሕወሃት ጎን ‘ተሰልፈን አገራችንን በመውጋታችን ተጸጽተናል’ እንዳሉም ይገልጻል። የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች የነበሩ ምርኮኞች ፣ኢትዮጵያ ጠል የሆነው የሽብርና የማፊያ ቡድን ለአገሩ ክብርና ሉዓላዊንት ዘብ የቆመን የመከላከያ ሰራዊት ከጀርባ በማጥቃት ግፍና ሰቆቃ መፈጸሙንም ያወሳል። ትህነግ ወጣት እንዳይኖር የማለ ይመስል ህጻናት እየነዳ እንደ እሳት እራት በራሪይ ይቆላቸዋል። አሁን ላይ ከየስፍራው የሚሰማው ድምጽ ይህ ነው። የሚገርመው ትህነግን ይህቺ አገር ምን አድርጋው ይሆን 50 ዓመት ሙሉ የሚያደማት? ህዝቧን የሚገለውና ጥሪቷን የሚያወድመው? ይህ ጥያቄ የሁሉም ሆኗል።

የጥቅምት ሀያ አራቷ ቀን በርግጥም ጥቁር ማክሰኞ ናት። የጥቁሯ ማክሰኞ ውሎ አዳር ግን የአንዲት የጀምበር ምህዋራዊ ሽክርክሪት ውጤት አልነበረም። ለዘመናት ተሰላስሎ፣ ተዘርቶ፣ ተኮትኩቶ፣ አፍርቶና ተወቅቶ የተበላ የጥላቻ ልክፍተኞች ሂሳባዊ ስሌት ውጤት እንጂ።አንዲት ጥንታዊት አገር ለመበታተን ህዝቦቿን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ተቆጣጥሮ፣ ትውልድን በጥላቻ መርዞ፣ የጥፋት ድግስ የቀመረ አሸባሪ ቡድን መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ነው።የጥላቻ ልክፍተኛ አሸባሪው ቡድን በሰራዊቱ ላይ ያደረሰውን ግፍና ሰቆቃ ለመግለጽ ግን ለብዙዎቻችን ቃላት ይቸግራል።

‘ቡድን ከፋባት እንጂ አልከፋችበትም፤ ለገሰች አልነፈገችውም፤ ግን ከውጭ ጠላት ጋር ተባብሮ ለማፍረስ መሞከር ከምን የመነጨ ይሆን?’ በማለት ይጠይቃሉ።የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ጭካኔ፣ ጥላቻ “ኢትዮጵያ ምን ብታደርገው ይሆን?” በማለት ለሁሉም ጥያቄ የሆነ መልሰ ቢስ ጥያቄ ያነሳሉ።

የሽብር ቡድኑ ለዘመናት በጥላቻ ኮትኩቶ ያሳደገውን ወጣት በማነሳሳት ኢትዮጵያን አስወግቷል፤ ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናትን በፕሮፓጋንዳ በማሰለፍ ወላጆችን ያለጧሪ አስቀርቷል፤ የታዳጊዎችንም ተስፋ አጨሟል።በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ድጋፍ ተመልሶ ወደ ስልጣን ለመምጣት የተቀናጅ ጥቃት ቢፈጽምም፤ ድርጊቱ ኢትዮጵያዊያን አስቆጥቶ ቡድኑ አከርካሪው ተሰብሮ ለስምንት ወራት ዋሻ ለዋሻ ሲሽሎከሎክ መቆየቱ ይታወሳል።

ማይካድራ ላይ አማራ ማንነት ያለችውን ዜጎች ጨፍጫፊዎችን ጨምሮ ከአሸባሪው ቡድን ጋር በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ያደረሱ ታጣቂዎች መካከልም ወደ ሱዳን ሸሽተው ቆይተዋል።ዳሩ ግን በሱዳን ከሚገኙ የሽብር ቡድን አመራር አባላት ዳግም ተመልምለው “በአሸንፈናል” ፕሮፓጋንዳ ሰክረው፤ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ቆርጠው አገራቸውን ማድማት የተመለሱ የቡድኑ አባላት እርምጃ ተወስዶባቸዋል፤ተማርከዋልም።በጥላቻ ልክፍተኞች ሰለባ ሆነው ከተያዙት መካከል አንዱ የ21 ዓመቱ ቸኮል በርሔ ነው።

ለወላጅ እናቱ ብቸኛ የሆነው ቸኮል የጥቅምት ሃያ አራት ክስተትን ተከትሎ በድሃ እናቱ ተነጥሎ በችኮላ ወደጦር ሜዳ እንዲጋዝ ተገደደ፤ ኑሮውን አሸንፎ የመለወጥ ህልሙም ከንቱ ቀርቷል።ቸኮልና ጓደኞቹ በውጊያ ተሸንፈው ወደ ሱዳን ቢሸሹም ከሰፍራው ከሚገኙ የአሸባሪው ሕወሃት አመራር አባላት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የመገናኛ ራዲዮን ተሸክመው በወልቃይት በኩል ወደ ትግራይ ሊገቡ ሲሉ ተማርከዋል።በከሃዲው የአሸባሪው ሕወሃት ቡድን ‘በሰሜን ዕዝ ላይ ያደረሰው ጥቃት አንገታችንን እንድንደፋ አድርጎናል’ የሚለው ቸኮል፤ በአሸባሪ ቡድኑ ስብከት ተታለው በታጣቂነት በመሳተፋቸውም መጸጸቱን ይናገራል።

ከአሸባሪው ቡድኑ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ከተማረኩት ውስጥ አለምሰገድ ተስፋዬ፣ ሀጎስ ተክለሃይማኖትና አቤል ብርሃኑም አገራቸውን በመውጋታቸው ተጸጽተዋል።የሕወሃት ቡድን ህጻናትን ጨምሮ የድሃ ልጆቹን ለጦርነት እያሰለፈ መሆኑን የሚናገሩት ምርኮኞቹ፣ ‘ወላጆቻችን የትና በምን ሁኔታ እንዳሉ አናውቅም፣ ስለኛም ወላጆቻችን አያውቅም’ ይላሉ።ምርኮኞቹ የመከላከያ ሰራዊት ከጀርባው በክህደት ቢወጋም እያደረገላችው ያለው እንክብካቤ ግን እንዳስደነቃቸው ገልጸው፤ ምንም ዓይነት ሰብዓዊ አያያዝ ችግር እንዳልገጠማችው ተናግረዋል።

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በአፋር ግንባር ትህነግ ሌላ ሽንፈት ደረሰበት፣ ሲያመልጥም ተደመሰሰ
“እንደን ማዕበል ገፍቶ ትህነግ የደፋቸው የጥፋት ሃይሎች በወጡበት እንዲቀሩ ተደርገዋል”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2