Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  አብን በአማራ ክልል የተፈጠሩት ችግሮችን መንግስት በጥንቃቄና በውይይት ሊፈታቸው እንደሚችል መከረ
News

አብን በአማራ ክልል የተፈጠሩት ችግሮችን መንግስት በጥንቃቄና በውይይት ሊፈታቸው እንደሚችል መከረ

Ethioreview newsEthioreview news—May 2, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

.….የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸውን በሸፍጥ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ባልተገባ መልኩ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው እንደሚቀርቡ ሊታወቅ ይገባል። ትላንት የአማራ ሕዝብ መጠነሰፊ የወረራ ጦርነት ሲከፈትበት ዳር ላይ ቆመው የነበሩ እና ከጠላት ጋር አብረው የከረሙ አካላት የአማራ ሕዝብ ድንገተኛ ወዳጅ እና ወኪል በመሆን ግጭት ለማስነሳት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እናሳስባለን። የአማራ ሕዝብ እነዚህ አካላት የሚያደርጓቸውን አደንቋሪ የጥፋት ጥሪዎች ፈፅሞ እንዳይሰማ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ህዝብ በተደጋጋሚ ከተከፈተበት የወረራ ጦርነት ወጥቶ አንጻራዊ መረጋጋት ካሳዬ ገና ጥቂት ወራቶች ብቻ ተቆጥረዋል። በተከፈተበት ተደጋጋሚ ወረራ ለከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት መዳረጉ ይታወቃል። የአማራ ህዝብ ግጭትና ጦርነትን በተግባር የተመለከተ እንጅ በሩቅ የሚያውቀው ጉዳይ አይደለም።

የአማራ ህዝብ ያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ከፍትህ እና እኩልነት ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ከጥላቻና ፅንፈኛ ሃይሎች በስተቀር ሌሎች ወገኖች በተለይም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚያደምጧቸውና የሚደግፏቸው ናቸው።

በተለይ በጦርነቱ ወቅት የተከፈለውን ዋጋ በማይመጥን ደረጃና አግባብ የተመራው የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሁም ድኅረ-ጦርነት በመንግስት በኩል እየተካሄደ ያለው ግልፅነት የሌለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እና ስጋት መፍጠሩን መተማመን ያስፈልጋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

በዚህ ረገድ የአማራ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ቀናኢነት እና ሀገሩን ለመታደግ የከፈለውን ዋጋ የሚያራክሱ ተግባራት መደበኛ ሆነው አደባባይ ላይ መዋላቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ በድኅረ-ጦርነት ወቅት ከሕዝቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሰረታዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይነት ያለው ግልፅ ውይይት ባለመደረጉ ምክንያት የተፈጠሩ ችግሮች መሆናቸውን እንገነዘባለን።

ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ምክንያቶቹ ለረዥም ጊዜ የቆየው የፖለቲካ ችግር እና ወቅታዊው የመንግስት ፍላጎትና አቅም ማጣት ናቸው።
በአንድ በኩል የአማራ ሕዝብ በተደጋጋሚ ሀገሩንና የማዕከላዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመጠበቅ በመንግስት የተደረገለትን ጥሪዎችን በክብር ተቀብሎ መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል። ሆኖም መንግስት ለአማራ ሕዝብ ፍትኅዊ ጥያቄዎች፣ ፍላጎቶች እና ስጋቶች በቂ ትኩረት አለመስጠቱ ችግሩን አባብሶታል ብለን እናምናለን።

በአማራ ሕዝብ በኩል መንግስት ፍፁም መወያየትና ማድመጥ የማይፈልግ አካል መሆኑን አንድምታ ከተወሰደ ቆይቷል። አጠቃላይ ፖለቲካው ግልፅነት የጎደለው በመሆኑ እና ማሕበረሰቡን የሚያስተዳድርበትን ፍኖት ስለማያሳይ ዘወትር ጥርጣሬና የሴራ ትንተና የበላይነት እንዲኖረው በር ከፍቷል። ይሄም በሂደት እየጎለበተ ሄዶ አሁን ለተፈጠው የፀጥታ ችግር አስተዋፅኦ አድርጓል።

ስለሆነም በመንግስት በኩል በቀጠናው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጥታ በመወያየት ለተፈጠሩት ችግሮች እልባት የመስጠት ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አናሳስባለን። በተለይ ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና አንድነት በጋራ ተሰልፈው መስዋዕትነት የከፈሉት የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቅራኔ ውስጥ እንዳይገቡና ለግጭት እንዳይዳረጉ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል።

መንግስት የክፉ ቀን አጋሩ ከነበሩትና በእውነትም ከሕዝብና ከሃገር ፍላጎትና ጥቅም በተፃራሪ የመቆም ተሞክሮ፣ ዝንባሌና ታሪክ ከሌላቸው የአማራ ገበሬዎች፣ ወጣቶችና ፋኖዎች ጋር ያልተገባ ግብግብ ውስጥ መግባት የለበትም። ይህ ጉዳይ በውይይት እና ምክክር ሊፈታ የሚችል መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

በሌላ በኩል ግን የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸውን በሸፍጥ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ባልተገባ መልኩ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው እንደሚቀርቡ ሊታወቅ ይገባል። ትላንት የአማራ ሕዝብ መጠነሰፊ የወረራ ጦርነት ሲከፈትበት ዳር ላይ ቆመው የነበሩ እና ከጠላት ጋር አብረው የከረሙ አካላት የአማራ ሕዝብ ድንገተኛ ወዳጅ እና ወኪል በመሆን ግጭት ለማስነሳት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እናሳስባለን።
የአማራ ሕዝብ እነዚህ አካላት የሚያደርጓቸውን አደንቋሪ የጥፋት ጥሪዎች ፈፅሞ እንዳይሰማ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በተለይ የአማራ ወጣቶች፣ ፋኖዎች እና የልዩ ሃይል አባላት የሕዝባችን ሰላም እና ደህንነት እንዳይናጋ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዳይሰተጓጎሉ፣ የልማት ስራዎች እንዳይኮላሹ፣ በዋናነት ደግሞ ወገኖቻችን ላይ ምንም አይነት አካላዊ እና የህይወት ጉዳት እንዳይደርስ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ጥሪ አናቀርባለን። የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ምናልባት በጊዜያዊ ስሜት ሳይገፉ በሆደ ሰፊነት ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ተመሳሳይ ትጋት እንዲያሳዩ ጥሪ ለማቅረብ እንወዳለን።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአማራ ሕዝብ ያሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዲዘነጋና በምትኩ በደራሽና ስሜታዊነት በተጫናቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያተኩር የሚገፋፉ እንቅስቃሴዎች፣ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ የአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳዎች ሰለባ እንዳይሆን ህዝባችንና የህዝባችን ወዳጆች ሁሉ አዎንታዊ እገዛ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ህዝባችን ግራ ቀኙን በአግባቡ መዝኖ በስሙ የሚነግዱ ኃይሎችን ይሁንታ ሊነሳቸው ይገባል።

አብን አጠቃላይ የህዝባችን ትግል በሂደትና በየደረጃው ሰላምና መረጋጋት እንዲጎለብት፣ ጦርነትና ደም መፋሰስ እንዲቆም፣ የንግግርና የምክክር ምዕራፍ እንዲከፈት የሚያደርግ መሆን አለበት ብለን እናምናለን። ለአማራ ህዝብ እንታገላለን የሚሉ ኃይሎች ለህዝቡ ሰላም እና መረጋጋት ቅድሚያ መስጠት እና ሕዝባችን ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር ያለው ወዳጅነት እየተጠናከረ የሚሄድበትን መንገድ መቀየስ አለባቸው። በዚሁ አጋጣሚ የሌሎች ወንድም ሕዝቦችን ማንነት ማንቋሸሽ እና መዝለፍ የአማራ ሕዝብ ፍላጎት እንዳልሆነና መቼም ሆኖም እንደማያውቅ፣ ወደፊትም ጭምር እንደማይሆን በጥብቅ ማሳወቅ እንሻለን። ይህ የአማራ ሕዝብ ጠላቶች የሚያዛምቱትን የሀሳት ትርክት በተዘዋዋሪ መንገድ ለማረጋገጥ የሚደረግ ከንቱ ጥረት እንደሆነ ማስገንዘብ እንፈልጋለን።
በአማራ ሕዝብ ላይ ነውረኛ የሆኑ ፅንፈኛ ኃይሎች የሚያሰሙትን ፀያፍ ንግግርና የሚፈፅሙትን ጥቃት በአማራ ሕዝብ ስም በሌሎች ወገኖች ላይ መፈፀም ለአማራ ሕዝብም ይሁን ለኢትዮጵያ ተጨማሪና ተደራራቢ ችግር ከመፍጠር ባለፈ የሚያጣፋው ወይም የሚፈታው ችግር አይኖርም። የአማራ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ያደሩና የሚታወቁ የፍትኅ፣ የእኩልነት እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በመሆናቸው በጊዜ ሂደት፣ በሰላማዊ መንገድ፣ በውይይትና በሰለጠነ ድርድር እንዲሁም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወንድምና እህቶቻችን ድጋፍና ትብብር የሚሳኩ ናቸው።

ሌላው ከህዝባችን የመከራና የሰቆቃ አድማስ የራቁና የማይታወቁ እንዲሁም በመንግስት መዋቅሮች እና በተለያዩ የፖለቲካ አሰላለፎች ውስጥ ሆነው በአማራ ሕዝብ ላይ ዘወትር ግጭት የሚጠምቁ፣ የአማራ ክልልን የጦርነት ቀጠና ማድረግ የሚፈልጉ አካላት በአስቸኳይ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጥሪ እናስተላልፋለን።

የህልውና ዘመቻው አይነተኛ ሚና የነበራቸውን የአማራ ፋኖዎች በውትወታ ከመስመር ማስወጣት እና ግጭት ውስጥ ማስገባት፣ በቅጡ ባልተሰላ ፖለቲካ ሕዝባችንን ማጎሳቆል የሚፈልጉ ኃይሎች ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

ስለሆነም:-

  1. የባለድርሻ አካላት ውይይት ማለትም የክልል እና የፌድራል መንግስት፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ የምሁራን መማክርት፣
    ታዋቂ እና ተደማጭ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ካውንስልን ያካተተ ቡድን በተመረጡ ከተማዎች አንገብጋቢ አጀንዳዎችን ለይቶ ከህዝባችን ጋር ውይይት በማድረግ፣ ውዥንብርን በማጥራት የጋራ መረዳት እንዲፈጠር ማድረግ ይገባል ለዚህም ጥሪ እናደርጋለን።
  2. ሐገራችንም ሆነ የአማራ ህዝብ የተቃጣባቸውን ወረራ በመመከት ሂደት ላይ ለመከላከያ ሰራዊት ባደረገው የደጀንነት ሚና ከፍተኛ ምስጋና የተቸረው መሆኑ የትናንት ትዝታ ነው። በዚህም የአማራ ህዝብ ሐገር ችግር ላይ በወደቀች ጊዜ ከሐገሩ ጎን የመሰለፍ የቆዬ ታሪኩን ያስመሰከረ ሐቅ ሆኖ አልፏል። ስለሆነም ከዚህ የወገን ኃይል ጋር ፈፅሞ መቃቃር አስፈላጊ ነው የሚል እምነት የለንም።
  3. ፋኖን ጨምሮ ለሁሉም ታጣቂ ወንድሞቻችን ህዝባችን ላይ የተቃጣውን ወረራ በመመከት ሂደት ላይ ያሳያችሁት ቆራጥነት በታሪክ የተመዘገበ የጀግንነት ፍኖት ሆኖ አልፏል። ለዚህ ውለታችሁም የአማራ ህዝብ የተሟላ ሰላም ውስጥ በሚገባበት ወቅት አስፈላጊውን ሽልማት እና እውቅና የሚቸራችሁ እንደሚሆን እናምናለን። ሆኖም ትናንት በአንድ ምሽግ አድራችሁ፣ በአንድ ኮዳ ጠጥታችሁ፣ በአንድ ሳህን ቆርሳችሁ፣ በአንድ ጉድጓድ ከተቀበረው ወንድማችሁ ከሆነው የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል የፀጥታ ኃይል ጋር በፍፁም ግጭት ውስጥ መግባት እንደሌለባችሁ አበክረን እንረዳለን። ስለሆነም አሁን ያለውን መካረር በማርገብ በተወካዮቻችሁ ዘንድ ከፀጥታ አካላት አመራሮች ጋር ንግግር ትጀምሩ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
  4. የአማራ ክልል መንግስትን ጨምሮ የፌደራል መንግስት ከግጭት ተጨማሪ ሀገራዊ ጉስቁልና ከመጋበዝ ውጭ ምንም አይነት ዘላቂ ፖለቲካዊ ትርፍ ማግኘት እንደማይቻል ያሳለፍነው የጦርነት መንገድ በቂ ትምህርት ሰጥቷል የሚል ፅኑ እምነት አለን። ስለሆነም መንግስት ከግጭት ምንም ፋይዳ እንደማይገኝ ተረድቶ አሁን ላይ እየታዬ የመጣውን መካረር በሰላም ማዕቀፍ የሚፈታበትን እድል እንዲተገብር በጥብቅ እናሳስባለን። ስለሆነም መንግስት ደም አፋሳሽ ሊሆን የሚችልን እቅድ ሁሉ ከወዲሁ ተረድቶ ለሰላም እና ውይይት በር እንዲከፍት እና በአስቸኳይ እንዲተገብር እንጠይቃለን።

በተያያዘ መልኩ የመንግስት የፀጥታ አስከባሪ አካላት ንፁኃን እንዳይጠቁ እና ያላግባብ እንዳይታሰሩ ማድረግ እንዳለባቸው እንዲሁም ያላግባብ የታሰሩትን ባስቸኳይ እንዲፈቱ እናሳስባለን።

በመጨረሻም የጋራ የውይይት መድረኩ በአስቸኳይ እውን ይሆን ዘንድ አብን የማስተባበር ድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ እየጠቆመ ባለ ድርሻ አካላት ዕቅዱ በአፋጣኝ ይተገበር ዘንድ የዘወትር ትብብራችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም ሆነ በአሉታ አልተነፈሱም። ነገሮችን በጥሞና የሚከታተሉ “ቴድሮስ ራሱ ወይም…

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ እንግዶች ፊት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ…

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን ተከትሎ ያኮረፉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ ሰሞኑን አሜሪካ መልሳ ልትዋዳጃቸው ማቀዷ…

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኢዜማ መንግስት ከኦነግ ጋር በሚያደርገው ድርድር ግልጽነትን ጠየቀ
በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2