Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  አብይ ሲወጡ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አዲስ አበባ ገቡ – ከመጡት ይልቅ የሄዱት ዜና ሆኑ
News

አብይ ሲወጡ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አዲስ አበባ ገቡ – ከመጡት ይልቅ የሄዱት ዜና ሆኑ

Ethioreview newsEthioreview news—August 17, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለራ ጉብኝት አገር ውስጥ ባለመኖራቸው ምክንያት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት የተላኩትን በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን ጋር ተወያይተዋል።ይህን ተከትሎም ከገኡት እንግዳ ይልቅ የሄዱት አብይ ዜና ሆነዋል። በውይይቱ ሁሌም እንደሚባለው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ታሪካዊ ፣ የቆየ ፣ በጋራ ፍላጎትና ራዕይ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተጠቅሷል።

በቱርክ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ግብዣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ቱርክ እንደሚያቀኑ የቱርክ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬትን ጠቅሰው የቱርክ ሚዲያዎች ዘገበዋል። ከቱርክ ጉብኝታቸው በላይ ዜና የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጉብኝት ሲወጡ አሜሪካ የላከቻቸውን የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ አበባ መግባታቸው ነው።

ሁኔታውን የተከታተሉና አስቀድመው የመልዕክተኛውን ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሰሙ ” ምን ውይይት ያስፈልጋል? ትህነግ ካሁን በሁዋላ ክልል ሆኜ ልቀመጥ ነው የሚለው ወይስ ምንድን ነው? በኢትዮጵያ ሕዝብና በትህነግ መካከል ያለውን ልዩነት አሜሪካ እያወቅች ምን አይነት ሽምግልና ነው የምታራምደው?” በሚል ሲያጣጥሉ ከርመው ነበር።

ሳምናታ ፓዎር አዲስ አበባ በነበሩበት ወቅት ያላነጋገሯቸው አብይ አሕመድ መልዕክተኛውን ላይ ቢሯቸውን ቆልፈው መሄዳቸው ከላይ ከተቀመጠው አስተአየቶች ጋር የገጠመ ይመስላል። እልህ መጋባቱን ያለወደዱ ቢኖሩም፣ “ፌልትስ ማን ዙሪያውን እየዞሩ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ለመናድ እንደሚያሴሩ እየታወቀ ያን ያህል ክብር መስጠቱ አስፈላጊ አይደለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቋማችሁን ቀይሩ ማለታቸው ትክክል ነው” ሲሉ የተደመጡ አሉ።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ጄፍሪ ፊልትማን የኢትዮጵያ ህዝብ ለትህነግ ያለውን ስሜት እንደሚረዱ፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪቃ አንድ ሆና ሚናዋን እንድትወጣ የአገራቸው ፍላጎት መሆኑንን ጠሰው በተቃራኒው ከትህነግ ጋር ለውይይት መቀመጥን እንደ አንድ አስገዳጅ ጉዳይ ማቅረባቸው እርስ በርሱ የሚቃረን የተንኮል አካሄድ መሆኑንንም የገለጹ አሉ። አሜሪካ በቀጣናው ፋልጎቷን ለማሟላት ሰፊው ህዝብ የሚፈልገውን እንጂ፣ የሚጠላውን በማድረግ እንዴት ሊሳካላት እንደሚችል ሊገባቸው እንደማይችል ያስታወቁ አሉ።

ተቀብለው ያናገሯቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ቢያውቁትም ለምብራሪያቸው መነሻ የሽብር ቡድኑ ህወሃት በሰሜን ዕዝ ላይ ስላደረሰው ጥቃት እንዲሁም ቡድኑ እየፈጸማቸው ያለው አስከፊ  ድርጊቶች ለዚህ  ችግር መነሻ መሆኑንን የአገር ውስጥ መገናኛዎች ገልጸዋል።

ወራሪው  የሽብር ቡድን  በአሁኑ ወቅት በአፋርና በአማራ ክልሎች ግልጽ ወረራ ፣ ዝርፊያና ግድያ በማካሄድ ከፍተኛ ሰብዓዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ወንጀሎችን  እየፈጸመ መሆኑን አቶ ደመቀ ገልጸዋል። ቡድኑ እነዚህን ሁሉ ወንጀሎች እና ክህደት በሚፈጽሙበት ጊዜ የአሜሪካ መንግስት ዝምታን መርጧል ብለዋል። ይህም በሁለቱ ወንድማማች  ሀገራት ግንኙነት ውስጥ ያልተለመደና የሁለቱን  የወንድማማች ሀገሮች ግንኙነት የማይመጥን ነው ብለዋል።

አቶ ደመቀ አያይዘውም አሜሪካ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በሚመጥን መልኩ የወራሪ ኃይሎችን አጥፊ ድርጊቶች እንደምትኮንነው  ኢትዮጵያ  ተስፋ ታደርጋለችም ነው ያሉት። ቡድኑ ከተመሰረተ  ጊዜ  ጀምሮ ቀጠናውን እያወከ መሆኑን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ  በአንክሮ ሊገነዘበው  ይገባልም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።

ልዩ መልዕክተኛው ጄፍሪ ፊልትማን  በበኩላቸው፣ የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ በሽብር ቡድኑ ላይ ያለውን አመለካከት በሚገባ እንደሚረዳ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ ሰላምና አንድነት ጠብቆ ማቆየትና ማረጋገጥ የአሜሪካ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ላይ መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸውም ብለዋል። በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት ቀጠናዊ ጠቀሜታ  ያለው መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል።

ልዩ መልዕክተኛው  በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፎቶና መነሻ ዜና ፋና

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የጦርነቱ አበሳና ቀጣዩ ስጋት – በሰልባዎቹ አንደበት
ለአሸባሪው ህወሓት የቀረበ ምስጋና
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2