Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Thoughts on an American-mediated settlement in Ethiopia

    January 26, 20220

    Pelé dies aged 82

    December 29, 20220

    As BRICS Accumulate Gold, Western Banks Continue to Short Sell

    October 15, 20240

    የአውሮፓ ሕብረት የ38 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

    November 10, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    አደዋ መንፈስ ነው ይጋባብን!!

    March 2, 20240

    ነፋስና የበረዶ ውሽንፍር የበላት ቡፋሎ ከተማ ‘የጦርነት ቀጠና’ 

    December 27, 20220

    «የኢትዮጵያ አንድነት የሚቆመው በጋራ ስንሠራ ነው ብለን ተስማምተናል”

    February 12, 20220

    “የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ

    December 8, 20210

    ካረን ባስ – አቋማቸውን አስተካከሉ፤ ጠ/ሚ አብይን በማንሳት ጉዳይ እንደማይስማሙ ይፋ አድረጉ

    November 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  አብይ አሕመድ ለሕባቸው መልዕክት አስተላለፉ!!
News

አብይ አሕመድ ለሕባቸው መልዕክት አስተላለፉ!!

Ethioreview newsEthioreview news—September 10, 20210
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አሕመድ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- 

እንኳን ለ2014 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 

ይሄን አዲስ ዓመት የምናከብረው በወሳኝ ሀገራዊ ፈተናና ተስፋ መካከል ሆነን ነው። ኢትዮጵያ በፈተና እና ተስፋ መካከል ሆና አዲስ ዓመት ስታከብር ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ምናልባትም የመጨረሻዋም አይሆንም። ኢትዮጵያውያን ፈተና የማያስበረግገን፣ ድልም የማያሰክረን ስለመሆናችን ዓለም ሁሉ ያውቃል። ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር ታሪክ ከሚያነሣቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ ዐቅሙም አቋሙም አለን። 

ኢትዮጵያን የሚፈትኗት ኢትዮጵያን የማያውቋት ናቸው። ኢትዮጵያ ለሺ ዓመታት በነጻነት ኖረች ሲባል ትርጉሙን አይረዱትም ማለት ነው። ጠላት አጥታ አይደለም ሺ ዘመን በነጻነት የኖረችው። ፈተና ረስቷት አይደለም የነጻነት ቀንዲሏ ሳይጠፋ እስከ ዛሬ ያለው። ኃያላን ራርተውላት አይደለም ከከፍታዋ ያልወረደችው። ሁሉንም እንደ አመጣጣቸው አሸንፋ ብቻ ነው። ታሪካችንን ሳያውቁ የሚገጥሙንን ታሪካችንን ዐውቀን እንጠብቃቸዋለን። ለወዳጃችን ወተት፣ ለጠላታችን ዕሬት መስጠት እንችልበታለን።

More stories

“አሻባሪው ህወሃት የአፍሪካ ቀንድን በማተራመስ የአንዳንድ ምዕራባውያንን ተልዕኮ ለማስፈፀም ሞክሯል”

December 25, 2021

ደመቀ መኮንን ዛሬ ያነጋገሯቸውን የአውሮፓ አገራት ዲፕሎማቶችን ወቀሱ

October 25, 2021

አብይ አሕመድ 60 ከመቶ ከኤሌክትሪክ ጋር የማይተዋወቁ ዜጎች ቅድሚያ መሆናቸውን አመለከቱ

January 20, 2022

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ከቶም ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከማሸነፍ እንጂ ከመሸነፍ ጋራ ተጠርቶ አያውቅም። ከነጻነት እንጂ ከባርነት ጋራ ዝምድና የለውም። ኢትዮጵያ ተፈትና ታውቃለች። ተሸንፋ ግን አታውቅም። ቀጥና ታውቃለች፤ ተበጥሳ ግን አታውቅም። የዘመመች መስላ ታውቃለች፤ ወድቃ ግን አታውቅም። ይህ አዲሱ ዓመት ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን የተጣባትን ፈተና የምንገላገልበት፣ አዲስ መንግሥት የምንመሠርትበት፣ ከደረሰብን ፈተና የምናገግምበትና ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ ብልጽግና የምናዞርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው። አዲሱ ዓመት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን የሚጸናበት፣ ዴሞክራሲያዊ ዕሴቶቻችን የሚጎለብቱበት፣ የጀመርነው ሪፎርም መልክ የሚይዝበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ፈተናችን ከኋላ፣ ተስፋችን ከፊት ነው።

በሀገር ፍቅር የነደደ፣ በማንነቱ የሚኮራ፣ አካባቢያዊ ማንነቱ ከሀገራዊ ማንነቱ ጋር የተስማማለት፤ አዳዲስ ፈጠራዎችን መሞከር የማይታክተው፤ ባልተሄደበት ለመጓዝ ድፍረትና ጽናት ያለው፣ ጋራ ሸንተረሩን በደንና በምርት ለመሸፈን የሚተጋ፣ አዲስ ትውልድ እየተፈጠረ ነው። ኢትዮጵያ በልጆቿ ተስፋዋን ሰንቃለች። ለሀገራችንም ሆነ ለግል ሕይወታችን አዲስ ዓመት አዲስ ነገር ይዞ የሚመጣው ለአዲስ ለውጥ ራሳችንን ባዘጋጀንበት ልክ፣ ለመለወጥ ባለን መሻትና እሱን ለማሟላት በሚናሳየው ትጋት መጠን ነው።

ለውጥን ከራሳችን ሳንጀምር የሀገራችንን መለወጥ የምንናፍቅ ከሆነ ዘመኑ እንጂ እኛ አልተቀየርም። በሀገር ጉዳይ ጣት ከመጠቆም ይልቅ “ከእኔስ ምን ይጠበቃል?” ማለት ካልጀመርን ዘመኑ አዲስ ቢሆንም እኛ አሮጌው ላይ ቆመን ቀርተናል። እንደ ሀገር ወደ አዲሱ ዘመን የምናደርገው ሽግግር የሚጎዱንን አሮጌ ማንነቶች በመጣልና በአዲስ ጠቃሚ ማንነቶች በመተካት መሆን አለበት። በየግላችን ከምናደርገው ሩጫ ይልቅ ለጋራ ራዕይ ከተጋን፣ እርስ በእርስ መጓተቱን ትተን ለመተባበር ከቆረጥን፣ ጥላቻን ንቀን ፍቅርን ካነገስን ያኔ ለሀገራችን አዲስ ዘመን ይመጣል። አዲስ ዓመት ተፈጥሯዊ ነው። አዲስ ዓመትን ሰዋዊ ማድረግ የሚቻለው እኛ በአዲስ ጎዳና ከተጓዝን ነው። ምንጊዜም ያለፈው መነሻችን ነው። የዛሬው መጓዣችን ነው።

የነገው ደግሞ መድረሻችን። ትናንት የተጓዝንበትን መንገድ እንደ አዞ አናጠፋም። እንደ ፍየል ቀንድም ትናንትን ብቻ እያየን አንኖርም። ዛሬ ትልቁ ሀብታችን ነው። ዓመትን አዲስ ማድረግ የሚቻለው ዛሬን በመጠቀም ነው። የ2013 የመጨረሻው ገጽ ጳጉሜን 5 ቀን ተጠናቅቋል። መቼም አይመለስም።የ2014 ዓ.ም አዲሱ ገጽ መስከረም 1 ይገለጣል። ማንም ምንም አልጻፈበትም። አዲሱ ዓመት ሁለት ነገሮችን ለመቀበል ዝግጁ ነው። በባዶው ገጽ ላይ የሚጽፍ ጀግና እና የሚጻፍበት ታሪክ። እኛ ዝም ብንል፣ ሌሎች የኛን ነገር በፈለጉት መንገድ ይጽፉበታል።

እኛ ባንጽፍም የኛ ያልሆነ ነገር ይጻፍበታል። አሁን ቁልፉ ጥያቄ አንድ ነው። በዚህ ለሁሉም ባዶ ሆኖ በቀረበው አዲሱ የዘመን መጽሐፍ ላይ እኛው ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ዕጣ ፈንታ እንጽፋለን? ወይስ ሌሎች እንዲጽፉልን አሳልፈን መጽሐፉን እንሰጣለን? አባቶቻችን የራሳችንን የዘመን አቆጣጠር ሲፈጥሩ የራሳችንን የዘመን መጽሐፍ እንድናዘጋጅና የራሳችንን ዕጣ ፈንታ እኛው ራሳችን እንድንጽፍ ያሰቡ ይመስለኛል። 

እኛው ዐቅደን፣ እኛው ሠርተን፣ እኛው ችግሮቻችንን ፈትተን፣ እኛው ተነጋግረን፣ እኛው ተወያይተን፣ እኛው ዘምተን፣ እኛው አሸንፈን፣ እኛው አልምተን፣ እኛው ተጠቅመን፣ እኛው አምርተን፣ እኛው ረሐብ አሸንፈን – የእኛኑ ጉዳይ እኛው እንድንወስን ይመስለኛል። በአዲሱ መጽሐፍ ላይ መጻፍ ብቻ ሳይሆን አዲሱን መጽሐፍም ራሳችን እንድናዘጋጅ ያሰቡ ይመስለኛል። በራሳችን ቁሳቁስ፣ በራሳችን ፈጠራ፣ በራሳችን መንገድ የራሳችንን የዘመን መጽሐፍ፣ ለእኛው በሚስማማ መንገድ፣ እኛው እንድናዘጋጀው ያሰቡ ይመስለኛል። 

የዘመን መጽሐፉን የፈጠርን ሰዎች በዘመን መጽሐፉ ላይ በራሳችን መንገድ የራሳችን ዕጣ ፈንታ በእጆቻችን ለማሳረፍ የሚያቅተን ነገር የለም። ዕንቅፋቶቻችን እየተወገዱ ነው፤ ወደረኞቻችን ሁሉ ድል እየሆኑ ነው። ዘመኑ የኢትዮጵያ ነው። አዲሱ ዓመት የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ በአዲሱ የዘመን መጽሐፍ ላይ አዲሱን የብልጽግና ጉዞዋን ትጽፍበታለች። ድሏንና አሸናፊነቷን ትጽፍበታለች። ክብሯንና ታላቅነቷን ትጽፍበታለች። ሀገራችን ብልጽግናና ድሎቿን ለመጻፍ ስትነሳ መጻፊያ ብዕሯ እኛ ነን፡፡ ቀለሙም የሚቀዳው ከላብና ከደማችን ነው፡፡ ዜጎች ተደጋግፈው በጋራ ለማደግ ሊነሱ ኢትዮጵያ የጨበጠችው ብዕር በአግባቡ መሥራት ይጀምራል፡፡ ዜጎች እርስ በእርስ ሲተሳሰቡ ብዕሩ ትርጉም ያለው ገድል ይጽፋል፡፡ የሀገር ልጆች ልዩነታቸውን ጠብቀው በጋራ ጉዳይ አብረው መቆም ሲችሉ ያኔ ብዕሩ ድልን አድምቆ ይጽፋል። በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት፣ ዘመኑ አዳዲስ ስኬቶችን የምናስመዘግብበት ይሁን!! 

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር! 

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

ሃያ አራት ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጥሪ አቀረቡ
በአንድነት ፀንተን እንቁም – ደመቀ መኮንን
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

Egypt and Eritrea Ink Maritime and Security Deals: What It Means for Ethiopia

June 10, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
News

ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

June 5, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚 𝐚𝐧𝐝 𝐍𝐢𝐠𝐞𝐫𝐢𝐚 𝐃𝐞𝐞𝐩𝐞𝐧𝐏𝐚𝐫𝐭𝐧𝐞𝐫𝐬𝐡𝐢𝐩 𝐭𝐡𝐫𝐨𝐮𝐠𝐡 𝐁𝐢𝐥𝐚𝐭𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐓𝐚𝐥𝐤𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐋𝐞𝐠𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐨𝐩𝐞𝐫𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐀𝐠𝐫𝐞𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭

June 10, 20260
News

Egypt and Eritrea Ink Maritime and Security Deals: What It Means for Ethiopia

June 10, 20260
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
Load more
Recent Posts
  • 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚 𝐚𝐧𝐝 𝐍𝐢𝐠𝐞𝐫𝐢𝐚 𝐃𝐞𝐞𝐩𝐞𝐧𝐏𝐚𝐫𝐭𝐧𝐞𝐫𝐬𝐡𝐢𝐩 𝐭𝐡𝐫𝐨𝐮𝐠𝐡 𝐁𝐢𝐥𝐚𝐭𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐓𝐚𝐥𝐤𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐋𝐞𝐠𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐨𝐩𝐞𝐫𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐀𝐠𝐫𝐞𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭 June 10, 2026
  • Egypt and Eritrea Ink Maritime and Security Deals: What It Means for Ethiopia June 10, 2026
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news