10 ሚሊየን ብር የሚገመት ጥፍጥፍ ወርቅ ከግል ተበዳይ አስፈራርተው ወስደዋል የተባሉ ግለሰቦች በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰሱ፡፡ ክሱ የቀረበው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ሲሆን÷ችሎቱ ዛሬ ከሰዓት በኃላ የክሱን ዝርዝር በንባብ አሰምቷል።
ተከሳሾቹ 1ኛ ተከሳሽ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ አባልና የቀድሞ ወታደር የነበረው ሻለቃ ፀጋዬ ሃይሉ፣ 2ኛ ደበበ ገመዳ፣ 3ኛ ሰናይት ብርሃኑ፣ 4ኛ አለማየሁ ደነቀ እና 5ኛ አሚር ወርቁ ናቸው።
የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ሁለት የሙስና ወንጀል ክሶችን አቅርቦባቸዋል።
ተከሳሾቹ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ/ለ እና አንቀጽ 33 እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1ሀ /ሐ እና ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ እና በወንጀል የተገኘ ንብረትን ወይም ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የወንጀል ክስ ነው የተመሰረተባቸው።
በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም የግል ተበዳይ ከትግራይ ክልል ይዞት የመጣውን 1 ሺህ 611 ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ ለማሰራት ወደ ፒያሳ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር አብረው ሲጓዙ 3ኛ ተከሳሽ 1ኛ፣2ኛና 4ኛ ተከሳሾች የመንግስት የፀጥታ አካላት መስለው ወርቁን እንዲወስዱበት ለማድረግ በመስማማትና ተከሳሾቹ ወደ ሚገኙበት ቃተኛ ተብሎ ወደሚጠራ ምግብ ቤት ምሳ እንብላ በማለት የግል ተበዳይን ወደ ምግብ ቤቱ ወስዳለች፡፡
ምግብ ቤት እንደደረሱ 1ኛ ተከሳሽ የወታደር ልብስ በመልበስ እራሱን ወታደርና የፀጥታ አካል አስመስሎ የግል ተበዳይ ወደነበረበት ተሽከርካሪ በመቅረብ ተበዳይ ተቀምጦበት ወደነበረው የሹፌር ወንበር እንዲወርድና ከኋላ እንዲቀመጥ ካደረገው በኋላ እራሱ ተከሳሹ ወደመኪናው ገብቶ ጋቢና ከተቀመጠ በኋላ መኪናው በሕገወጥ መንገድ ሀገር ውስጥ የገባና ነው በማለትና መኪናውን በጂፒኤስ እየተከታተሉት መሆኑን በመግለጽ መኪናው ይታሰራል ሲል እንዳስፈራራ በክሱ ተጠቅሷል።
ሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ የመኪናው የኋላ ወንበር ላይ ገብቶ በመቀመጥና ሽጉጥ አውጥቶ የግል ተበዳይ ጭንቅላት ላይ በመደቀን የግል ተበዳዩ ይዞት የነበረውን የዋጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ 1ሺህ 611 ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ ነጥቆ መውሰዱ በክሱ ተመላክቷል።
ወርቁን ከነጠቁት በኃላ ተበዳዩን ከመኪናው በማስወረድ በ3ኛ አሽከርካሪነት ጥፍጥፍ ወርቁን ይዘው በርቀት ሆኖ ሲጠብቃቸው ከነበረ 4ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ወርቁን ፒያሳ አካባቢ በመውሰድ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ለሌለው ለ5ኛ ተከሳሽ በ3 ሚሊየን 415 ሺህ በመሸጥ እና ገንዘቡን በተለያየ መጠን በመከፋፈል ለግል ጥቅም አውለዋል በማለት ዐቃቤ ሕግ የተከሳሽን ሚና ዘርዝሮ ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቧል።
ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በተረኛ ችሎት ቀርበው ክሱ ከደረሳቸው በኋላ የክስ ዝርዝሩ በችሎት በንባብ ተሰምቷል።
የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ በችሎት ከተነበበ በኃላ ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግና የክስ መቃወሚያ ለማቅረብ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ተረኛ ችሎቱን ጠይቀዋል።
ዐቃቤ ህግ በኩል በጠበቆች የቀጠሮ ጥያቄ መቃወሚያን በሚመለከት አልቃወምም በማለት አስተያየት ሰጥቷል።
ይሁንና ተረኛ ችሎቱ ግን የተከሰሱበት አንቀጽ ዋስትና እንደሚያስነፍግ በማብራራት ተከሳሾቹ የክስ መቃወሚያ እስኪያቀርቡ ድረስ ባሉበት ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
የተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ለነሐሴ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ ፋና
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደርበኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት ጽንፍ ተፈርጀው ይተቻሉ። በአንድ በኩል “ለኦሮሞ ሕዝብ ማንነትና ታሪክ የታገሉ ምሁር”… Read more: ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር
- እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ በኢትዮጵያ ምድር እየኖሩ የኤርዶኻን መልእክተኛ ለመሆን የሚንፈራፈሩ ወኪሎች፣ እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ ይሻላል። የዓለም… Read more: እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…
- የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙየአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር አኔት ዌበር Dr. Annette Weber ለኤርትራ መሪዎች ጣልቃ ገብነታቸውን እንዲያቆሙ አሳስበው መመለሳቸውን ተልትሎ በግል… Read more: የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ






