Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ሀገራት አሸባሪው ትህነግ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ -“ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የፈጸመው ወንጀል ይጣራ”
News

የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ሀገራት አሸባሪው ትህነግ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ -“ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የፈጸመው ወንጀል ይጣራ”

Ethioreview newsEthioreview news—February 21, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አሸባሪው ህወሃት ለፈፀመው ግፍ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት አስታወቁ። በአፍሪካ ሕብረትና በኢጋድ በኩል ትህነግንና ሸኔን በሽብርተኛነት እንዲፈረጁ እየተሰራ መሆኑ መሰማቱ ይታወሳል።

በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ዛሬ ባወጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አሸባሪው ህወሃት በአፋርና በአማራ ክልሎች ለፈፀማቸው ግፎች እርምጃ እንዲወሰድበት እንዲያደርጉ ጠየቁ።

ሁለቱ ህብረቶች የሰው ልጆች መብቶችን በሚጥሱ ኃይሎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የግንኙነታቸውን መርሆ ማክበር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የህወሃት አመራሮች ኢትዮጵያን ለ30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገዛዝ ስር እንዳቆዩዋት በኋላም በህዝብ ታቃውሞ ከስልጣን ሲባረሩ ወደ ትግራይ በመሸሽ ህዝቡን መሸሸጊያ እንዳደረጉት መግለጫው አትቷል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ይህ ቡድን የሰዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የሀሳብ ብዝሃነትን ጨምሮ መሰረታዊ የሰው ልጆች መብቶችን ሲረግጥ እንደቆየም ጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ በቅርብ ጊዜ እንኳን መንግስት ያደረገውን የተኩስ አቁም በመጣስ በአፋርና በአማራ ክልሎች ወረራ ማካሄዱን ያስታወሰው መግለጫው በወረራውም አሰቃቂ ግፎችን መፈፀማቸውን አብራርቷል።

በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ አስገድዶ መድፈር፣ በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል ብሏል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የሽብር ቡድኑ ለእንስሳት እንኳን የሚራራ ልብ እንዳልነበረው በመጥቀስ እንስሳትን ከአካባቢው አርሶ አደር ከመዝረፉም ባለፈ በጥይት እየተኮሰ መግደሉን አብራርቷል።

የዳያስፖራ ማህበራቱ መግለጫ አሰቃቂ ግፎችን የፈፀመው አሸባሪው ህወሃት ተጠያቂ መሆን እንዳለበት በመጥቀስም የሽብር ቡድኑ የፈፀማቸውን ማስረጃዎች እንደሚከተለው አቅርቧል፦

  • በአማራና አፋር ክልሎች በሚኖሩ ሴቶችና ህጻናት ላይ በቡድን አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ፆታዊ ጥቃት አድርሷል፤ በዚህም ሴቶችና ህጻናት ከፍተኛ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ አንዳንዶችም በደረሰባቸው ጉዳት የተነሳ ራሳቸውን እስከማጥፋት ደርሰዋል።
  • በሁለቱ ክልሎች በርካታ ሰላማዊ ዜጎችን መግደሉን በዓለም አቀፍ ገለልተኛ የምርምራ ተቋማት ተረጋግጧል።
  • በአማራ ክልል ብቻ 40 ሆስፒታሎችን፣ 453 ጤና ጣቢያዎችን፣ 466 የግል ክሊኒኮችን በአፋር ክልል ደግሞ 57 የጤና ተቋማትን ከማውደሙ ባሻገር ህዝቡ የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ የማድረግ ወንጀልም ፈጽሟል ነው ያለው መግለጫው።
  • በሽብር ቡድኑ ጥቃት ከ7 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች በመውደማቸው ከ 3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዲርቁና የመማር መብታቸው እንዲጣስ አድርጓል ብሏል።
  • በትግራይ ክልል እያንዳንዱ ነዋሪ በአስገዳጅ ሁኔታ ልጆቹን ወደ ጦርነት እንዲልክ በማስገደድ ታዳጊዎችን ወደ ጦርነት መማገዱን እንዲሁም በከፈተው ጦርነት ምክንያት የትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ እንዳያገኝ ማድረጉን ነው የጠቀሰው።
  • በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ማህበራት አሸባሪው ቡድን ያደረሳቸውን አሰቃቂ ውድመቶች አውግዞ የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረቶች የሽብር ቡድኑን ተጠያቂ እንደያደርጉት ጥሪ አቅርቧል።

አሸባሪ ቡድኑ ወደ አገዛዝ ከመጣበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ለፈጸማቸው ግፎችም ገለልተኛ ምርመራ በማካሄድ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ጠይቋል።

ኢፕድ

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ሹመት ጸደቀ
ጀርመን 80.6 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገባ፤ ትህነግ ሰላማዊ ዜጎችን ሰላም እየነሳና ተቋማት እያወደመ ስለሆነ እንዲወገዝ ተጥይቋል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2