Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ያበደው  የመጸዳጃ ቤት ጽሁፎችና … ለመረጃነት አይበቁም
ያበደው

የመጸዳጃ ቤት ጽሁፎችና … ለመረጃነት አይበቁም

Ethioreview newsEthioreview news—September 19, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኡ ኡ ኡ ኡ …. ለሚሰማ፤ ሰሚ ካለ … ኡ ኡ ኡ ኡ መንግስትን ውቀጠው። ቀጥቅጠው። ዘልዝለው። ባለስልጣኑንን ማንም ይሁን ማን አትልቀቀው። መተንፈስ እስኪያቅተው አበራየው፣ አንገዋልና ለነፋስ ስተው። ስራው ያውጣው። መረጃ!! ተጨባጭ የሆነ መረጃ፤ የሚናደፍ ምላስ ሳይሆ መረጃ ግድ ነው። ይህ ሳይሟል ከመጸዳጃ ቤት፣ ከሰገራ ቤት መረጃ ማጣቀስ ቅዳቂነት ነው። የሽንት ቤት መረጃን ፈጽሞ አታጣቅስ። የሽንት ቤት ግድግዳ ላይ ጽሁፎች መረጃ ሆነው አያውቁም። የመጸዳጃ ቤት ጽሁፎች አጣቅሶ መንግስትንና ሃላፊዎችን ማራከስ አይነፋም። ቧልት ነው። የጎ ፈንድ ገበያ ነዳጅ ነው። የዲጂታል አቁማዶ / መለመኛ ነው። ውሎ አድሮ ያዋርዳል። ያሳፍራል። የልጅ ልጅ ያፍርበታል። የልጅ ልጅ የሚወርሰው ጠባሳ ይሆናል። ያበደው እንቅጭሁን ይናገራል።

  • ስቶኮልም ሲንድረም … ያሰቃየህን የመናፈቅና የማፍቀር፣ እንዲሁም አዳኝ አድርጎ የማሰብና የማመን በሽታ ነው። ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ “በሬ ያኮላሸውን” እንደማለት ነው። በሬው ጨው መላሱን እንጂ ቂጡና ማጅራቱ አብጦ ለእርድ እንዲሆን ጨው አልሰው ብልቱን እመቀመጫው ድረስ እንደቀጠቀጡት አይገባውም። የቦሰና ረቂቅ እይታ ነው። ጨውና በሬ!!

“ቦሰና ቤተሰብ፣ ሚስት፣ ልጆች፣ ዘመድ፣ አዝማድ፣ ወዳጅ፣ ፈርሃ ፈጣሪ ያላቸው” ትልና ጣልቃ ገብተው ለማረቅ ለምን እንደማይሞክሩ ስታስብ ትነግፈገፋለች። ሰው አፈናቅሎ፣ አጋድሎ፣ አገር ላይ መርዝ እየረጩ በሚሰበስቡት ገንዘብ የምታጌጪ ሚስት፣ ልጆች፣ ይህንኑ የዕርም፣ የዕንባና የብዙሃን ስቃይ ድምር ሃብት እየሰበሰባችሁ ልጆቻችሁን የመትመግቡ ዋ!! ዋ!! ዋ!! ትግራይ፣ አማራ፣ ሃዋሳ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊሌ፣ ቤኒሻንጉል … እናቶች፣ አቅመ ዳካሞች፣ አዛውንቶች፣ እመጫቶች፣ በጫካ የተወለዱ ህጻናት ሲቃ ወደ ሰማይ ይጮሃል … ጫካ ውስጥ የዛፍ ስር ይዛ አምጣ የተገላገለች ወይም የቀበረች የምጧ ስቃይና ሃዘኗ እላይ ይጮሃል…. ያበደው አነባ። ምን ያለ ጭካኔ … ምን እንሁን? ምን እስኪሆን ይሆን በማተራመስ፣ አተራምሶ ኪስ በመሙላት የሚዘለቀው? ይህም እንደ ኩራት ” አይበገሬው፣ አንበሳው፣ ትንታጉ …” እያሰኘ …. የሚዘፈነው፤ ለዚህ ክፋት በሰልፍ ግብር በኦንላይን የሚገባለት? ያበደው ተወራጨ። ህዝብ አዳም የመርዝ አካእፋፋዮችን ” ሰርተህ ብላ” እንዳይል፣ “ከጌቶቻቹህ” ተቀበሉ ሲል አበሻቅጦና አራክሶ ከማባረር ይልቅ ” በጎ ፈንድ” ይመዘገባል። በሱፐር ቻት ስሙ ሲጠራ፣ ስሟ ሲነሳ እየወበቀው፣ እየወበቃት ደም ተፍታ የሰብሰበችውን ታስረክባለች። አያስረክባል። በዘምናዊ ለማኞች መደንዘዝ!!

በማያውቁት፣ በሌሉበት የታረዱ፣ የተሰቀሉ፣ ስቅላት በቂ ስላልነበር ተሰቅለው የድንጋይ ወገራ የተመረቀላቸው፣ ይህ ሲሆን ፊልም እየቀረጹ መዋጮ የሚሰበስቡ፣ እምባቸው ወደ ላይ ፈሷል። ቤታቸው እያነደድክ ስትገልፍጥ የነበርክ ግፍህ ሰማይ ነክቷል። እንዲህ ያለውን ቪዲዮ የምታሰራጭና ተጨማሪ ደም ለመጋት ሴራ ስትጎነጉን የነበርክ ሁሉ የአጅህን አግኝተሃል ወይም ታገኛለህ። ማንም ሁን ማን የስማዩ አባት ያውቅሃል። በቤትህ እንደ በለአም መዓት ይወርድብሃል። እንዳሴርክ አትኖርም። ባለ ጊዜም ሁን ተሰናባች ሁልህም ትሰፈራለህ። በሁሉም አቅጣጫ ደም የምትራጩ ይብቃችሁ። ስላበጣችሁና በልመና ስላሽከረከራችሁ … ያበደው ተናናቀው!! አተራማሾቹ ሊያተራምሱ ስቱዲዮ ከመግባታቸው በፊት ክትፎ ሲበሉ የተራገመቸው ሴት ፊቱ መጣችበት። ” ደም ብሉ፣ አፈር ብሉ” እያለች ተራግማለች። እመቤቴ ብላ እዛ እያፋረሱ እዚህ ራሳቸውን ሲገነቡ ለምን በዝምታ እንደምታይ ወቅሳለች። እነሱን ይሰለቅጡ ነበር። ያንቃርሩ ነበር። ለካ ለንግግር ያመች ዘንድ “ያስተፈስህ” ይወሰዳል!!! ያበደው ዞረበት።

… ሁሉም አንባቢና አነብናቢ ስለሆነ ጩኸቱ አሳክሯል። ከሁሉም ወገን የሚተፋው አንድ ላይ ሆኖ ለማድመጥ አይመችም። ጃዋር ገብቶት ይሁን ለስልት “ስለፈልፍ ስለኖርኩ ላድምጥ እስኪ ብዬ ዝም አልኩ አለ” ግን መናገር ጀመረ። ይህ ድምጽ ጤነነቱ ባይረጋገጥም በሁካታና ጩኸቱ መካከል ተሰምቷል። ኮሮጆ ጎድሏል መሰል የአውሮፓ ቱር እቅድ ወጥቷል። ለጊዜው ኦሮሚያ በትራክተር እያረሰ ነው። አማራም ከጥይት ጩኸት ወደ ትራክተር እየዞረ ነው። ኢትዮጵያን አንድ የህብረትሰብ ጤና ዶክተር እንዳሸነፏትና የታላላቅ ሰው ወዳጅ መሆናቸው ሲራገብ ነበር። አሳቡ “የጀግኖቹን መንደር” ለመቀላቀል የሚደረግ ርብርብ ይመስላል!! “የጀግኖቹ መንደር!!” አብዮታዊት ትህነግ ወይም ሞት በአደባባይ!! ታስሮ ጀግና መባልና እርጥባን መልቀም!!

More stories

በተዓምር ካልሆነ እንዴት? የነቀዘ…

September 8, 2023

ያ – ሰፈር በሽሮ የሚፈተጉ በከሎች ? ዘይት ብርቅ ነው?

September 19, 2023

ቅዠት ራዕይ ነበር ፤ቅዠት ኢሳያስ ዘንድ ነበር፤ ቅዠት ራሱ ኢሳያስ ነበር፤ ቅዥት ኢሳያስን ሆኖ ኖሮ ኖሮ …. 

June 24, 2025

” ትግሉ እዚህ ደርሷል፣ ውሮወሻባዬ”

June 18, 2024

ማታ ማታ አየሩ ይታጠናል። አማትበው የሚጀምሩ “እናትና ልጅ ይመስገኑ” ብለው የስድብ አረር ያጎርፋሉ። ከዛ ሲጨርሱ ” የደንቧን፣ የአገልግሎቴን እንዳትረሱ። ጣል ታል አድርጉ…” ይላሉ። ዲጂታል ለማኞች !! ያበደው ተቆጣ። የኔ ቢጤ እሜዳ ላይ፣ ጎዳና ላይ ቁጭ ብሎ ወይም አቁማዶ ይዞ ይለምናል። ራዳ የኔ ቢጤዎች በዲጂታል መስኮት ይለምናሉ። ቦሰና ” ኤዲያ ሁሉም ለማኞች ናቸው” ትላለች። እውነት ነው። ማታ ምታ ቁጭ ብለው ” ሰማሁ፣ ይመስለኛል” እያሉ የሚቀለቡ፣ ቀለቡ ሲጎድል ” አምጡ” የሚሉ ታዲያ ምን ሊባሉ ነው?

ያበደው ጩኸት ቢጠላም ከጩኸት ማምለጥ አልቻለም። ጩኸት ሰፈሩ ገበያ ነበር። የድሮው መርካቶ ያለው የተለመደው ” እዛው በላች እዛው ቀረች”ና የበርሜል ተራ አይነት ጩኸት አይደለም። ዲጂታል ጩኸት! በዘመነ መገናኛ ውስጥ ደንቁሮ መጮኽ … ደንቁሮ ማደንቆር… በኢትዮጵያ ባንዲራ እየተጠቀለሉ መጮህ!! እዛም፣ እዚህም፣ እወዲያም፣ እወዲህ፣ ማዶ ለማዶ መጮህ፣ መርጨት፣ መርዝ ማሰራጨት … መርዝ እየረጩ ” እርዱኝ” ማለት። እንደምን ከረማችሁ። ያበደው ከሰላምታው በፊት ቀባጠረ!! የሚረጨው ያስቀባጥራል። ሂሮሺማ!!

ግን ግን እውነቱ እንነጋገር ከተባለ እጅግ በጣም ጥቂት ከሚባሉ አገር ወዳዶች በቀር እነማን ናቸው ለሕዝብ ጥቅም ሲሉ የምርመራ ስራ ሰርተው የሚያቀርቡት? ስንት አስገራሚ የምርመራ “ጋዜጠኞችን” አወቅን? እንደው ምን አዲስ ነገር ነገሩን? በማስረጃ አስደግፈው ምን ያህል አገር የሚገነባ ቁስል አከሙ? “አብይ አባይን ሸጠው” ከሚለው የዛር ጩኸት ውጪ ምን ….. ያበደው በወጉ የሚሰሩትን ያከብራል። የፌስ ቡእክ ዜናን እየገለበጡ ሟርት የሚያደርጉትን ደግሞ ” ጊዜ የሰጠው ቅል .. ” ይላቸዋል።

የታክሲ ውስጥ ጽሁፍ፣ የግድግዳ ላይ ጽሁፍ፣ የሽንት ቤት ውስጥ ጽሁፍ አዎ የሽንት ቤት፣ የሰገራ ቤት ጽሁፍ ምንጩ ይታወቃል? ማን እንደቀባው የሚያውቅ አለ? እሽንት ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ የጻፈን ያየ ማን ነው? …. መልሱ!! ስሙንና መልኩን ደብቆ በየትኛውም አድራሻ የሚጽፍ ማን ነው? ማን ያውቀዋል? ለምን ይደበቃል? ምን ያስደብቀዋል? ይህ ከሰገራ ቤት ጽሁፍ በምንጭነት በምን ይለያል? ያበደው ይጠይቃል? ማንህ መልስ ያለህ? አሁንም ያበደው ይጠይቃል? መልስ የለም። ዝም ብሎ ተቀብሎ ማከፋፈል። መርጨት። አከፋፋዩን ” ትንታግ፣ የቁርጥ ቀን” እያሉ ማወደስ። ያበደው ” ደግነቱ ጥቂት ናችሁ። ኢትዮጵያ 130 ሚሊዮን ናት” ያለው እንቁራሪት ነጋዴ ታወሰው። አይ ቅኔ!! ፈገገ!!

ከፈርንሳይ ወደ ስድስት ኪሎ ከዛም ወደ ጃፓን ኤምባሲ ለማምራት እንደሶምሶማ እየሮጠ ” እኮ ነገረኝ” ይላል!! አዎ የሰገራ ቤት ጽሁፍ ምንጭ አድረገህ ለሌላ ታሰራጫለህ?” …. በለቤቱ ያልታወቀ ጽሁፍ፣ ቪዲዮ፣ አውዲዮ፣ ደብዳቤ … ከሰገራ ቤት የግድግዳ ጽሁፍ በመን ይለያል? መልስ የለም፤ ያበደው አሁን ጮክ አለ ቁልቁል ወደ ስድስት ኪሎ እየተምዘገዘገ …

“ታመና። ማላመጥ አቁመናል። ማየትና መመርመር ትተናል። ያገኘነውን ጥቅልል እየዋጥን ታንቀናል። መታነቃችን ጣር ሆኖብናል። ጣሩ ለሌሎችም በሚሰማ ደረጃ ስለሆነ ይረብሻል … አጣራ፣ መርመር፣ ዝም ብለህ አትዋጥ፣ አኝክ፣ አልም፣ ….” ያበደው ስድስት ኪሎ ደረሰ። ዘንዶ ልብ እንደገዙ መስማቱ አስታውሶ ” አርፋችሁ ተማሩ ብሎ ወደ አራት ኪሎ ሮጠ። አራት ኪሎ!!

አራት ኪሎ ለመግባት አቅደው የሚተጉ የሉም። ጥሩ አማራጭ ለመሆን የሚለፉ የሉም። ሁሉም አቋራጭ ፈላጊዎች ናቸው። አቋራጩ ደግሞ የትርምስ መንገድ ማበጀት ነው። ትርምሱ ደግሞ ፓኬጆች አሉት። ፓኬጅ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት … እያለ ይሄዳል። አስፈሳሚዎቹ የሚጮሁት ናቸው። ቦሰና እንዲህ ትላለች። “ሰው እንዴት ቀን በቀን በፈጠራ ሲሳደብ ይውላል”

በኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ሆስፒታል ቢሰራ ዜና አይደለም። የተፈናቀሉ ቤታቸው ሲመለሱ ዜና አይደለም። ስንዴ ማምረት፣ ትራክተር ማደል፣ የደሃ ቤት መጠግን፣ ቆሻሻ መጥረግ፣ ችግኝ መትከል፣…. ውግዝ ነው። እንኳን ዜና ሊሆን ለርግማንም አይበቃም…. ያበደው “እቺ ተአምረኛ አገር” አለና ውጭ ጉዳይ ፊት ለፊት ቆመ። መናፈሻውን አየው። አብነት አትሮት ነበር። የተተናበረው የኢትዮጵያ ኢንዘስትመንት መንገድና የህዝብ መናፈሻ ይሸጥ ነበር። ተመስገን ዛሬ አርንጓዴ አምረፊያዎች እየተሰሩ ነው። ያበደው “ይቅርታ” አለ። በፈረሰ ልቡናቸው ግንባታ ስርስር እየሄዱ ” ሊያወድሙት ነው? ሊያጠፉት ነው? ሊሸጡት ነው …. የሚሉ ነቀዞችን አስታወሰ። አባይ ግድብ ስንቴ ተሽጦ፣ ስንቴ ፈርሶ፣ ስንቴ … “ምንጫችን ከውርልድ ባንክ ነገረን” ብለው አብይ አባይን መሸጡን የነገሩን እስካሁን ይቅርታ አልተየቁም። ዛሬም “ምንጫችን” እያሉ ነው …. አንተ ተከትልህ አራባ፡፤ አገርህ ላይ መርዝ እርጭ … ሳታስተውል በትነህ፣ ስትበተን ታርፈዋለህ ” እጄን በጄ …”

ማታ ማታ አየሩ ይታጠናል። አማትበው የሚጀምሩ “እናትና ልጅ ይመስገኑ” ብለው የስድብ አረር ያጎርፋሉ። ከዛ ሲጨርሱ ” የደንቧን፣ የአገልግሎቴን እንዳትረሱ። ጣል ታል አድርጉ…” ይላሉ። ዲጂታል ለማኞች !! ያበደው ተቆጣ። የኔ ቢጤ እሜዳ ላይ፣ ጎዳና ላይ ቁጭ ብሎ ወይም አቁማዶ ይዞ ይለምናል። ራዳ የኔ ቢጤዎች በዲጂታል መስኮት ይለምናሉ። ቦሰና ” ኤዲያ ሁሉም ለማኞች ናቸው” ትላለች። እውነት ነው። ማታ ምታ ቁጭ ብለው ” ሰማሁ፣ ይመስለኛል” እያሉ የሚቀለቡ፣ ቀለቡ ሲጎድል ” አምጡ” የሚሉ ታዲያ ምን ሊባሉ ነው?

የታክሲ ውስጥ ጽሁፍ፣ የግድግዳ ላይ ጽሁፍ፣ የሽንት ቤት ውስጥ ጽሁፍ አዎ የሽንት ቤት፣ የሰገራ ቤት ጽሁፍ ምንጩ ይታወቃል? ማን እንደቀባው የሚያውቅ አለ? እሽንት ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ የጻፈን ያየ ማን ነው? …. መልሱ!! ስሙንና መልኩን ደብቆ በየትኛውም አድራሻ የሚጽፍ ማን ነው? ማን ያውቀዋል? ለምን ይደበቃል? ምን ያስደብቀዋል? ይህ ከሰገራ ቤት ጽሁፍ በምንጭነት በምን ይለያል? ያበደው ይጠይቃል? ማንህ መልስ ያለህ? አሁንም ያበደው ይጠይቃል? መልስ የለም። ዝም ብሎ ተቀብሎ ማከፋፈል። መርጨት። አከፋፋዩን ” ትንታግ፣ የቁርጥ ቀን” እያሉ ማወደስ። ያበደው ” ደግነቱ ጥቂት ናችሁ። ኢትዮጵያ 130 ሚሊዮን ናት” ያለው እንቁራሪት ነጋዴ ታወሰው

በየመድረኩ ፈሱን ሲረጭ የነበረ “ጨዋ” ዛሬ ተንታኝ ነው። አዋቂ ነው። ዞሮ ዞሮ ሸቃይ ነው። ብቻ ሁሉም “ሱፐር ቻት” እያሉ ይቀፍላሉ። ተቀፋዮች ደም ተፍተው ከሚያገኙት ይሰጣሉ። ድርጎ ይሰፍራሉ … ሁሉም መርዙን እየረጨ ይለምናል። የማይለምኑ ጥቂት ናቸው። ሊለመናላቸው የሚገባቸው ብዙ አሉ። ግን ምርጫው “አተራምሰው፣ ነቃቅለው፣ ግፋ በለው፣ ቁረጠው፣ ድፋው፣ አፈናቅለው፣ አቃጥለው … ” የሚለው … ነው። ያበደው ከውጭ ጉዳይ ቁልቁል ተንደረደር። ለምን ወደ ጃፓን ኤምባሲ መሄድ እንደፈለገ አለገባውም። ግን እየሄደ ነው።

አሁን ምንጭ ማጣራት የፋራ ሆኗል። “ግፋ በለው” እርዳና ነው። ዘር ለይቶ የጅምላ ፍርድ መፍረድ አዋጪ ስራ ሆኗል። ሰሞኑንን ክፍት የስራ ማስታወቂያ ይወታል። የገቡትን ለመተካት የታሰበ ይመስላል። የብር ችግር የለም። መስፈርቱም ቀላል ነው። በጨበታ መነዳት ዋናው መስፈርት ሲሆን፣ ትንታጉ፣ አነጋጋሪው፣ አይበገሬው፣ ግንባሩ የማይታተፈው፣ የቁርጥ ቀን ልጅ፣ የታላቅነት ማማ፣ የጀግና ውሃ ልክ፣ የሞራል ጥግ፣ የክብራችን ምሶሶ፣ የኢትዮጵያ ወርቅ…” የሚሉትን ዝማሬዎች ያለ አፍረት መቀበል የሚችል። ከዚያ በተጨማሪ በሶስቱ ስላሴዎችና በአላህ የሚያምን። ያበደው ምራቁን ጢቅ አደረገ…. ኢትዮጵያን በወሬ፣ በፈተራ ሂሮሺማና ናጋሳኪ ማድረግ … በወሬ ኒኩለር ጢስ ማፈን … ያበደው ጃፓን ኤምባሲ ለመሄድ ያሰበበት ጉዳይ ታወሰው። ጃፓን አሁን ድረስ የመርዙ መዘዘ የታተመባቸው ልጆች እየታቀፈች ነው። ልብ ያባል!! ሌላ ቀን ወደ ኢምሬትስ ይሄድና ” እኔ በምሰራላችሁ ቤተ መንግስት ለምን ትርፍ ነገር ትናገራላችሁ። አሮጌዎቹ ቤተመንግስቶች ሙዜየም ሲሆኑ ከአፍሪካ አንደኛ ሙዜይም እንደሚሆኑና ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደሚያስገኙ እንዴት ማስላት አቃታችሁ” ብለው እንዲላጡብን ማድረግ የያበደው ዕቅድ ነው። መሳይ መኮንን ምን አለ? ” አሁንስ ይህ መንግስት አበዛው” ድሮስ ? በሉና ጠይቁልን?

ስቶኮልም ሲንድረም … ያሰቃየህን የመናፈቅና የማፍቀር፣ እንዲሁም አዳኝ አድርጎ የማሰብና የማመን በሽታ ነው። ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ “በሬ ያኮላሸውን” እንደማለት ነው። በሬው ጨው መላሱን እንጂ ቂጡና ማጅራቱ አብጦ ለእርድ እንዲሆን ጨው አልሰው ብልቱን እመቀመጫው ድረስ እንደቀጠቀጡት አይገባውም። የቦሰና ረቂቅ እይታ ነው። ጨውና በሬ!! ቁራዎቹም እነደዚህ ናቸው። የልመናና የመቃተት ዘመናቸውን እንደ በሬው ዘንግተው ጨው ይልሳሉ። ይመኛሉ። ያንን ጨው !! ዲያስፖራ ሞኙ ሞኙ … ኪሱን ዘርግፎ ያበደው ሳቀ !! ምጽ!!

አሁን መሽቷል። ለአይን ያዝ እያደረገ ነው። ደጎልም በሃሳብ ያበደን ይናፍቃል። ደጎል ልዩ ውሻ ነው። ዩቲዩብ ላይ አማትበው ጀምረው የሚሳደቡትን፣ ኢየሱስ ብለው የሚነግዱትን ሲያይ ዘሎ ፊቱ ያዞራ። … ቦሰና እንደወትሮው ታጥናለች። ሙቀት ሲያምራት ቀድሞ ያናጫታል። ግን ከሰኮንዶች ነው። ማገዶ አትፈጅም። ወዲያው ክር፣ ወዲያው መርፌ ሲያሻትም ጂዶ ትችልበታለች። ቦሰና ስኳር ናት። ለቤቷም እመቤት ናት። ሙገሳ አትወድም። ሁሉም ነገር ለጋራ ጥቅም ሲባል እንደሆነ ታምናለች። ቦሰናና የግል ናት። ቤት ያላችሁ ግቡ። በቤታችሁ አግቡበት። የመጸዳጃ ቤት ጽሁፍ ለመረጃነት አይበቃም። ሰላም ሁኑ!!


    yabedew
    FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
    እንደ ሱዳን የመሆን ምኞትና ጥድፊያ – የነጻ አውጪ ጋጋታ
    ያ – ሰፈር በሽሮ የሚፈተጉ በከሎች ? ዘይት ብርቅ ነው?
    Related posts
    • Related posts
    • More from author
    News2

    ቅዠት ራዕይ ነበር ፤ቅዠት ኢሳያስ ዘንድ ነበር፤ ቅዠት ራሱ ኢሳያስ ነበር፤ ቅዥት ኢሳያስን ሆኖ ኖሮ ኖሮ …. 

    June 24, 2025
    ያበደው

    ” ትልቅ ስኬት አሳክተናል” የጃዋር ኃይሎጋዬ ሆ!

    November 12, 2024
    Events

    ” ትግሉ እዚህ ደርሷል፣ ውሮወሻባዬ”

    June 18, 2024
    Load more
    Read also
    News

    ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

    April 26, 2026
    WORLD

    ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

    April 26, 2026
    News

    “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

    April 26, 2026
    WORLD

    አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

    April 26, 2026
    WORLD

    የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

    April 26, 2026
    WORLD

    የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

    April 26, 2026
    Load more
    Recent Posts
    • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
    • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
    • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
    • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
    • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
    • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
    • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
    • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
    • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
    • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
    • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
    • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
    • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
    • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
    • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
    Social networks
    FacebookLikes
    X TwitterFollowers
    PinterestFollowers
    InstagramFollowers
    YoutubeSubscribers
    VimeoSubscribers
      VOE
      The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

      MENU

      NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
      © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
      • CONTACT
      • law
      • INTERVIEW
      • ያበደው
      • ECONOMY
      • Home demo times
      • VOE VIDEO
      • ENGLISH PAGE
      • Home Demo default 2