Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ዓባይ ከግብጽ እስከ አረብ ሊግ!
News

ዓባይ ከግብጽ እስከ አረብ ሊግ!

Ethioreview newsEthioreview news—May 23, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከሳምንት በፊት “ኢትዮጵያ አራተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት በቅርቡ ትጀምራለች፤ አሁንም አቤቱታችሁን ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ልትወስዱት ትችላላችሁ?” የሚል ጥያቄ በጋዜጠኞች የቀረበላቸው የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ የሰጡት ምላሽ የአረብ ሊግ የአቋም መግለጫን ቀድሞ ያመላከተ ነበር፡፡ “ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ” እንደሚባለው ከስብሰባው በፊት የአቋም መግለጫውን የስብሰባው ዘዋሪዎች ለዓለም ሕዝብ ጆሮ አደረሱት፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሚ ሽኩሪ በምላሻቸው “እስከአሁን አቤቱታችንን ከጸጥታው ምክር ቤት እስከ አፍሪካ ኅብረት አቅርበን የተለየ ነገር አልመጣም፡፡ በተደጋጋሚ መንገድ መሄድ ሳይኾን ጉዳዩን አቅጣጫ ቀይሮ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ የግድቡን የውኃ ሙሌት በተመለከተ ግብጽ ጉዳዩን ወደ አረብ ሊግ ትወስደዋለች” ሲሉ ተደመጡ፡፡ እንደ እውነቱ ከኾነ በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ የተካሄደው 32ኛው የአረብ ሊግ ስብሰባ ከወትሮው የተለየ እና ትኩረት የሚሹ የመወያያ አንገብጋቢ ነጥቦች ነበሩት፡፡

የአረብ ሊግ እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር መጋቢት 22/1945 ሲመሰረት ከመሥራቾቹ ሰባት ሀገራት መካከል አንዷ የኾነችው የበሽር አላሳዷ ሀገር ሶሪያ ከ12 ዓመታት በኋላ በተመለሰችበት ስብሰባ ከኢትዮጵያ የተሻገረ የአባል ሀገራቱ አንገብጋቢ ጉዳዮች ነበሩባቸው፡፡ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት እና በጦርነት የተጎዳችውን ሶሪያን ከማቋቋም በላይ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ አቋም መያዝ ከሊጉ ጀርባ የስብሰባው ዘዋሪዎች እነማን እንደነበሩ በግልጽ አመላካች ኾኖ ታይቷል፡፡

ላለፉት ሦስት ዓመታት በሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ዙሪያ ከካይሮ ጋር የወገነችው ካርቱም በሁለቱ ጀኔራሎቿ እልኽ አስጨራሽ ጦርነት ድምጿ ጠፍቷል፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ እንዴት እና ለምን ሱዳን ውስጥ እንደተገኙ እስካሁንም ድረስ ምክንያቱ ግልጽ ያልኾነው የግብጽ ወታደሮች ጉዳይ ለሱዳን ሕዝብ የእግር እሳት በኾነበት በዚህ ወቅት ግብጽ በውኃ ሙሌቱ ዙሪያ ሱዳንም ተመሳሳይ አቤቱታ እንዳላት ሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ተገኝታ ጉዳይ ፈጻሚ መኾኗን አረጋገጠች፡፡ ይህ ሁሉ ተሰባስቦ የዓባይ ጉዳይ ከግብጽ እስከ አረብ ሊግ ውስብስብ እጆች እንዳረፉበት አመላካች ነው ይላሉ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አደም ካሚል፡፡

More stories

በጁባ የተበጣጠሰው የጁንታው የሽብር መረብ

August 20, 2021

ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው! – (ኢዜማ)

November 23, 2021

ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

May 17, 2021

የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አጀንዳ ቀርጸው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተገለፀ

June 12, 2021

ግንባር ቀደም ጉዳይ አስፈጻሚዎቹ እና ዋና ጽሕፈት ቤቱ ካይሮ ላይ ከተቀመጠ ሊግ ከዚህ የተለየ አቋም መጠበቅ “በተኩላ ዘመን በግ መኾን” ነው ያሉት ፕሮፌሰር አደም ሳዑዲ አረቢያም የዓባይን ጉዳይ የአረቡ ዓለም ጉዳይ ለማድረግ በቅርቡ የምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የሊጉ አቋም ቅድመ ምልክቶች ነበሩ ይላሉ፡፡ በሳዑዲ አረቢያው የሊጉ ስብሰባ የሕዳሴ ግድቡን በሚመለከት የታየው አቋም ከወትሮው ያልተለየ እና መሻሻል ያልታየበት ነውም ብለዋል፡፡

“የግብጽ የውኃ አቅርቦት ጉዳይ የአረብ ሊግ ሀገራት የፀጥታ ስጋት ጉዳይ ነው” የሚለው የሊጉ ወቅታዊ አቋም የሳዑዲ አረቢያን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ነው የሚሉት ፕሮፌሰር አደም ምክንያቱን ሲያነሱም ሳዑዲ አረቢያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በግብጽ እና ሱዳን ከፍተኛ የእርሻ ኢንቨስትመንት ማስፋፋቷን ተከትሎ የቀረበ ስጋት ነው ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ በየጊዜው “አልቀበለውም” ከሚል ምላሽ ወጥታ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን በጥናት እና በውጤት ተመስርታ መሥራት እንደሚኖርባትም አስገንዝበዋል፡፡ በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጎላ የመጣው የፐብሊክ እና ዲጂታል ዲፕሎማሲ ለግብጽ ሴራ ፍቱን መድኃኒት እንደኾነም አንስተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው ባሕር ዳር ፡ (አሚኮ)

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም ሆነ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ እንግዶች… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን ተከትሎ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እርስ በርስ የሚረዱበትን አዲስ የጋራ መከላከያ ስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት መስማማታቸውን… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን የከፋ ቀጣት ይጠበቃቸዋል።… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ክንፈ ዳኘው በቀረበባቸው ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባሉ
ለረዥም ጊዜ ሳንጠቀምባቸው የቆዩ የጎግል አካውንቶች ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2