Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በአዲስ አበባ 303 አሻባሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
News

በአዲስ አበባ 303 አሻባሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Ethioreview newsEthioreview news—July 23, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያው የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበሩ 51 ጽንፈኛ የፋኖ አባላት፣ 174 የህወሓት ጁንታ ቡድን አባላት፣ 98 የሸኔ ቡድን አባላት፣ በከተማው ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ 100 ተጠርጣሪዎች እና 31 የአልሸባብና የአይ.ኤስ.ኤስ አባላትን በድምሩ 454 ተጠርጣሪዎች ሊያደርሱት ያሰቡትን የሽብር ጥቃት እና ትርምስ ቀድሞ በማክሸፍ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ከፌደራል የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:-

የህወሃት ጁንታ ቡድን አባላት፣ የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ)፣ የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ (ጉህዴን) እና የኦነግ-ሸኔ አሸባሪዎች ተደራጅተውና ተቀናጅተው በጋምቤላ ክልል በጋምቤላ ከተማና በአካባቢው እንዲሁም በጊምቢና ደምቢ ዶሎ ከተማ በቅርቡ ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ ማድረጋቸውና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከአካባቢው የፀጥታ ኃይል እና ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት በወሰዱት እርምጃ እኩይ ሴራቸው መክሸፉ ይታወቃል፡፡

ግብረ-ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በርካቶች ማርኮ 137 የሽብር ቡድን አባላትን ደምስሷል፡፡ በዚህም በክልሉ የነበረው የፀጥታ ችግር በአሁኑ ወቅት ተወግዶ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ተደርጓል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሽብር ቡድኖቹ ሽንፈታቸውን ለመቀበል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊንቢ ከተማ አካባቢ በሚገኝ ቶሌ ቀበሌ ላይ ሰላማዊ በሆኑና ምንም በማያውቁ ንፁሃን ህፃናትና ሲቪሎች ላይ ወዲያውኑ ዘግናኝ ጉዳት ማድረሳቸውና በርካቶችንም መግደላቸው ይታወሳል።

ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ ክልል የፀጥታና ደህንነት አካላት የተውጣጣው የጋራ ግብረ-ኃይል ከሰኔ 07 እስከ ሐምሌ 07 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ዘመቻ ከ153 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላትን ደምስሶ፣ ከዘጠኝ መቶ በላይ ማርኮና በቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ ይገኛል፡፡

በዚህም ዘመቻ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ይጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎች፣ ብዛት ያላቸው ጥይቶችና የጥይት መጋዘኖች፣ ወታደራዊ ትጥቆችና አልባሳት፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ንብረቶችም ተይዘዋል፡፡

በሌላ በኩል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር አሸባሪ የጁንታ ቡድኑን ሲፋለሙ እና ለፀጥታ አካላቱ የኋላ ደጀን ሆነው እገዛ ሲያደርጉ የነበሩ የፋኖ አባላት ዛሬ ላይ በክልሉ ለተገኘው ሰላምና ፀጥታ ድርሻቸውን ያበረከቱ ሲሆን ይህንን መልካም ተግባር አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

ሆኖም ፋኖን ሽፋን በማድረግ በህቡዕ የተደራጁት ጽንፈኛ የፋኖ አባላት ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በመታጠቅ እና በህግ-ወጥ ተኩስ ሁከት ለማስፋፋትና ክልሉ ወደ ለየለት ብጥብጥ እንዲገባ ቢሞክሩም በፀጥታ ኃይሉ እና በክልሉ ህዝብ ከፍተኛ ጥረት ሙከራው ሊከሽፍ ችሏል።

የፅንፈኛው ፋኖ ቡድን አባላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከፖሊስ ተቋማት ዕውቅና ውጪ ወጣቶችን በመመልመል፣ በድብቅ በማሰልጠንና የጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ህዝቡ በፍርሀት እንዲሸበር ከማድረግ ባለፈ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን በሚዲያ እያሰራጩ እንዲሁም የንፁሃን ዜጎችን ህይወት እያጠፉ፣ ከቤት ንብረታቸው እያፈናቀሉና እየዘረፉ የነበሩ ከክልና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ከድተው የተያዙ፣ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጣቸውና በቁጥጥር ስራ ሳይውሉ የቆዩ እና በግድያ ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ በጥቅሉ 5 ሺህ 804 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

ከዚህ ባሻገር በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በህቡዕ እየተሰባሰቡና እየተደራጁ እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ውስን ፅንፈኛ የዲያስፖራ አባላት ጋር ተደራጅተውና ተቀናጅተው ለእኩይ ዓላማቸው ማስፈፀሚያ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ባሰባሰቡት ከፍተኛ ገንዘብ ትጥቅ በማሟላት፣ የጦር ሜዳ እና የሽምቅ ውጊያ ካርታ ስልጠና በመውሰድና ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በድብቅ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማስገባት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በውጭ ሀገር የሚገኙ ጽንፈኛ ሚዲዎችን በመጠቀም ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ፣ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱና በአማራ ክልል እና በፌደራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀምና መንግስትን በኃይል ለመጣል ሲያሴሩ በነበሩ ጽንፈኛ የፋኖ አባላት ላይ የአማራ ክልልና የፌደራል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል በጋራ ባደረጉት የተቀናጀ ኦፕሬሽን 14ቱ (አስራ አራቱ) በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ ሚስጥራዊ ሰነዶቻቸው ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

በዚህም በክልሉ የነበረውም የፀጥታ ችግር በአሁኑ ወቅት ተወግዶ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ተደርጓል።

በሌላ በኩል የጋራ ግብረ ኃይሉ በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያው ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ወደ ከተማው ሰርገው በመግባት የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበሩ 51 ጽንፈኛ የፋኖ አባላት፣ 174 የህወሓት ጁንታ ቡድን አባላት፣ 98 የሸኔ ቡድን አባላት፣ በከተማው ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ 100 ተጠርጣሪዎች እና 31 የአልሸባብና የአይ.ኤስ.ኤስ አባላትን በድምሩ 454 ተጠርጣሪዎች እግር በእግር በመከታተል ሊያደርሱት ያሰቡትን የሽብር ጥቃት እና ትርምስ ቀድሞ በማክሸፍ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ 50 በተለያዩ የዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችም ከተለያየ የዘረፉት ንብረት ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

እስከአሁን የተገኘው ውጤትም ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ባደረገው ቀና ትብብር ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ የጀመረውን የተቀናጀ የህግ ማስከበር ዘመቻውን የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እያስታወቀ ህብረተሰቡ ጥቆማውንና ትብብሩን እንደተለመደው በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን የተከተለ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለመቀበል የገንዘብ ሚኒስቴር ዝግጁ ነው”
የአማራ ክልል በቀጣይ አምስት አመት ከ26 ሺህ በላይ የእርሻ ትራክተር እና 300 ኮምባይነር ያስገባል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2