Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ የተሰጠ መግለጫ
News

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ የተሰጠ መግለጫ

Ethioreview newsEthioreview news—November 1, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የህወሃት ከሃዲ ጁንታ ስልጣኔን አሳጥተውኛል ብሎ በሚያስባቸው ወገኖችና መላ ኢትዮጵያውያን ላይ ጠንካራ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ይፋዊ ጦርነት ከከፈተብን አንድ አመት ሞላው። ከሃዲው የትህነግ ጁንታ የዛሬ ዓመት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከ20 ዓመታት በላይ በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ሲጠብቀው በኖረው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሃይላችን ላይ ታሪክ የማይረሳው ክህደት ከፈጸመ በኋላ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ሁሉንም አይነት ጥቃት ሲፈጽም ቆይቷል።

የትህነግ አሸባሪ ቡድን በአሁኑ ወቅት ያለሃፍረት ኢትዮጵያ ሳትፈርስ ነጻ ሃገረ ትግራይን መመስረት አይቻልም የሚል ግልጽ አላማ አንግቦ እየተፋለመን ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያግዙትን የውስጥና የውጪ አሸባሪዎችና ታሪካዊ ጠላቶቻችንን አስተባብሮ በሁሉም አቅጣጫ ውጊያ ከፍቶብናል።

አሸባሪው ሃይል በክልሉና ከክልሉ ውጪ የሚኖረውን የትግራይ ህዝብ በዘረኝነትና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማስከርም በወረራ በተቆጣጠራቸው የአማራና የአፋር አካባቢዎች አስከፊ ግድያና ዝርፊያ እየፈጸመ ነው።በዚህ ምክንያት በኛ ዘመን እጅግ የምንወዳትና እንደ አይናችን ብሌን የምንሳሳላት ሃገራችን የተባበረ ጥቃት ሰለባ ሆናለች።

More stories

በጁባ የተበጣጠሰው የጁንታው የሽብር መረብ

August 20, 2021

ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው! – (ኢዜማ)

November 23, 2021

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አጀንዳ ቀርጸው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተገለፀ

June 12, 2021

እናም ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን በመቆም ሃገራችንን መታደግ የግድ ከሚለን የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ነን። እንደ ሃገርም ቁርጠኛና የተናበበ አመራር ከምንሰጥበትና የተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ ከምናረጋግጥበት የትግል ምዕራፍ ውስጥ እንገኛለን።ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል የገጠሙኣትን የህልውና አደጋዎች በሙሉ የቀለበሰችው በህዝቦቹኣ ጠንካራ አንድነትና የተባበረ ክንድ ነው።

በዚህ ዘመን ኢትዮጵያን ካልዘረፍኳትና እንደወትሮው ረግጬ ካልገዛኋት ትፍረስ በሚል ስግብግብ ፍላጎት ክህደት የፈጸመብንና ጦርነት የከፈተብንን የህወሃትን ወራሪ ጁንታ የምንሰብረውና የምንቀብረውም ከታሪካችን በወረስነው በዚሁ የጀግንነትና የአንድነት መንፈስ ብቻ ነው።

በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸባሪው የህወሃት ጁንታ የከፈተብን ሁለገብ ጥቃት የደረሰበትን ደረጃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሁለንተናዊ አቅሙን ሃገራችን የተጋረጠባትን አደጋ ለመቀልበስ በሚያስችሉ እርምጃዎች ላይ ለማዋል ወስኗል።

የአዲስ አበባ አበባ ከተማ አስተዳደር የህወሃት ዘራፊ ጁንታ በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ቀጥተኛ ወረራ ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ አመራሩን፣ ባለሃብቱንና መላ የከተማውን ነዋሪዎች በማስተባበር ለመከላከያ ሃይላችንና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል 4 ቢሊዮን ብር ያህል ሃብት በማሰባሰብ ለፌደራልና ለክልል መንግስታት አስረክቧል።

የከተማ አስተዳደራችን ዛሬም በየግንባሩ በጽናትና በጀግንነት የሚፋለሙት የመከላከያ ሰራዊታችንና መላ የጸጥታ ሃይሎቻችን ጠንካራ ደጀን ከመሆን ባሻገር አመራሩንና ህዝቡን በማስተባበር በግንባር በመሰለፍ ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት አብሮአቸው ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል።

የከተማ አስተዳደሩ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ በአጭር ጊዜ ለመቀልበስ ከህዝቡና ከሁሉም የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በቁጭትና በጥድፊያ መንፈስ እንደሚሰራም በዚሁ አጋጣሚ ይገልጻል።

በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስትና ዓራት ዓመታት የታየውን ሁለንተናዊ ለውጥ የፈጠሩት በባዶ እጃቸው አደባባይ ወጥተው የህወሓትን የአፈና ታንኮች የገጠሙ ፍትህና ዕኩልነት የጠማቸው ወጣቶችና ጭቆና የበረታባቸው ዜጎች ናቸው። የህወሓት አሸባሪ ሃይል ዛሬ በየአንዳንዳችን ደጀፍ ለመድረስ እየማሰነ ያለው ይህንኑ ነባራዊ ዕውነት ለመመለስ ነው።

በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች በመቶ ሺዎች ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ሰላምና ጸጥታ ከመጠበቅ በተጨማሪ በገፍ የመከላከያ ሃይላችንን በመቀላቀል የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ ከመቼውም በላቀ ቁርጠኝነት ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማትና የውጊያ ግንባሮች እንዲተሙም አስተዳደራችን ጥሪውን ያስተላልፋል።

የከተማው ነዋሪዎችም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በመኖሪያ አካባቢዎች ደረጃ በመደራጀትና ከሁሉም የጸጥታና የአስተዳደሩ አካላት ጋር በመናበብ ሰላምና ጸጥታቸውን በንቃትና በብቃት እንዲጠብቁ ይጠይቃል።

የከተማው የመኖሪያ ቤት አከራዮች፣ ሆቴሎችና ሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቃማት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ሰርጎ ገቦችን ለመቀጣጠር የሚፈጸሙ መደበኛና ድንገተኛ ፍተሻዎችን ከመደገፍ በተጨማሪ ተገልጋዮቻቸውን በቅርበት እንዲከታተሉም የከተማ አስተዳደሩ ያሳስባል።

የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ በህወሓት አስተባባሪነት በግንባር የሚፈጸመውን የሽብር ድርጊት በከተማችን ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ማናቸውም አይነት እንቅስቃሴዎች ላይ ቋሚ ፣ ህጋዊና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳውቃል።

በመጨረሻም የከተማችን ነዋሪዎችና መላው ኢትዮጵያውያን በዚህ ወሳኝ ወቅት አንድ ሆነው በመቆምና ሁለገብ አቅማችሁን በማስተባበር የሽብር ቡድኑን ህልፈት ለማፋጠን የሚያስችል ፈጣንና ወሳኝ እርምጃ እንድትወስዱ የከተማ አስተዳደራችሁ ጥሪውን ያስተላልፍላችኋል።

ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Ethiopian Government Says TPLF Killed Over 100 Young Residents of Seized City
በራማ በኩል የኤርትራ ልዩ ሃይል ወደፊት ማጥቃት ወደ አድዋ ጉዞ ጀምሯል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2