የአቶ ግርማ የሺጥላንና አብረዋቸው የነበሩ ስድስት ጠባቂዎች ከመገደላቸው ስድስት ቀናት በፊት በተለይ እሳቸውን ማዕከል አድርጎ በተዘጋጀ ፕሮግራም ሊወገዱ እንደሚገባ መገለጹ በይፋ መረጃ የተያዘ ስለሆነና የአሜሪካ መንግስት የሽብር ተግባርን ስለማይቀበል ክስ ለመስረት ንግግር መጀመሩ ተሰማ።
የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ሀላፊ ግርማ የሺጥላ በትውልድ ቀያቸው የማህበረሰብ የሰላምና የልማት ጥያቄዎች ተቀብሎ ለመፍታት ሲያወያዩ ቆይተው፣ እገረ መንገዳቸውን ዘመድ አዝማድ ጠይቀው ከቤተሰቦቸውና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በስድስት ተሸከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ መንገድ ላይ አድፍጠው በጠበቁ ታጣቂዎች መገደላቸው፣ ልጃቸውና ሚስታቸው መትረፋቸውን የመንግስት ሚዲያዎች አስታውቀዋል።
አቶ ግርማ በ300 የዩቲዩብ ገጽ “ክልስ ነው ። ግማሽ ኦሮሞ ነው። እናቱ አማራ አባቱ ኦሮሞ ናቸው” በሚል አጥንታቸው ተቆጥሮ የስነልቦና ጠርዝ ማስያዣ ዝግጅት ሲደረግባቸው ነበር። የአማራ ህዝብ እንዲህ ያሉትን ማስወገድ እንዳለበትም በገሃድ ተነግሯል። ከተገደሉ በሁዋላም በዚህ ጣቢያ ” የሃዝን መግለጫ ባህላችን ቢሆንም ለሱ የሚሆን የለኝም” የሚል መልዕክት ተላልፏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው አሜሪካን አገር የሽብር ክስ ለመመስረት እንቅስቃሴ መጀመሩ የተገለጸው። ሽብርን አጥብቆ በሚቃወመው የአሜሪካ አገር ህግ መሰረት ክስ ለመስረት የህግ ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ መረጃ እየሰበሰቡ መሆኑንን ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ ገልጸዋል። ምን አልባትም ድርጊቱ ወንጀል ከሆነ ይህንኑ ተግባር በገንዘብ የሚደጉሙ በተመሳሳይ በአሜሪካ ህግ መሰረት ማጣራት ሊካሄድባቸው እንደሚችል ተመልክቷል።
ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም ሆነ በአሉታ…
ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ እንግዶች ፊት…
“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን ተከትሎ ያኮረፉት…
አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እርስ በርስ የሚረዱበትን አዲስ የጋራ መከላከያ ስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት መስማማታቸውን አስታወቁ።…
የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን የከፋ ቀጣት ይጠበቃቸዋል። ባለፉት…

