Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  law  የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ
law

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ

Ethioreview newsEthioreview news—February 9, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡

እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍርድ ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡

More stories

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ

February 9, 2022

በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡

በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍርድ ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ” ጉባዔ እንደሚገልጸው በተለያየ ደረጃ የፍርድ ቤቱ አገልግሎትም ሆነ ተደራሽነት እያደገ የመጣ ለመሆኑ ፍርድ ቤቱ በገለልተኛ የጥናት ተቋም የሰራው የሕዝብ አስተያየት ሰርቬይ “public perception survey” አመልክቷል፡፡

ይህም ሆኖ የዳኝነት ዘርፉ አገልግሎት በርካታ ሰብዓዊ ግብዓቶች ያሉበት የስራ ዘርፍ ከመሆኑ አኳያ እና እንደሌሎች ተቋሞቻችን ሁሉ ተግዳሮቶቹ በርካታ በመሆናቸው ስራችን በውሱን ዓመታት የሚጠናቀቅ ሳይሆን እያደገ የሚሄድ ውጤት እያመጣ ያለ ዘርፍ ነው፡፡

ፍርድ ቤት እንደ ሶስተኛው የመንግስት ዘርፍ አገራችን በጦርነት እና በተለዋዋጭ የፖለቲካ ዓውድ በማለፍ ላይ የምትገኝ ቢሆንም በሃገራችን ዘላቂ ልማት እና ሰላም እንዲረጋገጥ የህግ የበላይነት በማክበርና በማስከበር ረገድ የሚጫወተው ሚና እየተጠናከረ እንዲሄድ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸው እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት አለን፡፡

ለዚህ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የፕሬስ መግለጫ ምክንያት በቀን 28/4/2014ዓ.ም ዐቃቢ ሕግ ክስ እንዲነሳ ለፍ/ቤት ማመልከቻ በማቅረብ ክስ የተነሳባቸው ሶስት መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች አካሄድ ላይ የፍ/ቤቶች ሚና ምን እንደነበረ ሕዝቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ ነው፡፡

ግለሰቦች መብታቸውን ለመጠየቅ ወደ ፍርድ /ቤት የሚያመጧቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮችም ሆኑ በዐቃቤ ሕግ በኩል የሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮች ሁሉ በፍ/ቤቶቻችን እና በዳኞቻችን በልዩ ጥንቃቄ የሚታዩ ናቸው፤ መታየትም አለባቸው፡፡

በሌላ በኩል ግን የህዝብ ፍላጎት ያለባቸው ጉዳዮች “በሕዝብ እይታ ውስጥ ያሉ” በማለት በተቻለ ቅልጥፍና እንዲታዩ፣ ሂደታቸውም የስነ-ስርዓትም ሆነ ዋና ሕጎችን ተከትለው እንዲከናወኑ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የአመልካቾች የምርጫ ጥያቄን በተመለከተ፣ የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ እና የሕክምና አገልግሎት ጥያቄ በተመለከተ፣ እንዲሁም የምስክሮችን ከመጋረጃ ጀርባ ይሰሙ/ አይሰሙ የሚሉትን እና ሌሎች አስቸጋሪ ክርክሮችን ዳኞቻችን ተገቢ ነው ያሏቸውን ብይን አሳርፈውባቸዋል፡፡

እነዚህ እና መሰል ጉዳዮች ለጥናት እና ምርምር እንዲሁም የሕግ ፍልስፍና ማደግ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው፡፡ ፍ/ቤቱ በነጻነት የመስራት ደረጃ ላይ ለመድረሱ አመላካች ውሳኔዎች ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡

ታህሳስ 28/2014 ዓ.ም በሙሉ ወይንም በከፊል በተከሳሾች ላይ በሶስት መዝገቦች የቀረቡ ክሶችን እንዲቋረጡ የፍትህ ሚኒስትሩ ለሚመለከተው ችሎት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትለው ተስተናግደዋል፡፡

ጉዳዮቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

– በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ ጀዋር ሲራጅ መሀመድ (በድምሩ 20 ተከሳሾች)

– በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተካሾች እነ እስክንድር ነጋ (በድምሩ 7 ተከሳሾች) እንዲሁም

– በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (በድምሩ ስድስት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ) የሚመለከቱ ክሶች እንዲቋረጡ ጥያቄ ቀርቧል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሕገ-መንግስት እና ሽብር ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት የፍትህ ሚኒስትሩን ማመልከቻ በመመርመር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(3)ሠ መሰረት ክሱን ያነሱ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሾቹ እንዲለቀቁ “ተከሳሾች በሌላ ወንጀል የማይፈለጉ ከሆነ” ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ለማረሚያ ቤት አስተላልፏል፡፡

አሁን በስራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት ከሳሽ ዐቃቢ ሕግ በተለያዩ ምክንያቶች ክሱን መቀጠል እንደማይፈልግ ሲያመለክት ፍ/ቤቱ የክስ ይቋረጥ ጥያቄውን በመቀበል በእስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ የታዘዘ መሆኑ ሕጋዊ አሰራር መሆኑ ግንዛቤ እንዲፈጠር ይህ የፕሬስ መግለጫ ወጥቷል፡፡

የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት

L aw
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኢኮኖሚው በፈተናዎች ውስጥ እድገት ማሳየቱ
Putin issues dire threat of nuclear war in Europe if he doesn’t get his way
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
law

የአዲስ አበባ የከንቲባ ፅ.ቤት ፕሮቶኮልን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌብነት ተከሰው ተፈረደባቸው

July 23, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2