Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  አሁን ነገሮች ተቀያይረዋል – አዲስ አበባ የማይደረስባት መንግስት ሰማያት ሆናለች!!
News

አሁን ነገሮች ተቀያይረዋል – አዲስ አበባ የማይደረስባት መንግስት ሰማያት ሆናለች!!

Ethioreview newsEthioreview news—September 1, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail


ነገሮች እንደሚለዋወጡ የሚጠበቅ ነበር። አሁን የምናየውና የምሰማውም፣ የነበረው ተቀይሮ፣ በደመ ነፍስ የሚግተለተለው ሃይል፣ ተግትቶና የኋላ ማርሽ አስገብቶ ሲፈረጥጥ ነው። ካለፈው ሳምንት ወዲህ የህወሀት ቡድን ስካሩ በርዶለታል። አጉራ ዘለልነቱ ሉጋም ተበጅቶለታል።

በድንገት ባልታሰበ አቅጣጫ፣ የሳሳ የመከላከያ መስመር ያለበትን አከባቢ ሰንጥቆ በመግባት የበቀል በትሩን ሲያሳርፍ ሰነበተ። በጊዜያዊና ፕሮፖጋንዳ በተጫነው ድል ተኩራርቶና ልቡ አብጦ ለደጋፊዎቹና ለምዕራባውያን ቀላቢዎቹ “አዲስ አበባ በሁለት ሳምንት እንገባለን፣ የፋሺስቱን አብይን መንግስት መንግለን እናስወግዳለን” የሚል ተስፋ ሲግት ቆየ።

ለትግራይ ማህበረሰብ ልጅህን ስጠኝና አዲስአበባ ገብቼ ውለታህን እመልሳለሁ እያለ ተሳለቀበት። 27 ዓመት አዲስ አበባን ተቆጣጥሮ፣ የኢትዮጵያን ሰማይና ምድር በመዳፉ ጨብጦ ለትግራይ ማህበረሰብ ህይወት ትርጉም ያለው ለውጥ ያላመጣ ቡድን አከርካሪው ከተመታና መሪዎቹን በእስርና ሞት ካጣ በኋላ ምን ተዓምር ሊያመጣለት ከትግራይ ማህበረሰብ የልጅ ግብር እንደሚጠይቅ የሚያውቁት እንግዲህ እነሱ ናቸው።


አሁን ነገሮች ተቀያይረዋል። እንደፈለጉ መገስገስ የለም። አዲስ አበባ የማይደረስባት መንግስት ሰማያት ሆናለች። የጅቡቲን መስመር ይዤ የኢትዮጵያውያንን ጉሮሮ እዘጋለሁ የሚለው ቅዠትም ውሃ በልቶታል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተለይም ከሀሙስ ወዲህ በህወሀት መንደር ርዕደ መሬት መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች እየወጡ ነው። ድሮኗ ስራ ጀምራለች። ከአርብ አንስቶ የተመረጡ ዒላማዎችን እየቀጠቀጠች ነው። ዘመቻውን ከሚመሩት አዛዦች የተገኘው መረጃ እንደሚያረጋግጠው ሰሞኑን በህወሀት ጀሌ ሰራዊት ላይ የተወሰደው እርምጃ ቡድኑን ዳግም ለማንሰራራት እንዳይችል የሚያደርገው ነው። ለአብነትም ከጋይንት እስከ ጋሸና ባለው መስመር በትንሹ 10ሺህ የሚሆን ጀሌ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።
እስከእስታይሽ የተከማቸው የህወሀት ጀሌ አብዛኛው ተመትቷል። በክፍል ጦር ሂሳብ ከተሰላ ህወሓት አንድን ክፍለጦር ከ1600 እስከ 2000 ባለ የታጣቂ ቁጥር አደራጅቷል። ካለፈው ሀሙስ ምሽት አንስቶ በድሮን በታገዘ ጥቃት 9 የህወሀት ክፍለጦሮች ተደምስሰዋል። ኪሳራው በሰው ሃይል ከተሰላ በትንሹ ከ16ሺህ የሚልቅ ታጣቂ ተገድሏል። እንደሰማሁት የተረፈው ሃይል በላሊበላ አቅጣጫ ሸጡን ይዞ ወደትግራይ እየሸሸ ነው። ሆኖም ይህም ሃይል በህይወት ከትግራይ የሚደርስ አይመስልም። በየአከባቢው ህዝቡ እየጠበቀ እያስቀረው ነው። በእስታይሽና መርሳ ማዶ ስብሰባ የተቀመጠ የህወሀት አመራር ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ እዚያው ከስብሰባ እያለ በድሮን መመታቱም ታውቋል። ስለደረሰው ኪሳራ በሚቀጥሉት ቀናት የተሟላ መረጃ የሚደርሰን ይሆናል።
በሌሎች ግንባሮችም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። የአፋሩ ግንባር እንደተለመደው ለህወሀት ሃይል መቅሰፍት የወረደ ያህል ሆኖ ቀጥሏል። ህወሓት በወልቃይት በኩል ሰብሮ የሱዳኑን ኮሪዶር ለማስከፈት ፈጽሞ የማይሞከር እንደሆነ ተረድቶተታል። ለዚህም በአፋር በኩል የጅቡቲን መስመር በመያዝ ላይ ሙሉ ትኩረቱን ለማድረግ የፈለገ ይመስላል። ከሁለት ወር በፊት በጭፍራ በኩል ሰብሮ ሚሌ ለመድረስ ያደረገው ሙከራ ከተጨናገፈበት በኋላ ሰሞኑን ነፍሰጡር ሴቶችን ሳይቀር አሰልፎ በአፋር በኩል አዲስ ጥቃት ከፍቶ ነበር። ከሀሙስ ጀምሮ እስከ ትላንት ቅዳሜ አራት ጊዜ ሞክሮ በከፍተኛ ኪሳራ ተመትቶ ተመልሷል። በአንድ የአፋር ግንባር ብቻ ከ1ሺህ በላይ ሙት ተመዝግቧል። የሰውን ህይወት እንዲህ በቁጥር ሲገልጹት ቀላል ይመስላል። በማይጠብሪ፣ አደርቃይ፣ በደባርቅ ቀበሌዎች የህወሓት ሃይል ላይ የደረሰበትን ኪሳራ ከጨመርን ትግራይ ምን ሰው ተረፋት ብለን አብዝተን እንድንጨነቅ የሚያደርገን ነው። ያሳዝናል። ለአንድ ጨርቁን ጥሎ ላበደ ቡድን ተብሎ ይህ ሁሉ የህይወትና የቁስ ኪሳራ ልብን ይሰብራል።
በህወሀት መንደር አሁንም ሽለላውና ፉከራው አልበረደም። አሁንም አዲስ አበባን ልንቆጥስጠር ነው የሚለው ማደንዘዣ ዲስኩር ከትግራይ ማህበረሰብ ጆሮ ላይ ይጮሃል። የምዕራቡ መንግስታት በእርግጥ አሁን ላይ የመሬቱን እውነት የተረዱት ይመስላል። ዝምታቸውን ሰብረው ስለ ድርድር የሚጮሁት ያለምክንያት አይደለም። በየሳምንቱ ከጉድጓድ እየወጣ ፊቱን በቅባት ወዛም እያደረገ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚወራጨው ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጹ ላይ ሀተታ ዘ ፍርሃት ጽፎ አየሁት። ስለ ድርድር ጭንቅ ጥብብ ብሎታል። ድርድር ስለመኖሩ ሳናውቅ ስለአደራዳሪ ምርጫ ውስጥ ገብቶ ይፈተፍታል። ፍርሃት ሊሆን ቢችልም አብይን ልናስወግድ አንድ ሀሙስ ቀርቶናል፣ አዲስ አበባን ልንይዝ እንጦጦ አፋፍ ላይ ደርሰናል እያለ ለትግራይ ማህበረሰብ ሲደሰኩር ቆይቶ ፍሬቻ ሳያበራ ድንገት ታጥፎ ስለ ድርድር ሲያወራ መስማት አስገራሚ ነው። ከዚህስ በኋላ የትግራይ ማህበረሰብ ይህንን ቡድን ተከትሎ የገደል መንገዱን ይቀጥለው ይሆን?
ድርድር የሚባል የለም። ደብረጺዮን ለጉተሬዝ ደብዳቤ ጽፎ ድርድር እንፈልጋለን፣ አደራዳሪው ግን የአፍሪካ ህብረት መሆን የለበትም ሲል ተማጽኗል። ጌታቸውም በትዊተሩ ላይ የአፍሪካ ህብረትን ጥምብ እርኩስ እያወጣ የአደራዳሪ ምርጫ ዝርዝር ሲሰጥ ነበር። መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች፣ ባል ሳታገኝ ለሰርጓ ተጨነቀች፣ ማን ሊስምሽ ታሞጠሙጪያለሽ። የህወሀት መሪዎችን ከድርድር ዲስኩራቸው አንጻር የሚገልጹ አባባሎች ይመስሉኛል። ድርድር ሳይኖር የአደራዳሪ ምርጫ ውስጥ የገባው ህወሓት መሬት ላይ በጥሩ መደቆሻ እየተደቆሰ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። ቀደም ሲልም እንዳልኩት የህወሀት ጀምበር እየጠለቀች ነው። ከዚህ በኋላ ትንሳዔ የሌለው ሞት እንጂ እንደ ባለፈው አፈር ልሶ የመነሳት እድል አይኖርም። በነገራችን ላይ ድሮን ሲነሳ ሁሌም ከጆሮዬ ላይ የሚያቃጭልብኝ የሌ/ጄ ታደሰ ወረደ ቃለመጠይቅ ነው። ድሮን ምን ያህል እንደሚፈሩ በግልጽ የተናገረበት ነበር። ጀነራሉ በቁጭትና ንዴት ጥርሱን ነክሶ፣ ቡጢ ጨብጦ እንዲህ አለ “ድሮኗ ቀጠቀጠችን። መሳሪያዎቻችንን አነደደችብን። ያልጠበቅነው ነገር ነው”
እንግዲህ ድሮኗ ዳግም ስራ ጀምራለች።

More stories

«የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ» የዲፕሎማሲው መንገድ መቀየር !

August 5, 2021

መልስ የሚሻ ዜግነታዊ ጥያቄ – ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ

May 9, 2021

… ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ …

January 29, 2021

የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ 22

September 12, 2022

ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የገቢዎች ቢሮ ደረሰኝ ብቻ በመሸጥ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
EPLF said it supports Ethiopia’s territorial integrity and condemns US intervention in the Horn of Africa.
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2