Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ጆ ባይደን “የ ያ ዘመን አጢያት” ሲሉ አገራቸው የሰራችውን ግፍ አነሱ
News

ጆ ባይደን “የ ያ ዘመን አጢያት” ሲሉ አገራቸው የሰራችውን ግፍ አነሱ

Ethioreview newsEthioreview news—December 16, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዩናይትድ ስቴትስና አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ ለመካፈል ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኙ የአፍሪካ መሪዎች ትላንት ማታ የዕራት ግብዣ አድርገውላቸዋል። ከተወሰኑ የአፍሪካ መሪዎች ጋራ በተናጠል በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የተመረጡትን የአፍሪካ ሀገሮችን ዝርዝርም ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትላንት በዋሽንግተን ለተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች በዋይት ኃውስ ባደረጉት የዕራት ግብዣ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ “ለአፍሪካ መጪ ዘመን በሙሉ አቅሟ ትሰራለች” ሲሉ ተናግረዋል። በጤና፣ በመሰረተ ልማት፣ በቢዝነስ እና በቴክኖሎጂ እያደገች ያለችውን አህጉር ለማገዝ አሜሪካ በቢሊየን የሚቆጠር የመንግስት ገንዘብ እና የግል መዋዕለ ንዋይ መመደቧንም አብራርተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አፍሪካንና አሜሪካን ለዘላለም የሚያስተሳስራቸውን ግንኙነት አስመልክተው ሲናገሩም “ሕዝባችን የሚኖረው አሜሪካንና አፍሪካን ለዘላለም በሚያስተሳስረው ረቂቅ እና ጥልቅ ትስስር መካከል ነው። በሰንሰለት ታስረው በባህር ዳርቻዎቻችን በኩል እንዲገቡ የተደረጉትንና ለማይታሰብ ጭካኔ የተዳረጉትን ወንዶች እና ሴቶች እናስታውሳለን።” ብለዋል።

አክለውም “የሀገሬ የመጀመሪያ ሀጢያት ያ ዘመን ነበር። ይህችን ሀገር በመገንባትና ከፍ እንድትል በማድረግ፣ በኃላፊነት በመምራት፣ አዳዲስ መንገዶችን የፈነጠቁ እና በአሜሪካ ውስጥ ላለ ሁሉም ሰው የተሻለ የወደፊት ህይወት የፈጠሩ የሆኑትን የነሱን ትውልዶች እናከብራለን።” ሲሉ ተናግረዋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

አፍሪካውያን አሜሪካን እንደ ሀገር ዛሬ ያለችበት ደረጃ ለማድረስ የከፈሉትን መስዋዕትነት ከማንሳት ባሻገር ዛሬ በአሜሪካ የሚኖረው የአፍሪካ ማህበረሰብም እንዲሁ ለአሜሪካ ዕድገት ያለውን አስተዋፅኦ ባይደን አንስተዋል። በመጀመሪያው ጥቁር የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር ማገልገላቸውንም አፅንኦት ሰጥተው አስታውሰዋል።

“ኢቦላ” – ለድሆች የቀረበ ስጦታ? “የ ያ ዘመን ” ተቀጥላ አጢያት?

በሽታውን ማስተላለፍ ባልተቻሉበት ሁኔታ ደግሞ በእስረኞቹ የቆሰሉ ብልቶች እንዲሁም እጅና ፊት ላይ የበሽታው ባክቴሪያ እንዲፈስ በማድረግ ይህም ካልሆነ የአከርካሪ አጥንታቸውን በመብጣት በበሽታው እንዲለከፉ መደረጉ ታውቋል፡፡

“ዛሬ በአሜሪካ የሚኖረውን የአፍሪካ ዳያስፖራ ማህበረሰብም እናከብራለን። በአሜሪካ ያሉ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ጠንካራ ህዝቦች እንደ አንድ በጥብቅ የተሳሰረ ቤተሰብ እንኖራለን። እዚህ ላይ የቀድሞ አለቃዬ የነበሩትን እና ከሳቸው ጎን ሆኜ ለስምንት ዓመታት በማገልገሌ ክብር እንዲሰማኝ ያደረገኝን ሥራ ላንሳ፡፡ ባራክ ኦባማን እና እሳቸው ፕሬዝዳንት እያሉ ስላስተናገድነው የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ እና የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ለማንሳት እፈልጋለሁ። እንደ መሪ ህዝባችን ያበረታታናል። በእጃችን ውስጥ ያሉ ዕድሎች እንድናይ ይቀሰቅሰናል። አብረን ከሰራን ብዙ የሚቻሉ ነገሮች አሉ። ለመስማት የሚከብዱንን እውነቶች ይነግሩናል። የዚች ሀገር መስራቾች ያስቀመጡልንን እሴቶች ጠብቀን እንድንኖር እና ለተሰጠን የተቀደሰ አደራ ኃላፊነታችንን በብቃት እንድንወጣ ይፈትኑናል”፡፡ ብለዋል፡፡

ባይደን አክለው አብሮ መስራት በተለይ ለመጪው ትውልድ የተሻለ ነገር ለማውረስ ያለውን ጥቅም አስምረውበታል።”ለዓመታት በፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ እንዳሳለፈ ሰው እንደአሁን የተስፋ ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም። ከልቤ ነው የምናገረው፣ ስለወደፊቱ የጋራ ዕጣችን ከዚህ በላይ በተስፋ ተሞልቼ አላውቅም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ህዝባችን፣ በተለይ ደግሞ የየሀገሮቻችን ወጣቶች ናቸው። በጋራ ጤናማ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የበለጠ እኩል፣ የበለጠ ፍትሃዊ፣ የበለጠ የበለፀገ እና ለሁሉም ሰው የበለጠ ዕድል የተሞላበት ዓለም ዕውን ማድረግ እንችላለን” ብለዋል።

ይህን ይንብቡ ማርታ ኦሪላና ይባላሉ፡፡ የ74 ዓመት አዛውንት ናቸው፤ የልጅ ልጅ አይተዋል፡፡ አሜሪካ በጓቴማላ በቂጥኝ ላይ ባደረገችው ምርምር ያለፈቃዳቸው በሽታው ተሰጥቷቸው ለከፍተኛ ስቃይ ተዳርገዋል፡

ባይደን በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ በዋይት ኃውስ የተሰበሰቡት መሪዎች እና ተጋባዦች ለአዲስ ትብብር ያላቸውን መልካም ምኞት ፅዋቸውን በማንሳት እንዲገልፁ ጋብዘዋል።”ለአሜሪካ ህዝብ፣ ለዩናይትድ ስቴትስ፣ ለአፍሪካ ህዝብ እና ወደፊት ለሚኖረን አጋርነት ለተገባው ቃል እባካችሁ ፅዋችሁን ወደላይ ከፍ አድርጉ! “የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳልም እንዲሁ አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለሚኖራት ትብብር ተጋባዦች ፅዋቸውን እንዲያነሱ ጠይቀዋል።

“ለአስተናጋጃችን ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ለቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ክብር፣ ለአሜሪካ ህዝብ ክብር እና በአሜሪካ እና አፍሪካውያን መካከል ልለው ትብብር መጠናከር በአፍሪካ ስም ሁላችሁም ፅዋችሁን እንድታነሱ እጠይቃለሁ!!”።

በዋይት ኃውስ ከተካሄደው የራት ግብዣ በተጨማሪ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጉባዔው ላይ ለተገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የእራት ግብዣ አድርገዋል።

ብሊንከን በግብዣው ላይ ባደረጉት ንግግር “አጋርነት የፕሬዝዳንት ባይደን የአፍሪካ ስትራቴጂ እምብርት ነው” ያሉ ሲሆን “በተለይ በዓለም ላይ የተደቀኑትን የአየር ንብረት ለውጥ፣ ንፁህ ታዳሽ ኃይል፣ የህብረተሰብ ጤና፣ ኢኮኖሚ፣ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ችግሮች ለመፍታት የተሻለው እና ውጤታማው መንገድ የንግዱን ማህበረሰብ ጥረት ጨምሮ የተቀናጀ ትብብር ማድረግ ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል።

ይህንን ያንብቡ “እርግጥ ነው የደረሰብንን ቁስል ወደኋላ ሄዶ እንዳልተደረገ ማድረግ አይቻልም፤ አለአግባብ በደል ተፈጽሞብናል፤ እንደ እንስሳ መድሃኒት መሞከሪያ (ጊኒፒግ) ተደርገናል፤ … ነገርግን በእኔ አመለካከት፣ እምነትን እና መተማመንን እንደገና ለማስፈን አሁንም የዘገየን አይመስለኝም”

ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎችን ለማራመድ እና ወሳኝ የጤና እና የኃይል እድገትን ወደፊት ለመግፋት አሜሪካ ታማኝ አጋር መሆኗን አስረግጠው እየገለፁ ያሉት ባይደን በሚቀጥሉት ሶስት ዐመታት 55 ቢሊየን ዶላር የሚገመት መዋዕለ ንዋይ በአፍሪካ እንደምታፈስ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ አስታውቀዋል። ከ15 ቢሊየን ዶላር በላይ ደግሞ በግል ንግድ እና መዋዕለ ንዋይ ትብብሮች ቃል መገባቱን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን በጉባዔው ለአፍሪካ መሪዎች ባደረጉት ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ ከአዲሱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት ጋር ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟን እና ይሄም ከዚህ በፊት ያልታየ ሲሉ የገለጹትን ከቀረጥ ነፃ ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሚሊኒየም ቻሌንጅ ኮርፖሬሽን የተሰኘው የአሜሪካ የውጭ ርዳታ ተቋም ለመጀመሪያ ግዜ በአፍሪካ መንገዶችን ለመገንባት፣ የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ እና በተለይ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በፍጥነት ምርቶቻቸውን ለማጓጓዝ የሚያስችላቸው የ 500 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ከአፍሪካ መንግስታት ጋር መፈራረሙንም ይፋ አድርገዋል።

አሜሪካ ዲሞክራሲን ለማጠናከር ከአፍሪካ ህብረት ጋር እንደምትሰራ የገለፁት ባይደን “መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ የሚፈልጉ የአሜሪካ የንግድ ተቋማት ወደ አፍሪካ እንዲሄዱ ወይም የአፍሪካ ኢኮኖሚ ወደፊት እንዲሻገር የመልካም አስተዳደር፣ የጤናማ ማህበረሰብ እና የተመጣጣኝ የኃይል አቅርቦት መኖር ወሳኝ ነው” ብለዋል።ለሶስት ቀን በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ባለው የዩናይትድ ስቴትስ እና የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ ፕሬዚደንት ባይደን ከተመረጡ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር የተናጠል ስብሰባ የሚያደርጉ ሲሆን እነርሱም ጋቦን፣ ናይጄሪያ፣ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ማዳጋስካር እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መሆናቸውን ትላንት ይፋ አድርገዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በኃያላን ሀገራት መካከል ለሚደረገው ፉክክር ቁልፍ የጦር ሜዳ በሆኑት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ ከቻይና ወደ ኃላ ቀርታለች። አፍሪካ በፍጥነት እያደገ በሚሄደው የህዝቧ ቁጥር በግዙፍ የተፈጥሮ ሃብቷ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትልቅ ድምፅ ሰጪ ቡድን ያላት በመሆኗ በዓለም ኃይል አሰላለፍ ቁልፍ ሚና አላት። በመሆኑም የባይደን አስተዳደር በውጪ ፖሊሲው ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ባላንጣ አድርጎ የሚመለከታትን ቻይናን ትኩረቱ ባደረገበት በዚህ ወቅት አፍሪካ ለዩናይትድ ስቴትስ ትልቅ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላት አህጉር መሆኗን ትቀጥላለች።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ቻይና ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ፈቀደች
“ኢቦላ” – ለድሆች የቀረበ ስጦታ? “የ ያ ዘመን ” ተቀጥላ አጢያት?
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2