Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “እንደን ማዕበል ገፍቶ ትህነግ የደፋቸው የጥፋት ሃይሎች በወጡበት እንዲቀሩ ተደርገዋል”
News

“እንደን ማዕበል ገፍቶ ትህነግ የደፋቸው የጥፋት ሃይሎች በወጡበት እንዲቀሩ ተደርገዋል”

Ethioreview newsEthioreview news—August 10, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አሸባሪው ህወሓት በራያ ግንባር በሶስት አቅጣጫ የላካቸው ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን የአማራ ክልል አስታወቀ። ትህነግ እንደ ማዕበል ገፍቶ የደፋቸው” ሲል ብዛታቸውን የገለጸው መግለጫ ” ሳይመለሱ ቀርተዋል” ሲል ነው መደምሰሳቸውን ያስታወቀው። በዚህ ንዴት ወልደያን በመድፍ ደብድቦ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ምስኪን ዜጎች አጥቅቷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ እንዳሉት አሸባሪው ትህነግ የሰው ማዕበል አሰልፎ የሚከረው ወረራ ስላልተሳካለትና እንዳይወጣ ተደርጎ በመደምሰሱ ብጥስጣሽ ቁጥር ያላቸውን ቡድኖች በማዋቀር በተበታተነ መልኩ ሽብር የመፍጠር ሥልትን መከተል ጀምሯል።

የሽብር ቡድኑ እንደ ማዕበል ገፍቶ የደፋቸው የጥፋት መልእክተኞቹ በአማራ ልዩ ኃይል፤ ሚሊሻ፣ በብሔር ብሔረሰቦች ጥምር ኃይል እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት በኩል በተሠጣቸው አጸፋ ወደየትም ሳያፈገፍጉና ሳያመልጡ በወጡበት ለመቅረት እንደተገደዱ ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል። በዚሁ እርምጃ ሳቢያ አሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎቹን እንደማዕበል በማትመም ወረራ ለመፈፀም የሚጠቀምበትን የሰው ኃይል መክሰሩን ገልጸዋል።

በውጤቱም ተስፋ የቆረጠው የሽብር ቡድኑ በትላንትናው እለት በወልዲያ ከተማ ሠላማዊ ሕዝብ ላይ በሠነዘረው የመድፍ ጥቃት ለግዜው ቁጥራቸው ባልታወቁ ንጹሃን ላይ የህይወት እና የአካል ጉዳት ማድረሱንም አቶ ግዛቸው አመልክተዋል፡፡

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በዚሁ ወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ሃሳብ የሚከተለው ነው።

ማንኛውም የረጋ የውኃ አካል ቀድሞ ከነበረበት ሥፍራ ወደ አልነበረበት ሥፍራ ተገፍቶ ለመውጣት ማእበል መሆን የግድ ይለዋል፡፡ ማእበል ለመሆን ደግሞ ከውኃው ውስጣዊ ወይም ውጫዊ አካል የሚነሳ የእሳተ ገሞራ አሊያም የአውሎ ንፋስ ግፊት ያስፈልገዋል፡፡

በውስጣዊም ይሁን በውጫዊ አካል ግፊት የተነሳ የውኃ ማእበል ተረጋግቶ የነበረበትን ስፍራ ለቆ መንጎድ፤ ነጉዶም በደረሰበት ቦታ ላይ ተደፍቶ የመቅረት እንጂ ወደተነሳበት የመመለስ እድል የለውም፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ገፍቶ የላከው ታጣቂም ፍጻሜው በነፋስ ተገፍቶ እንደተነሳ የውኃ ማእበል ሁኗል፡፡ ለሽብር ቡድኑ የከሰረ ፍላጎት ተገፍተው የወጡት ሁሉ በወጡበት መቅረት እንጂ ተመልሶ የመሄድ እድል አላገኙም፡፡

ህልውናችንን በመጻረር ከፊታችን የተጋረጠው አብዛኛው ማእበል ክምር በጋራ ክንዳችን ብርቱ ምት መክኗል፤ አሁን የቀረ ማእበል አለ ከተባለም የቀረው የስኒ ላይ ማእበል ሊባል የሚችለው ብቻ ነው፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በራያ ግንባር በሶስት አቅጣጫዎች እንደ ማዕበል ገፍቶ የደፋቸው የጥፋት መልእክተኞች በአማራ ልዩ ኃይል፤ ሚሊሻ፣ በብሔር ብሔረሰቦች ጥምር ኃይል እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት በኩል በተሠጣቸው አጸፋ በወጡበት ቀርተዋል፡፡

በተወሰደባቸው ራስን የመከላከል እርምጃ ትህነግ እንደማዕበል በማትመም የአማራ ክልልን ለመውረር የሚጠቀምበት የሰው ኃይል እንዲያጣ ተገዷል፡፡ በዚህም ምክንያት ብጥስጣሽ ቁጥር ያላቸውን ቡድኖችን በማዋቀር በተበታተነ መልኩ ሽብር የመፍጠር ሥልትን መከተል ጀምሯል፡፡

በተበጣጠሰ አደረጃጀት ተበታትነው በስሪንቃ እና አካባቢው የተወሸቁት የሽብር እንደራሴዎች በወገን ኃይል ተከቦ ተገቢው እርማት እየተሠጣቸው ይገኛል፡፡ አሸባሪው ትህነግ በአዲስ አውሎ ነፋስ ከመሃል የትግራይ ከተሞች አዲስ ቀልጦ ቀር የታጣቂ ማእበል ለማስነሳት የሚያደርገው ጥረትም በተለያዩ ግባሮች ባሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እየመከነ ይገኛል፡፡

በዚህ አቅሙ የወገን ኃይልን መቋቋም ሥለተሳነውም በትላንትናው እለት በወልዲያ ከተማ ሠላማዊ ሕዝብ ላይ በሠነዘረው የመድፍ ጥቃት ለግዜው ቁጥራቸው ባልታወቁ ንጹሃን ላይ የህይወት እና የአካል ጉዳት አድርሷል፡፡ በሰላማዊ ዜጎች የመኖሪያ ቤቶችና ንብረቶች ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን እንገልጻለን፡፡

ሊያወድመን ተገፍቶ የመጣን የጥፋት ማእበል ባገኘንበት ስፍራ ሁሉ እንዳይመለስ አድርገን ከማስቀረት ውጭ ሌላ አማራጭ የሌለን መሆኑን በመገንዘብ መላው የአማራ ህዝብ በያለንበት ቦታ ላይ ህልውናውን የማስጠበቅ ተጋድሎውን አጠናክሮ ሊያሰቀጥል ይገባል፤ ግድ ይላልም፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከትግራይ ክልል ተጨማሪ ማዕበል እየገፋ ወደ ክልላችን በመላክ የእኛን ሙሉ ጊዜ፤ የሰው ኃይልና ሀብት የታጣቂ ማእበል በመቅበር ሥራ ላይ ብቻ ተጠምደን እንድንኖር ለማድረግ የሚሞክረውን ጥረትም ከስር ከስር ለመቅጨት መረባረብ የኃይላችንና የመላው ህዝባችን ተግባር እንዲሆን እናሳስባለን፡፡

ሥለሆነም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ህዝብ በህልውናችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ በአጭሩ ለመቅጨት ከእንግዲህ ዋናው ኢላማችን ሊሆን የሚገባው ተግፍቶ የመጣብንን ቀልጦ ቀር ማእበል መቅበር ብቻ ሳይሆን ለማእበሉ መነሻ ምክንያት የሆነውን አውሎ ንፋስ ከመነሻው የማጨንገፍ ትግልም ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም አውሎ ንፋሱ ከሌለ ማእበል ብሎ ነገር የለምና፡፡

ስለሆነም ውድ የክልላችን ነዋሪዎች፣ በአውደ ውጊያው ያላችሁ ታሪካዊ ጀግኖቻችን፣ የክልላችን የፖለቲካ ሊህቃን፣ ምሑራን፣ የማህበራዊ አንቂዎች፣ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች፣ መላው የክልላችን ወጣቶችና የኃይማኖት መሪዎች የጀመርነው ጦርነት አማራንና መላውን ኢትዮጵያዊያንን ለመበታተንና እድል ካገኘ እርስ በራሳችን እያባላ ስልቱን እየቀያየረ በሁሉም አከባቢዎች ጦርነትና እሳት እየለኮሰ እረፍት ከመንሳቱም ባሻገር ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር ጭምር በመወገን እንደለመደው ታሪካችንን ማበላሸት፣ ስነልቦናችንን ዝቅ ማድረግ፣ ቅርሶቻችንን፣ በወንድማማችነት አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን፣ በአጠቃላይ ሰባዊ፣ ቁሳዊ፣ ባህላዊና ኃይማኖታዊ ትውፊቶቻችንን የመዝረፍ፣ የማቆሸሽ አላማን አንግቦ በግላጭ እስከ ሲዖል ሊፋለመን ቆርጦ የተነሳ ያለማችን ቀንደኛ አሸባሪ ጋር መሆኑን ተገንዝበን ለእያንዳንዳችን የተሰጠንን ተልዕኮ ከልብ በመተግበር ህልውናችንን መታደግ ግዴታችን መሆኑን ከልብ ልንገነዘብ ይገባናል። ምርጫችን ሁለት መሆኑ ግልፅ እየሆነ መጥቷል።

ይሄውም የመጀመሪያው አማራጭ የመጣብንን አደጋ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከፍለን በጋራ ከፍለንና ተፋልመን ህልውናችንን ማስቀጠል፣ ታሪካችንን ከፍ ማድረግ፣ ትክክለኛ ዴሞክራሲና ሰላም የተረጋገጠበት ክልልና አገር መገንባት።

ሁለተኛው አማራጭ ህልውናችን አደጋ ውስጥ የሚገባበት፣ የጠላት አላማ ተሳክቶ በዓለማችን በሴራ እንደተበታቱኑን ጥቂት አገራት ለአብነትም እንደ ሶሪያ፣የመን፣ አፍጋኒስታን፣ ሊቪያ እንደመሳሰሉት ሀገራትና ሕዝቦች የምንበታተንበት፤ አሳፋሪ ታሪክ የምንከናነብበት፤ በዓለም አደባባይ የምንኮራበት ታሪካችንን የምናጠለሽበት፣ ሰይጣናዊ የጠላት አማራጭን መከተል ነው።

መቼም ቢሆን ጀግናው ሕዝባችንና ታጋዮቻችንን ምርጫችን የመጀመሪያው መሆኑ አያጠራጥርም። እናም የመጀመሪው ምርጫችንን አሳክተን በዓለም አደባባይ ኩሩ ሕዝቦች ለመሆን በስህተት የበቀለውን የአሸባሪውን የህውሓት አረምና የሕዝባችን የጋራ ጠላትና ካንሰር በተባበረ ክንድ በአንድነት ነቅሎ መጣል የግድ ይለናል። ደግሞም ይሆናል።

ድል ለጀግኖቻችን!!!

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ትህነግን ኢትዮጵያ ግን ምን አድርጋው ይሆን 50 ዓመት የሚያደማት? ” ምን አድርጉ ነው የሚሉን?”
“እምቢተኝነት ከሌለ ነፃነት አይገኝም ” የወልድያ ከተማ ወጣቶች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2