Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ኢትዮጵያ በስንዴ ነዶ …
News

ኢትዮጵያ በስንዴ ነዶ …

Ethioreview newsEthioreview news—August 7, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች በመሆኑ በዘንድሮው የምርት ዘመንም ከፍተኛ ውጤት ይጠበቃል። በተደጋጋሚ እንደተነገረው ለጎረቤት አገራትም ስንዴ መሸጥ ይጀመራል። ዛሬ ማለዳ በመንግስት ሃላፊዎችና መሪዎች አማካይነት ይፋ የሆነውና በምስል የታገዘው የስንዴ ነዶ የቀና ልብ ባለቤት ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን የሰንበት የተስፋና የምስጋና ምንጭ ሆኖላቸዋል።

በ2015 ዓ.ም ከመኸር እርሻ ምርት ስንዴን ጨምሮ ከሁሉም የሰብል ምርቶች በአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደርና አርብቶ አደሮች ብቻ አራት ሚሊየን ኩንታል ለማምረት መታቀዱ ተሰምቷል። ይህ ቅዠት እንዳልሆነ የሚያሳዩት መረጃዎችና ማረጋገጫ ናቸው። ከሁሉም በላይ ግን ከማሳው ወደ ቤታቸው ለመሄድ የሚችገሩት አርሶ አደሮች ህያው ምስክሮች ናቸው።

ከመኸር በተጨማሪ በበልግ ወቅት እርሻ ደግሞ ሁለት ሚሊየን ሔክታር በማልማት 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የዘርፉ ተቋማት መረጃ ያስረዳል። በበጋ መስኖ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተያዘው ሀገራዊ ዕቅድ ለመተግበር በበጋ መስኖ 36 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚመረት ይፋ ሆኗል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕመድ የማይታረሱ መሬቶችን በማረስ በኩታ ገጠም እርሻ በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ሥራዎችን እየተሰራ መሆኑንን ቀደም ባሉት ዓመታት መናገራቸው ይታወሳል። ከስር አዲስ ዘመን የግብርና ሚኒስትርን ጠቅሶ የሚከተለውን ጽፏል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

በግብርናው ዘርፍ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ከማስፋት ባለፈ አዳዲስ ሃሳቦችን በመተግበር የተሻለ ውጤት ለማምጣት ታቅዷል

በግብርናው ዘርፍ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ከማስፋት ባለፈ አዳዲስ ሃሳቦችን በመተግበር በ2014/15 የምርት ዘመን ከግብርናው የሚጠበቀውን ፍላጎት ለማሳካት መታቀዱን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ።

በ2013/2014 የምርት ዘመን በግብርናው ዘርፍ የተመዘገበው ውጤታማ አፈጻጸም በዘርፉ ላይ መነቃቃት እንዲፈጠር ማድረጉም ተገልጿል።

የግብርና ሚኒስቴርና የክልል ግብርና ቢሮዎች የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 ዓ.ም ዕቅድ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን በዚህ ወቅት ዘርፉ ከኢንዱስትሪ፣ ከምግብና ከኤክስፖርት አኳያ ከፍተኛ ፍላጐት እንደሚቀርብበት ጠቅሰዋል፡፡

ግብርናው የእነዚህን ዘርፎች ፍላጎት እንዲመልስ በቂ ዕውቀት የተላበሰና ሙያውን የሚረዳ አመራር ይጠይቃል ብለዋል።

የግብርናው ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ እስኪደረግበት ድረስ ፈተናዎች እንደማያጡት የተናገሩት ሚኒስትሩ፤በዚህም ፈተናዎችን የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ነው ያነሱት።

የ2013/2014 የምርት ዘመን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተለይም ግብርናው መልከ ብዙ ፈተናዎችን ቢያሳልፍም የተሻሉና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው አፈጻጸሞች እንደታዩበት አንስተዋል።

በምርት ዘመኑ ከአጠቃላይ ወጪ ምርቶች ግኝት ግብርናው 72 በመቶ ሲሸፍን፣ በተለይም በቡና ኤክስፖርት ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን አስታውሰዋል።

በአበባ፣በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በስጋ ኤክስፖርት ከዕቅዱ አንጻር የተሻለ አፈጻጸም እንደነበር ገልፀው፤በቀጣይ የአሰራር ስርዓትና የአመራር ሚናው ከተስተካከለ የተሻለ አፈጻጸም እንደሚኖር ገልጸዋል።

በዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት መኖሩን ጠቁመው የፌዴራልና ክልል አመራር ህዝብን አሰልፎ ሚናውን በአግባቡ መወጣቱ ስኬት ለማስመዝገብ አጋዥ መሆኑን በተግባር ማሳየት ተችሏልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከገጠሟት ተግዳሮቶች አንፃር ሲመዘን ዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም እንደነበረው ገልፀዋል።

በመሆኑም በዓመቱ በስራ ዕድል ፈጠራ፣በኤክስፖርትና ገቢን በማሳደግ ረገድ መልካም ውጤቶች እንደተገኙ አንስተዋል።

የሜካናይዜሽን እርሻን በሁሉም ክልሎች ማስጀመር የተቻለበት እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አፈጻጸም ኢትዮጵያ በአፍሪካና በዓለም ስሟ የተወሳበትን ውጤት ማስመዝገቧን ተናግረዋል።

በምርት ዘመኑ በመኸር ምርት ለመሰብሰብ ከታቀደው 374 ሚሊዮን ኩንታል 336 ሚሊዮን ኩንታል ምርት በመሰብሰብ የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካት ተችሏል።

ይህን ስኬት ለማስቀጠል ከቴክኖሎጂ አቅርቦት እና ስራውን ከማሳለጥ አንጻር የ2014/2015 ምርት ዘመን ትልቅ የቤት ስራ ይጠይቃል ነው ያሉት።

በእንስሳት ልማት ዘርፍም በዶሮ ልማት፣በዝርያ መሻሻልና ስጋ ልማት ጥሩ ጅምሮች ቢኖሩም ቀሪ ስራዎች ስለሚጠብቁን መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ነው ብለዋል።

የ2015 ዓ.ም ዕድቅ የተለጠጠ በመሆኑ ግቡን ለማሳካት ከየተቋማቱ ትልቅ ጥረት ይጠበቃል። ጠንካራ ጎኖችን ማስፋት ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ሃሳቦችን ወደተግባር በመቀየር የኢንዱስትሪዎችን የግብዓት እጥረት ማሟላት፣የወጪ ምርትን መጠን ማሳደግና የከተማ ግብርናን ማጎልበት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህ ስኬት የፌዴራልና የክልል ተቋማት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ መሆኑን ነው የተናገሩት። ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎችም በቀጣይ የምርት ዘመን ለታቀዱ ግቦች ውጤታማነት አበክረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ወርቁ ክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ባለፈው የምርት ዘመን በበጋ መስኖ ልማት ረገድ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ክልሉ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ፣የውጭ ገቢ ተኪ ምርቶችን በመጠንም በአይነትም መጨመርና ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ አራት አንኳር ግቦችን ይዞ እየሰራ ነው ብለዋል።

በምርት ዘመኑ በመኸር 205 ሚሊየን፣በመስኖ 17 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱንና ለዚህ ይረዳ ዘንድ በግብዓት አቅርቦት ዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

የጋምቤላ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኩዌት ሉል በበኩላቸው ክልሉ በግብርና ዘርፍ ትልቅ አቅም እንዳለው ገልፀው፤ በቀጣይ ምርት ዘመን 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልጸዋል።

ክልሉ ቀደም ሲል በቆላ ስንዴ የሸፈነው መሬት 100 ሄክታር ብቻ እንደነበር አስታውሰው በቀጣይ በ2 ሺህ 100 ሄከታር መሬት ላይ የቆላ ስንዴ ለማልማት መታቀዱን ተናግረዋል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ሶስተኛው ሙሌት
«በህዳሴ ግድብ የግዳጅ ቀጣና ሠራዊቱ ቀን ከሌት ግዳጁን እየተወጣ ነው»
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2