Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ
News

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

Ethioreview newsEthioreview news—May 5, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዓለም አስደማሚውን የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተጋድሎ ድል እና ተዓምራዊ ክስተት ካጣጣመ አራት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ተሸናፊዎቹ ሰላቶዎች ያልጠበቁት ምትሃታዊ ሽንፈት የእግር እሳት ሆኖባቸው ለሌላ እልቂት እና ጦርነት ቂም ቋጥረው በደል ጠንስሰው ቀን እየጠበቁ ነው፡፡ ፋሽስት ጣሊያን አርባ ዘመኗን ሁሉ ለዳግም ወረራ ስትዘጋጅ ኢትዮጵያ ግን የተለየ ዝግጅትም፤ የተሻሻለ አቅርቦትም አላደረገችም ነበር፡፡

ከዓድዋ ድል ማግስት ጀምሮ በኢትዮጵያ በኩል የተለየ የሚባል ክስተት ካለ ሊጠቀስ የሚችለው የነገስታቱ ለውጥ ብቻ ነበር፡፡ የዓድዋ ድል ጉልላት የነበሩትን ንጉሰ ነገስቷን የተፈጥሮ ሕግ በሆነው ሞት ያጣችው ኢትዮጵያ ከልጅ ኢያሱ እና ከንግስተ ነገስት ዘውዲቱ ተሸጋግራ በጊዜው ተራማጅ ከሚባሉት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መዳፍ ላይ ወድቃለች፡፡ ንጉሰ ነገስቱም ዘውድ ከጫኑ ማግስት ጀምሮ በሀገሪቱ ሥር የሠደደውን ዘውዳዊ ሥርዓት የጎሪጥ እየገረመሙ፤ ተራማጅ ሀገር እና ሥርዓት ለማንበር ምቹ አጋጣሚ ያማትራሉ፡፡

ከሁለተኛው ዙር የጣሊያን ወረራ አምስት ዓመታት ቀደም ብሎ በበርካታ ውጣ ውረድ መካከል አልፈው ንጉሰ ነገስት ተብለው የተቀቡት ጃንሆይ ይህችን ጥንታዊት፣ ቀዳማዊት እና ታሪካዊት ሀገር የመምራት አጋጣሚው ጫንቃቸው ላይ አርፏል፡፡ የመጨረሻው ሰለሞናዊ ንጉስ ታሪክ የሰጣቸውን መልካም እድል ማባከን አልፈለጉም፡፡

ጃንሆይም ከቀደምት አባቶቻቸው የመሪነት ጥበብን፤ ከዓልም አቀፉ የፖለቲካ አሰላለፍ እውቀትን አጣምረው ነጻዋን አፍሪካዊት ሀገር በባህላዊም በዘመናዊም መንገድ ማስተዳደራቸውን ቀጥለዋል፡፡ የንጉሰ ነገስቱን ግለ ታሪክ የጻፈው ሃጋይ ኤርሊክ “ጃንሆይ በወቅቱ ወግ አጥባቂውን ነባር ሥርዓት በተራማጁ ለውጥ ፈላጊ ተተኪ ወጣት ቀስ በቀስ ለመለወጥ ብርቱ ሥራ ላይ ነበሩ” ይሉናል፡፡

More stories

“ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሤ

May 5, 2023

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

ትግራይ በራሷ ልጅ አንደበት ምስክርነት

June 28, 2021

“ኑ ! የወልቃይት ምድር ነጻ ወጥቷል” በስደት የሽሽት ኑሮ ላይ የነበሩ አማሮች ወደ ወልቃይት ጠገዴን ሰቲት ሁመራ ተመለሱ

June 17, 2021

ለንጉሰ ነገስቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከንግስናቸው ማግስት ጀምረው የነበሩት አምስት ዓመታት እጅግ መልካም የሚባሉ ሆነውላቸው ነበር፡፡ አልጋቸው እረግቶ እና አጀባቸው በዝቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ቦታ እንደ አዲስ መገንባት የሚችሉበትን ነጻነት እና ኃይል አገኙ፡፡

ንጉሰ ነገስቱ በእነዚህ ዓመታት የሀገራቸውን እና የራሳቸውን እጣ ፋንታ የሚወስኑት እራሳቸው ብቻ ነበሩ፡፡ ገና አልጋ ወራሽ እያሉ በርካታ የምዕራቡ ዓለም ሀገራትን የመጉብኘት እድል እና አጋጣሚ ያገኙት ንጉሰ ነገስቱ የገበዩትን እውቀት እና የሸመቱትን ተሞክሮ ተጠቅመው ኢትዮጵያን ከራሳቸው ጋር እንድትመሳሰል አድርገው ለመሥራት ደፋ ቀና እያሉ ነበር፡፡

በዚህ ሁሉ መካከል ግን በዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች አናት ላይ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥታ አሳፋሪ ሽንፈትን የተጋተችው ጣሊያን ለዳግም ወረራ ዝግጅት ማድረጓን በሰሚ ሰሚ ከንጉሰ ነገስቱ እና መኳንንቶቻቸው ጆሮ ደርሷል፡፡ ከመጀመሪያው ወረራ ሽንፈቷ ብዙ የተማረችው ጣሊያን በምሥራቅ አፍሪካ የተንሰራፋ የቅኝ ግዛት ይዞታ እንዲኖራት ብትፈልግም በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል ኤርትራን ብቻ ይዛ በሠላም መቀጠል እንደማትችል ግን አውቃዋለች፡፡ ለዚህም ሲባል በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ እና ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ልዩ ተልዕኮ በልዩ ዝግጅት ቋፍ ላይ ደርሷል፡፡

ማርሻል ኢሚሎ ደቦኖ የጣሊያን ቅኝ ግዛት ሀገሮች ኮሚሽነር ሆኖ ተሹሟል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል በኮሚሽነሩ የሚመራ እና ከሊቢያ፣ ከሶማሊያ እና ከኤርትራ የተውጣጣ 400 ሺህ ወታደር ተዘጋጅቷል፡፡ ከ1920ዎቹ ጀምሮ ብርቱ ቅድመ ዝግጅት ላይ የነበረችው ጣሊያን ይህንን ዘመቻ በማያዳግም ሁኔታ ለመፈጸም ከ300 በላይ የጦር አውሮፕላኖች ለግዳጅ ዝግጁ አድርጋለች፡፡ በሌላ በኩል በማርሻል ሮዶልፍ ግራዚያኒ የሚመራ ኃይል መነሻውን በደቡብ በኩል አድርጎ በ100 አውሮፕላኖች እየታገዘ ወደ መሃል ኢትዮጵያ እንዲንቀሳቀስ ግዳጅ ተሰጥቶታል፡፡ በጣሊያን በኩል ይህ ሁሉ የሚሆነው የሊግ ኦፍ ኔሽንን ተፅዕኖ ለመቋቋም አዲስ አበባን በአጭር ጊዜ መቆጣጠር የሚል ዓላማ አንግባ ነበር፡፡

ከጣሊያን ዘውዳዊ መንግሥት የጦር ኃይል ተቀንሶ ተጨማሪ እና ተጠባባቂ 650 ሺህ ሠራዊት ኤርትራ ገብቷል፡፡ በከፍተኛ ሥንቅ እና ትጥቅ ተጠናክሮ የገባው ይኽ ጦር አይቀሬውን የወረራ ድል በብቃት ይፈጽማል የሚል እምነት ተጥሎበታል፡፡ ማርሻል ሮዶልፍ ግራዚያኒም ለሮማዊያን ሁሉ “ኢትዮጵያን ከነሰዎቿ ወይም ያለሰዎቿ ተረክቤ አስረክባችኋለሁ” ሲል በጀብደኝነት ቃል ገብቷል፡፡ የጦርነቱን ጣፋጭ የድል ብሥራት ዜና እየተከታተሉ ለዓለም ሕዝብ ጆሮ ቀለብ ለማድረስ እና የዓድዋ ጦርነት የተሸናፊነትን ትርክት ለማረም 200 ያህል ጋዜጠኞች አብረው ተሰማርተዋል፡፡

እጅግ የላቀ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጅት ያደረገውን የጣሊያን ወራሪ ኃይል የሚመክተው ኋላ ቀር የጦር መሣሪያ የታጠቀውና ዘመናዊ የውትድርና ሥልጠና ያላገኘው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት ነበር፡፡ አይቀሬው የጦርነት ነጋሪት በፍሽስት ጣሊያን እየተጎሰመ ተጀምሯል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ከሽሬ እስከ እንዳባጉና፣ ከተምቤን እስከ ዓቢይ ዓዲ፣ ከእምባ አርአዶም እስከ አምባ አላጌ የሞት ሽረት ውጊያዎች ተካሄዱ፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች በተደረጉት ጦርነቶች ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሀገር ወዳድ ቢያልፍም በተለይም በሽሬ በተደረገው ጦርነት 300 ያክል መትረጌሶች፣ ታንኮችና ሌሎችም ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች ተማረኩ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ግንባር በማርሻል ግራዚያኒ የሚመራውን የጦር ኃይል የነራስ ደስታ፣ ደጃዝማች ነሲቡ እና የራስ መኮንን የጦር ኃይል በኦጋዴን በተደረገው ጦርነት ገጥሞታል፡፡ በቦነያ ነቀምት ደጃዝማች ሃብተ ማርያም እና በሲዳማ ራስ ደስታ ዳምጠው አይቀሬውን ጦርነት ተጋፍጠዋል፡፡ በዚህ ሁሉ መካከል በሰሜኑ ክፍል በወርሃ መጋቢት 1928 ዓ.ም ማይጨው ላይ በተደረገው ጦርነት በንጉሠ ነገሥቱ የሚመራና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ቢሰለፍም ኢትዮጵያዊያኑ ድል ሆኑ፡፡

በሁሉም አቅጣጫ በለስ የቀናቸው ጣሊያናዊያኑ የሀገሪቱን ርእሰ መዲና አዲስ አበባ ተቆጣጠሩ፡፡ ማርሻል ባዶሊዮ ሚያዝያ 27/1928 ዓ.ም አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አስወርዶ፤ ቀይ ነጭ እና አረንጓዴውን ባንዲራ በአዲስ አበባ ሰማይ ስር አውለበለበው፡፡ “ይኽን ቆሞ ከማየት ሞት በስንት እጁ ይጥማል” ያሉት አርበኞችም ውሎ እና አዳራቸውን በዱር በገደሉ አድርገው እምቢ ለነጻነቴ አሉ፡፡

ኢትዮጵያ በንጉሠ ነገሥቷ አማካንነት የዓለማቀፉን ማሕበረሰብ ድጋፍ ብትጠይቅም የዓለም መንግሥታት ጆሮ ነፈጓት፡፡ ጭራሽ በጣሊያን ላይ አስተላልፈውት የነበረውን ማዕቀብ ነሐሴ/1928 ዓ.ም ላይ አነሱት፡፡ ታኅሳስ/1929 ዓ.ም ላይ ደግሞ ጃፓን የጣሊያንን ቅኝ ገዥነት እውቅና ሰጠችው፡፡ ፈረንሣይ እና እንግሊዝም ከቅኝ ገዥዋ ጣሊያን ጎን በመቆም የድጋፍ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ በርካቶቹ ኃያላን ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ ፊታቸውን አዞሩ፡፡ ጣሊያንም ከየአቅጣጫው የሚጎርፍላት ድጋፍ የልብ ልብ ሰጥቷት የተከለከለውን የመርዝ ጋዝ እስከመጠቀም ድረስ የግፍ ዶፍ አዘነበች፡፡

ከሜክሲኮ እስከ ቻይና፣ ከኒውዚላንድ እስከ ሶቪየት ኅብረት፣ ከስፔይን ሪፐብሊክ እስከ አሜሪካ ወራሪው የጣሊያን መንግሥት በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ ተቃወሙ፡፡ ነገር ግን እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት መቀስቀስ ድረስ እነዚህ ሀገራት ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም ሆነ ለኢትዮጵያ ያመጡት ተፅዕኖ፤ የፈጠሩት ለውጥ አልነበረም፡፡ የዘገየው ዲፕሎማሲ በንጉሰ ነገስቱ እና ልዑካቸው በመላ አውሮፓ እየተዘዋወረ “ፍትህ ወዴት አለሽ” ቢልም ኃያላኑ የጣሊያንን ክፉ ላንሰማ “የዝሆን ጆሮ ይስጠን” አሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ግን “እንኳን ሰዎቹ ምድሪቱ እንኳን ለወራሪዎች እሾክ ትሁን” ተብሏልና የሞት ሽረት ትግሉ በአሃድም በህቡዕም አልተቋረጠም፡፡

በዓለም መንግሥታት ማሕበር ፊት ጀኔቭ አደባባይ ላይ ቆመው “ዛሬ እኛ ነን ነገ ደግሞ እናንተ ትሆናላችሁ” ያሉት ንጉሰ ነገስቱ ትዕምቢታቸው እውን ሆኖ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ተቀሰቀሰ፡፡ ጦርነቱ የዓለም ሀገራት በተለይም በጅኦ-ፖለቲካል አጠራራቸው ምዕራባዊያኑ ሀገራት ጎራ ለይተው ተሰለፉበት፡፡ ፋሽስት ጣሊያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጀርመን ናዚ ደጋፊ ሆና ብቅ አለች፡፡ ይኽ አቋሟ ደግሞ በተለይም እንግሊዝ ጥርስ እንድትነክስባት አደረጋት፡፡ ኃያላን አንሰማም ያሉትን የፍትህ ድምጽ የኃያላን አምላክ ሰምቶ እንደ ባቢሎናዊያን እርስ በእርስ አናከሳቸው፡፡

ሲለመኑ እምቢ ያሉት እንግሊዞች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጣሊያን ከናዚዎች ጎን መሰለፏን ተከትሎ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም ከስደት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መንገድ ጠራጊ የፍትህ መልዕክተኛ ለመሆን ወሰኑ፡፡

በጀኔራል ካኒንግሂም የሚመራው የእንግሊዝ ጦር ከኬኒያ ተነስቶ ከደቡብ አቅጣጫ ወደ መሃል ኢትዮጵያ ገሰገሰ፡፡ በጄኔራል ፕላት የሚመራው ጦር ደግሞ ከሱዳን ተነስቶ ወደ አስመራ፤ ከአስመራ ወደ መሃል ኢትዮጵያ ተንቀሳቀሰ፡፡ ጌዲዮን የሚል ስያሜ የተቸረው ጦር በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አርበኞች እና በእንግሊዝ አማካሪዎች ተዋቅሮ ከሱዳን ተነስቶ በኦሜድላ አልፎ በጎጃም በኩል ወደ መሃል ሀገር ገሰገሰ፡፡

በዚህ ሁሉ መካከል ግን እምቢ ለሀገሬ ያሉት አርበኞች አጣብቂኝ ውስጥ የወደቀውን የፋሽስት ጦር ቁም ስቅሉን ያሳዩታል፡፡ በቡድን ወጥቶ በተናጠል የሚመለሰው የጣሊያን ጦር በኢትዮጵያዊያኑ አርበኞች አይገመቴ የጦር ታክቲክ እየከፈለው ባለው የሕይዎት ዋጋ ተሰላችቷል፡፡ ዘመቻው ከተጀመረ ሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ የፋሽስት ጦር አዲስ አበባን ለቆ ፈረጠጠ፡፡ መጋቢት 28/1933 ዓ.ም የጄኔራል ካኒንግሃም ጦር አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡

ኢትዮጵያ በርእሰ መዲናዋ አዲስ አበባ ሰማይ ስር የማይመስላትን እና የማያምርባትን ባንዲራ ባውለበለበች ልክ በአምስተኛው ዓመት ሚያዝያ 27/1933 ዓ.ም አዲስ ታሪክ ተመዘገበ፡፡ ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በከፍተኛ አጀብ እኩለ ቀን ላይ ከታላቁ በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት አደባባይ ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ዓላማ መልሰው አውለበለቡት፡፡ መድፍ ደጋግሞ እያጓራ፣ የክብር ዘብ ተሰልፎ፣ አርበኞች በፍጹም ብሔራዊ ኩራት ቆፍጠን እንዳሉ ንጉሰ ነገስቱ እንዲህ አሉ

“ይህ የምትሰሙት ድምጽ የእኔ የንጉሳችሁ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድምጽ ነው፡፡ ይኽ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ከከባድ የመከራ ቀንበር እና ከዘላለም ባርነት ነጻ የወጡበት ቀን ነው፡፡ እኛም አምስት ዓመታትን ሙሉ ተለይተነው ከነበረው፤ ከምንወደው እና ከምንናፍቀው ሕዝባችን ጋር ለመቀላቀል የበቃንበት ቀን ነው፡፡ ስለሆነ ይህ ቀን የተከበረና የተቀደሰ በየዓመቱም ታላቁ የኢትዮጵያ ልጆች የድል በዓል ሆኖ ይከበራል” ሲሉ የአርበኞች ቀንን በአርበኞች መካከል ቆመው አወጁ፡፡

ኢትዮጵያም ከነሰዎቿም ሆነ ያለሰዎቿ ለባዕድ ሳትረካከብ ዳግም በንጉሰ ነገስቷ መዳፍ ውስጥ አረፈች፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም ኃያላን ጆሮ የነፈጉት የፍትህ ጥያቄዋ በልጆቿ እና ጎራ ባመሰቃቀላቸው ወዳጆቿ ከምንም በላይ ደግሞ በታመነችው የፍትህ አምላክ ዳግም ነጻ ወጣች፡፡ ሀገር በትውልድ ቅብብሎሽ ስትረማመድ አልጋ ባልጋ ሳይሆን እሾክ እና ቀጋ እየፈተኗት እንደነበር ታሪክ ምስክር ነው፡፡

የመረጃ ምንጮቻችን፡- “አጼ ኃይለ ሥላሴ አነሳሳቸው እና ውድቀታቸው” ሃጋይ ኤርሊክ፤ “የዓድዋ ጦርነት እና የዓለም ቅኝ ግዛት አሰላለፍ” በኤርሚያስ ጉልላት እና “የኢትዮጵያ ታሪክ” ሪቻርድ ፓንክረስት

በታዘብ አራጋው / አሚኮ

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?April 26, 2026
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም ሆነ በአሉታ አልተነፈሱም።… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትApril 26, 2026
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ እንግዶች ፊት ፕሬዝዳንት… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊApril 26, 2026
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን ተከትሎ ያኮረፉት ፕሬዚዳንት… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውApril 26, 2026
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እርስ በርስ የሚረዱበትን አዲስ የጋራ መከላከያ ስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት መስማማታቸውን አስታወቁ። በቆጵሮስ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችApril 26, 2026
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን የከፋ ቀጣት ይጠበቃቸዋል። ባለፉት ጥቂት… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ከአርበኝነት ውርስ ባሻገር”
US and WFP suspend food aid to Tigray
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2