Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የአማራ ክልል ህዝብ ከጥፋት በፊት በርጋታ እንዲያስብ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠየቁ
News

የአማራ ክልል ህዝብ ከጥፋት በፊት በርጋታ እንዲያስብ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠየቁ

Ethioreview newsEthioreview news—April 9, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ለማደራጀት መወሰኑን ተናግረዋል። ወደ ትግበራም መገባቱን ገልፀዋል።

ውሳኔው በፌዴራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት ስምምነት የተወሰነ መሆኑንም ተናግረዋል። ውሳኔው በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ  እንደሆነም ገልፀዋል።

በአማራ ክልልም ውሳኔውን ለመተግበር እየተሠራ መሆኑን ያነሱት ርእሰ መስተዳድሩ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በአፈጻጸም ላይ በታየ ክፍተት እና በተነዛው ፕሮፖጋንዳ ችግሮች መከሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ችግር እንኳን ቢኖር ተወያይቶ መፍታት ይቻላል ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ  አብዛኛው የልዩ ኃይል አባል ውይይቱን አጠናቆ ውሳኔውን  በካምፕ ሆኖ እየተጠባበቀ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ጀግና ልዩ ኃይል ነው፣ መስዋእትነት የከፈለ ልዩ ኃይል ነው፣ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ሆኖ የሀገርን ሕልውና እና ሉዓላዊነት የጠበቀና ያስከበረ  ነው፣ ይህ ልዩ ኃይል ትጥቅ የሚፈታና የሚበተን አይደለም፣ በላቀ አደረጃጃት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ነውም ብለዋል፡፡ ልዩ ኃይሉ ዓላማውን ተገንዝቦ ለበለጠ ተልእኮ እንዲዘጋጅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአማራ ሕዝብ በሁኔታው ቅሬታ ውስጥ መግባቱን የተናገሩት ርእሰ መስተዳድሩ ቅሬታው የመነጨው በተሟላ መንገድ ለሕዝቡ መረጃ ባለመድረሱ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ዓላማው የሀገር አንድነትን የሚያጸና፣ አብሮነትን የሚያስቀጥል እና የጸጥታ መዋቅሩ በክልልም ሆነ በፌዴራል የተናበበና ሕግን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ማድረግ ነውም ብለዋል፡፡ አደረጃጀቱ የሚደገፍ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የሀገርን አንድነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ አደረጃጀቱ የአማራን ክልል በተለየ መንገድ የሚጎዳ አይደለም ብለዋል፡፡

የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የታለመ ዓላማ እንደሌለ  አስገንዝበዋል፡፡ በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት በአንዳንድ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ፣ የአድማ ጥሪ እና የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴን የመገደብ አዝማሚያዎች እያታዩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

አላስፈላጊ አካሄዶች አውዳሚ እና አክሳሪ እንጂ አትራፊ አለመሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

የአማራ ክልል በጦርነት የከረመ ክልል ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ተጎሳቁሏል፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው ኅብረተሰብ እና መሠረተ ልማት ገና ማገገም አልቻለም ብለዋል፡፡ ከአንደኛው ችግር ሳያገግም ወደ ሌላ ችግር መሸጋገር ሕዝቡን መጉዳት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመወያየት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ማስቆም እንደሚቻልም ገልጸዋል፡፡ ሁሉም አውዳሚ የሆነውን ጉዳይ መከላከል እንደሚገባውም አመላክተዋል፡፡ ግጭት እንዳይፈጠር ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶች የሚመሰገን ሥራ እየሠሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን በውል በማጤን፣ በመመካከር እና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ ማስከን ይገባልም ብለዋል፡፡

የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ የሚጎዳ ውሳኔ አልተወሰነም፣ ወጥና ሀገራዊ ውሳኔ ነው የተደረገው፣ በሁሉም ክልል የሚፈጸም ነው፣ ውሳኔው ለሀገር ግንባታ ታላቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው እናምናለንም ብለዋል፡፡

ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር የሚነሳው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም አፈጻጸሙ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ከካምፕ የወጡ የልዩ ኃይል አባላት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በረጅም የሀገረ መንግሥት ግንባታ ታሪኩ እና በስርዓት አክባሪነቱ የሚታወቀው የአማራ ሕዝብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማየት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ችግሩ ዳር ወጥቶ ግጭት እንዳይከሰት እያደረጉ ላሉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ አትፈቱም፣ የምትበተኑበት ነገር የለም፣ ወደ ላቀ ተልእኮ ነው የምትሽጋገሩት፣ ይሄን አውቃችሁ ለሀገራችሁ እና ለክልላችሁ ስታደርጉት የነበረውን አስተዋጽዖ በተሟላ መንገድ ለማስቀጠል እንድትችሉና እንድትዘጋጁ አደራ እላለሁም ብለዋል፡፡
እንደ አሚኮ ዘገባ፤ በመደማመጥ ችግሮቻችን እንፈታለን፣ የአማራን ጥያቄዎች እናስመልሳለንም ነው ያሉት፡፡

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ከጊዜያዊ መፍትሄ ዘላቂ ጥቅም አይገኝም!” ዐቢይ አሕመድ
አብን የተጀመረርው የአማራ ልዩ ሃይልን መልሶ ማደራጀት እንዲቆም አሳሰበ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2