በሳዑዲ አረቢያ እና ኢራን በሞት ፍርድ የሞት ቅጣት የሚፈጽምባቸው ሰዎች ቁጥር እአአ 2021 ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በ18 አገራት 579 የሞት ቅጣቶች ተግባራዊ ሆነዋል ያለ ሲሆን፤ ይህም ከቀደመው ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብሏል።
ኢራን 314 ሰዎችን በሞት በመቅጣት ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበባት አገር ሆናለች። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ደግሞ በሞት የተቀጡ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ 65 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
አምነስቲ በዚህ ሪፖርቱ ላይ ቻይና አለመካተቷን ገልጿል። ቻይና የሞት ፍርድን አገራዊ ምስጢር አድርጋ ስለምትይዝ በአገሪቱ በሞት የተቀጡ ሰዎች አሃዝን ማወቅ ባይቻልም ቤይጂንግ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በሞት እንደምትቀጣ ይገመታል።
አምነስቲ ከቻይና በተጨማሪ በሰሜን ኮሪያ እና ቬትናም በተመሳሳይ የሞት ፍርድ ምስጢራዊ ስለምታደረግ በቀጠናው በሞት የተቀጡ ሰዎችን ዝርዝር ማወቅ አዳጋች ነው ብሏል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ እንደ ኢራን ባሉ አገራት በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ ያሳየው ከአደኛ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ የሚባሉ ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ መሆኑን ገልጿል።
እአአ 2017 ላይ ኢራን 23 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን እአአ 2020 ላይ ቁጥሩ በአምስት እጥፍ አድረጎ 132 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል።
በሳዑዲ አረቢያ ደግሞ በሞት የተቀጡ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ140 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አምነስቲ ገልጿል። በሳዑዲ በዚህ ዓመት መጋቢት ወር በአንድ ቀን ብቻ 81 ሰዎች በሞት መቀጣታቸውን ገልጿል።
ከእነዚህ ሁለት አገራት በተጨማሪ የኢትዮጵያ በጎረቤት አገራት በሆኑት በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን እንዲሁም በየመን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል።
- 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚 𝐑𝐞𝐚𝐟𝐟𝐢𝐫𝐦𝐬 𝐖𝐓𝐎 𝐀𝐜𝐜𝐞𝐬𝐬𝐢𝐨𝐧 𝐂𝐨𝐦𝐦𝐢𝐭𝐦𝐞𝐧𝐭 𝐚𝐭 𝐆𝐞𝐧𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐮𝐧𝐜𝐢𝐥 𝐌𝐞𝐞𝐭𝐢𝐧𝐠State Minister of Finance, Eyob Tekalign, delivered a strong statement at the… Read more: 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚 𝐑𝐞𝐚𝐟𝐟𝐢𝐫𝐦𝐬 𝐖𝐓𝐎 𝐀𝐜𝐜𝐞𝐬𝐬𝐢𝐨𝐧 𝐂𝐨𝐦𝐦𝐢𝐭𝐦𝐞𝐧𝐭 𝐚𝐭 𝐆𝐞𝐧𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐮𝐧𝐜𝐢𝐥 𝐌𝐞𝐞𝐭𝐢𝐧𝐠
- ❝የአሸባሪውና ወራሪ የመጨረሻ ግብዓተ መሬት የምንፈፅምበት ጊዜ ሩቅ አይደለም❞ ጄነራል ብርሃኑ ጁላ❝እኛ የምንዋጋው ኢትዮጵያን ለማዳን ነው፤ የሕልውና ጦርነት ነው፤ ጠላት የሚዋጋው ኢትዮጵያን ሊያፈራርስ… Read more: ❝የአሸባሪውና ወራሪ የመጨረሻ ግብዓተ መሬት የምንፈፅምበት ጊዜ ሩቅ አይደለም❞ ጄነራል ብርሃኑ ጁላ
- ❝በሴራ ልክፍት እየናወዙ የለውጡ አካል ሆኖ መቀጠል አይቻልም!❞ የአማራ ብልጽግና ፓርቲየአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ባስተላለፈው መልዕክት ❝በሴራ ልክፍት እየናወዙ… Read more: ❝በሴራ ልክፍት እየናወዙ የለውጡ አካል ሆኖ መቀጠል አይቻልም!❞ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ
- ❝ሰርጎ ገቦችን የማጋለጡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል❞ የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮአሸባሪው ትህነግ በሰርጎ ገቦች በኩል ሕዝብን ለመረበሽ የሚያደርገውን ጥረት ሕዝብና የጸጥታ ኀይላችን… Read more: ❝ሰርጎ ገቦችን የማጋለጡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል❞ የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ






