Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንካሬ፣ ብልኃትና እምነት ሊኖረን ይገባል” ኬንያ
News

“በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንካሬ፣ ብልኃትና እምነት ሊኖረን ይገባል” ኬንያ

Ethioreview newsEthioreview news—November 17, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ የሚል እምነት እንዳላቸው የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ። “በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንካሬ እና ብልኃት (wisdom) እምነት ሊኖረን ይገባል ብለዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ራይቼል ኦማሞ ይህን እምነታቸውን የገለጹት፤ ከአሜሪካ አቻቸው አንቶኒ ብሊንከን ጋር ዛሬ ረቡዕ ህዳር 8 በናይሮቢ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። 

በሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መግለጫ የታደሙ ጋዜጠኞች ያነሷቸው ጥያቄዎች በዋናነት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ነበሩ። ጋዜጠኞቹ ካቀረቧቸው ጥያቄዎች ውስጥ “በኢትዮጵያ ያሉ ተፈላሚ ወገኖች ከተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ከዲፕሎማሲያዊ ግፊት ባሻገር ምን ሊደረግ ይችላል?” የሚለው ይገኝበታል። የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ወደ አዲስ አበባ ባቀኑበት ወቅት “እንደ ኢትዮጵያ ጓደኛ እና ጎረቤት” የተኩስ ማቆም ጉዳይን እንዳነሱ ጠቅሰዋል።

https://twitter.com/BekeleWoyecha/status/1461060256943980555?s=20
የተመድ ሰባዊ መብት ኮሚሽን በትግራይ ጄኖሳይድ ስለመፈጸሙ ምልክት አልታየም ማለቱ እየታወቀ ስለጄኖሳይድ ለወርውብ ጥያቄ “በሐቆች እና በሕግ ላይ አተኩረናል። ሐቆቹን እና የህጉን ትንታኔ ከተመለከትን በኋላ እንወስናለን” አንቶኒ ብሊንከን በጥያቄው መጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የተመረጡ ሕጋዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሉ እውቅናቸውን በአደባባይ አቅርበዋል

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ “ለዚህ ቀውስ መፍትሔ ለማግኘት ኢትዮጵያ ባላት አቅም እናምናለን። ተኩስ ማቆም ይቻላል ብለን እናምናለን። ሰብዓዊ  እርዳታን አስመልክቶ ያሉ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ሊሳኩ የሚችሉ ናቸው ብለን እናምናለን” ሲሉ ተደምጠዋል። “በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንካሬ እና ብልኃት (wisdom) እምነት ሊኖረን ይገባል። ምክንያቱም በስተመጨረሻ መፍትሔው የሚመጣው ከእነሱ ነው” ሲሉም ሚኒስትሯ አክለዋል። 

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

“ይህ ቀውስ ያበቃል ብለን እናምናለን” ያሉት ራይቼል ኦማሞ፤ ከዚያ በኋላ ኢትዮጵያ “ጠንካራ ሀገር፤ ጠንካራ አጋር እንደገና በቀጠናችን ሰላምን የምታረጋግጥ ሆና እንድትቀጥል” ሊደረግ ይገባል ያሉትን ጠቁመዋል። “እንደ ጎረቤት ማድረግ ያለብን መደገፍ፣ ማጽናናት እና ትክክለኛውን አቅጣጫ መጠቆም ነው” ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ “በኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ አንቁረጥ፤ በዚህ ቀውስ አዎንታዊ ሆነን በጽናት መቆም አለብን” የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው የኢትዮጵያ ጉዳይ፤ ኬንያ እና ሀገራቸውን እኩል በጥልቅ የሚያሳስብ እንደሆነ ተናግረዋል። ብሊንከን ውጊያው ባለፈው አመት በትግራይ ኋላም በአማራ ክልል ሲስፋፋ በአገሪቱ ዜጎች ለችግር መዳረጋቸውን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል። 

ግጭቱ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ጸጥታ ጭምር ስጋት እንደሆነ የገለጹት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ሁሉም ወገኖች ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ጥሪ አቅርበዋል። ብሊንከን፤ ህወሓት እና የኦሮሞ ነጻነት ጦር ወደ አዲስ አበባ ያደርጉታል ያሉትን ግስጋሴ እንዲያቆሙ አገራቸው እንደምትፈልግ ተናግረዋል።   “ጦርነቱ እንዲቆም [ተፈላሚ] ወገኖች በጠረጴዛ ዙሪያ ሲሰበሰቡ፣ የሰብአዊ እርዳታ በነጻነት ሲሰራጭ፤ የታሰሩ ሰዎች ሲፈቱ፣ ሁሉም ወገኖች ልዩነቶቻቸውን በሰላም እና ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ሲረባረብ ማየት እንፈልጋለን” ሲሉም የሀገራቸውን አቋም አስተጋብተዋል። 

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስትን ጨምሮ “ቅሬታ እና ስጋት ያላቸው ሁሉ”፤ በአገሪቱ ህገ መንግስት መሠረት በሚያደርጉት ንግግር፣ ውይይት እና ድርድር ልዩነቶች እና ግጭቶችን መፍታት እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ብሊንከን ገልጸዋል። “እንዳለመታደል ሆኖ በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ከፖለቲካዊ ሂደት ይልቅ ወታደራዊ መንገድን መርጧል” ሲሉ ተችተዋል።

በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል የዘር ማጥፋት (genocide) ተፈጽሟል ብለው ያምኑ እንደሆነ የተጠየቁት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “በሐቆች እና በሕግ ላይ አተኩረናል። ሐቆቹን እና የህጉን ትንታኔ ከተመለከትን በኋላ እንወስናለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ብሊንከን “ግፍ ሲፈጸም እና ሰዎች ሲሰቃዩ ተመልክተናል፤ አሁንም መመልከታችንን ቀጥለናል። ምንም እንበለው ምን መቆም አለበት። ተጠያቂነት መኖር አለበት። ተጠያቂነት እንዲኖር ቁርጠኞች ነን” ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ተደምጠዋል።

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይህን መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት ከኬንያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ብሊንከን በጋዜጣዊ መግለጫው፤ ኡሁሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በኢትዮጵያ በአካል በመገኘት አድርገውታል ያሉትን ጥረት አመስግነዋል። የኬንያው ፕሬዝዳንት ባለፈው እሁድ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

አሁሩ እና ብሊንከን ዛሬ በነበራቸው ውይይት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከባቢ አየር ለውጥ እንዲሁም የቀጠናውን ሰላም እና ጸጥታ የተመለከቱ ጉዳዮች እንደተዳሰሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የኬንያው ፕሬዝዳንት እና የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዚሁ ውይይታቸው፤ “የቀጠናውን ግጭቶች ለመፍታት እና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም በማምጣት ረገድ” ሊተባበሩ የሚችሉባቸውን ዕድሎች እንደፈተሹ መግለጫው ይጠቁማል።

ብሊንከን ከውይይቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸውም ይህንኑ አስተጋብተዋል። “ከኬንያ፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ እንዲሁም ሌሎች አጋሮች ጋር በቅርበት እየሰራን ነው” ሲሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ብሊንከን የአፍሪካ ህብረት ልዩ ልዑክ እና የአሜሪካው አቻቸው ጄፍሪ ፌልትማን፤ ውጊያ የገጠሙ “ወገኖች ያለቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ ግጭት እንዲያቆሙ ለመጫን” እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።  

ብሊንከን እንዳሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን ማስቆም እና በሰሜን ኢትዮጵያ የነፍስ አድን አቅርቦት በአፋጣኝ ለሚያስፈልጋቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ የሚቀርብበትን መንገድ ማመቻቸት ልዩ ልዑካኑ ከሚያደርጉት ጥረት መካከል ይገኙበታል። “ምንም እንኳ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሰራተኞቻችን ቁጥር ለመቀነስ ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ ብንወስድም፤ ኤምባሲያችን በእነዚህ ጥረቶች ሙሉ በሙሉ ተሳትፎ እያደረገ ነው” ብለዋል። 

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ቢሉም፤ የአሜሪካ ዜጎች ከኢትዮጵያ ለቅቀው እንዲወጡ አገራቸው ያስተላለፈችውን ጥሪ በናይሮቢም ደግመውታል። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስከ ቅዳሜ በአፍሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት ከኬንያ በተጨማሪ ወደ ናይጄሪያ እና ሴኔጋል ይጓዛሉ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ደሴ፣ ወልዲያና ቆቦ በቀናት ነጻ ይወጣሉ” ከድርድሩ ጦርነቱ እንዳይፈጥን
Killing of protesters in Sudan ‘utterly shameful’: UN rights chief
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2