ምርጫ ቦርድ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በተደነገገው አዋጅ መሠረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ሕጉን መሠረት አድርጎ ሲፈቅድ መሆኑንም ዛሬ ግንቦት 5/ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ህወሓት ለምርጫ ቦርድ የሕጋዊ ሰውነት ስረዛና የፓርቲው ንብረት እገዳ ይነሳልኝ ጥያቄ ያቀረበው ፕሪቶሪያ የተደረሰውን ግጭትን በዘላቂነት ለማስቆም የተደረሰውን ስምምነት በመጥቀስ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ነው።
ደብዳቤው ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ሕጋዊ ስረዛ አስመልክቶ ጥር 10/ 2013 ዓ.ም ያስተላለፈውን ውሳኔ ጠቅሷል።
ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን ተረጋግጧል በሚል የፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት እንዲሰረዝ፣ የፓርቲው ኃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንዳይችሉ፣ እንዲሁም የፓርቲው ንብረት ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳው መሸፈኛ እንዲውል፣ ቀሪው ገንዘብና ንብረትና ደግሞ ለሥነ ዜጋ መራጮች ትምህርት እንዲውል የሚደነግግ ነው።
በትግራይ ክልል የነበረው ጦርነት በሰላም በመቋጨቱና በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት መካከል የተደረሰውን ስምምነትም በመጥቀስም ፓርቲው የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል የሚለው ድምዳሜ አሁን ላይ መለወጡን ታሳቢ በማድረግ ቦርዱ ከዚህ ቀደም ያስተላለፋቸውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ስረዛና ሌሎች ብያኔዎች እንዲነሳ ሲል መጠየቁንም ምርጮ ቦርድ አስፍሯል።
ቦርዱ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ አስተላለፍኩት ባለው ውሳኔ ህወሓት በላከው ደብዳቤ እንደተገለጸው ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሠረት ያደረገው የአመጻ ተግባር አሁን የለም ብሏል።
ነገር ግን እንደገና የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/ 2011 ተደንግጎ እንደማይገኝ ጠቅሷል። በዚህም ምክነያት ቦርዱ በህወሓት የቀረበለትን የሕጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይን በሕግ የተደገፈ ሆኖ ባለማግኘቱ አንዳልተቀበለው ጠቅሷል።
ስለዚህ በአዋጁና በተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሠረት ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ሕጉን መሠረት አድርጎ ሲፈቅድ መሆኑን መወሰኑን አመላክቷል።
የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደ አዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ ሆነው ባለመገኘታቸው እግዱ እንዳልተነሳ ጠቅሶ የቀረበውን ጥያቄ ቦርድ ውደቅ ማድረጉ ተጠቅሷል።
ጥር 10/2013 ዓ.ም. ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን ማስታወቁ ይታወሳል።
ቦርዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ህወሓት በአመጽ ተግባር ላይ መሰማራቱን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጡን በመግለጽ፣ ሕጋዊ ሂደቶችን በመከተል የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት በመሰረዝ ማንም በህወሓት ስም መንቀሳቀስ እንደማይችል ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ይታወሳል።
በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ግጭት የማቆም ዘላቂ ስምምነት ተከትሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብር ቡድንነት ተሰይሞ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፍረጃው መነሳቱ ይታወሳል።
በትግራይ ተከስቶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት የመቶ ሺዎችን ሕይወት ቀጥፏል እንዲሁም ሚሊዮኖችን ለሰቆቃ ዳርጓል።
በመቶ ሺዎች በተቀጠፉበት ጦርነት መደፈር፣ ወሲባዊ ጥቃቶች፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ ረሃብ በጦር መሣሪያነት ጥቅም ላይ መዋላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሪፖርት ያሳያል ሲል ቢቢሲ የምርጫ ቦርድን ደብዳቤ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
- አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱበዙፋን ኡርጋ ደራሲነት የተጻፈውን ሌንጮ ለታ ትግል ሕይወቱ መጽሐፍን አነበብኩት። መጽሐፉ በ471 ገጾች እና በሦስት ክፍሎች ተቀንብቧል። የመጀመሪያው ክፍል ከልጅነት እስከ ትግል ዋዜማ የሚል ርዕስ የተሰጠው ሲሆን፤ ሁለኛው ክፍል ከዩኒቨርሲቲ እስከ ቤተ መንግሥት፤ ሦስተኛው ክፍል… Read more: አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደርበኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት ጽንፍ ተፈርጀው ይተቻሉ። በአንድ በኩል “ለኦሮሞ ሕዝብ ማንነትና ታሪክ የታገሉ ምሁር” የሚሏቸው አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ “የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተኑ፣የባዕድ አገር የኤርትራ መሪ ኢሳያስ ፍላጎት አስፈጻሚ”… Read more: ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር
- የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙየአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር አኔት ዌበር Dr. Annette Weber ለኤርትራ መሪዎች ጣልቃ ገብነታቸውን እንዲያቆሙ አሳስበው መመለሳቸውን ተልትሎ በግል የኤክስ ገጻቸው በዲፕሎማት ቋንቋ ያሰፈሩት መልዕክት ተቃውሞና አቤቱታ እያስተናገደ ነው። የጉብኝቱ ዋና ዓላማና ፖለቲካዊ… Read more: የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ







