Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው! – (ኢዜማ)
News

ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው! – (ኢዜማ)

Ethioreview newsEthioreview news—November 23, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሀገራችን በውስጥና በውጪ ጠላቶች የተደቀነባትን አደጋ በጀግኖች ልጆቿ መራር ትግልና መሰዋዓትነት በድል እንደመትወጣ ሙሉ እምነት አለው፡፡

ጠላቶቻችንን በደማቅ የአሸናፊነት ታሪካችን ብቻ ሳይሆን በብሩህ ተስፋችንም ጭምር ፊታቸው ጠቁሯል፡፡ በዚህም ዛሬም እንደ አራዊት እርስ በእርስ ሊያናክሱንና ሊያጠፋፉን፤ ማንነታችንን እና ክብራችንን ሊያዋርዱ ጦርነት ከፍተውብናል፡፡ ኢትዮጵያውያን በአሸናፊነት የምንቋጨው ጦርነት ላይ ብንሆንም ጦርነቱን በአጠረ ግዜ አለመጨረስ የሚያስከትለብን ፈተና ከባድ ይሆናል፡፡ የተራዘመ ጦርነት እንደ እሳት ነበልባል ሀገራችንን እና ህዝቦቿን ይበላል፡፡ ለውጭ ጠላቶቻችንን የበረታ ጫና ተጨማሪ ዕድል ይሰጣል፡፡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳቱም እጅግ የበዛ ነው፡፡ ስለሆነም መላው ኢትዮጰያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የህልውና ጦርነቱን በአጭር ግዜ ግቡን እንዲመታና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲቋጭ ዛሬ ነገ ሳትሉ የሚጠበቅባችሁን የዜግነት ግዴታ እንደምትወጡ አንጠራጠርም፡፡

More stories

በጁባ የተበጣጠሰው የጁንታው የሽብር መረብ

August 20, 2021

ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው! – (ኢዜማ)

November 23, 2021

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አጀንዳ ቀርጸው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተገለፀ

June 12, 2021

የዜግነት ግዴታችንን ስንወጣ የሀገራችን ፓለቲካ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ዘንግተን አይደለም፡፡ ያለን የፖለቲካ አመለካከት ልዮነቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተለይ በእንዲህ ያለ ግዜ ለሀገር ህልውና በጋራ መቆሙ ምርጫ የሌለው ግዴታችን በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ ሀገሬን እና ህዝቤን እወዳለሁ የሚሉ ሁሉ በተግባር የሚፈተኑበት ግዜው አሁን ነው፡፡ ሲተቹና አስተያያት ሲሰጡ የነበሩ ሁሉ የተናገሩትን ፈፅመው ሀቀኞች መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ቀን ደርሷል፡፡

ጥሬው ከብስሉ የሚለይበት ከንግግር ያለፈ ተጨባጭ ሥራ ሰርተን በታሪክ ፊት በእውነት የምንመዘንበት የታሪክ አጋጣሚ ከእጃችን ላይ ነው፡፡ ኢዜማ ለመላው የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ለመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሊያጠፋን የመጣውን ኃይል በህብረት ለመደምሰስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ አባላትና ደጋፊዎች ይህን ዘመቻ ሊያጠናከርና ሊደገፍ በሚችል አደረጃጀት ውስጥ በመቀላቀል፤ በገንዘብና በጉልበት ተግባራዊ ድጋፍ በማደረግ እውነተኛ ደጀን በመሆን፤ እንዲሁም የአካባቢያችንን ፀጥታ በንቃት በመጠበቅና አጥፊዎችን በአግባቡ ለሕግ በማቅረብ ብሎም ከተሳሳተ ፐሮፖጋንዳ ራሳችንን በመጠበቅ ይህን የፈተና ወቅት በፅናት እንድንወጣ አደራ እንላለን፡፡

በዚህ አሰቸጋሪ ወቅት ከፊት ሆነው እየተዋደቁ ያሉ ጀግኖችን ሁሉ በርቱ ታሪካችን ደማቅ ድላችንም አንፀባራቂ እንደሚሆን አትጠራጠሩ እያልን ወደ ግንባር የዘመቱት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለጉዳዩ ክብደት የሰጡት ትኩረት ተገቢ ነው እያልን በዚህ ሂደት ውስጥ የጸጥታውን መዋቅር በአንድ ወጥ አመራር አሰልፈው የሀገራችንን ድል ያፋጥኑታል ብለን እንተማመናለን፡፡ ስለዚህም ወጥ በሆነ የዕዝ ሰንሰለትና በተጠና ሀገር አቀፍ የውጊያ ስልት ሃገራችንን ለመጠበቅ ቆራጦች መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በዓለም አደባባይ ተገኝታችሁ ለምትወዷት ሀገራችሁ ሉዓላዊነት እያደረጋችሁ ላለው እጅግ የሚያስመካ ተግባር ኢዜማ ከፍ ያለ ክብር አለው፡፡ አንዳንድ የውጪ ሀገር መንግስታት እና ተቋማት ኢትዮጵያዊያን የሀገራችንን ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት እያደረግን ያለው ተጋድሎ ላይ እያሳረፉ ያሉትን ያልተገባ ጫና እንዲያቆሙ ድምጻችሁን አሰምታችኋል ፤ ድጋፋችሁን የሚሹ ወገኖቻችሁንም ሳትሰስቱ እየረዳችሁ ነው። ካለንበት ውስብስብ ችግር አንፃር ሲታይ እናት ሀገራችሁ ከመቼውም ጊዜ በላይ የእናንተን አቅም እና ድጋፍ አሁንም ትሻለች። ያለእናንተ አስተዋፅዖ የተሟላ ድል ሊገኝ እንደማይችል በተግባር ተረድተናል፡፡ ስለሆነም የምዕራባውያንን የተዛባ አመለካከት በማጥራት እንዲሁም ሊፈጠር የሚችለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቅረፍ በሚያስችል ደረጃ የተደራጀ እና ወጥነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ ከወትሮው በላቀ ሁኔታ በያላችሁበት የዓለም ጥግ እራሳችሁን እንድታዘጋጁ አደራ እንላለን፡፡

በመጨረሻም ከልዩነቶቻችን፣ አለመግባባቶቻችን እና የጎደሉን ነገሮች በፊት ኢትዮጵያ ሃገራችን ትቀድማለች፡፡ በተለይ የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት የሀገራችን ህልውና ቀዳሚ ነው። የመጣብንን የጋራ ጠላት በጋራ መክተን የሀገረ መንግስቱን ቀጣይነት ካረጋገጥን በኋላ ልዩነቶቻችንን ለመፍታት እና ቅሬታዎቻችንን ለማከም በጠረጴዛው ዙሪያ እንቀመጣለን። በዛም ወቅት ሀገራችንን የመፍረስ ስጋት ጫፍ ላይ ያደረሳት የፖለቲካ ስርዓት እና አካሄድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይመለስ መስራት ሀላፊነታችን ይሆናል፡፡ አሁን ላይ ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው! ይህንንም ስናደርግ እንደ ሀገር አብሮ መኖራችንን በማያቆሽሽ እና የወደፊት አብሮነታችንን በማይጎዳ ሁኔታ እንዲሆን አሁንም አበክረን እናሳስባለን፡፡

አሁን ያለንበት ወቅት ሁሉን አቀፍ አርበኝነትን የሚጠይቅ መሆኑን ግምት ውስጥ በመክተት የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ህዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ አባላት እና ደጋፊዎቹ ግንባር ድረስ በመዝመት፣ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመስጠት እና ሌሎችንም ተግባራት በመከወን የሀገርን ህልውና የማረጋገጥ ስራ ለመስራት ውሳኔን አስተላልፏል፡፡

ህዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?
POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
China wants to control what apps citizens use. But will Google play ball?
ኢትዮጵያ የመላውን ጥቁር ሕዝብ ትግል እያካሄደች ነው
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2