በቀድሞ አጠራሩ የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በአዲሱ አወቃቀር ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ላይ የሒሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ባደረገው የሒሳብ ኦዲት ምርመራ፣ 65 ቢሊዮን ብር የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ ተገለጸ፡፡
በአገሪቱ ከሚገኙ ትልልቅ ድርጅቶች መካከል አንዱ የነበረው ሜቴክ ከተመሠረተ ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ የነበረው የሒሳብ ኦዲት ከተሠራ በኋላ ከፍተኛ ኪሳራ መገኘቱን የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ሱሌማን ደደፎ (አምባሳደር) ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።
” የሒሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በሠራው ሪፖርት መሠረት 65 ቢሊዮን ብር የት እንደደረሰ ስለማይታወቅ፣ የኦዲት ሪፖርቱን መሠረት በማድረግ መንግሥት እንዲሽረው (Write off) ተጠይቆ ውሳኔ አግኝቷል ” ብለዋል፡፡
በዚህም መሠረት የተገኘው የኪሳራ ገንዘብ በዕዳ እንዳይመዘገብ መንግሥት ሽሮታል (Writeoff) ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
በኦዲት የተገኘው ገንዘብ ምንም ሥራ ላይ ያልዋለና በወቅቱ የነበሩ አመራሮች ተከፋፍለው የወሰዱት በመሆኑ በዚህ ተቋም አማካይነት የአንድ ህዳሴ ግድብ መሥሪያ ብር መዘረፉን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ወታደራዊ ምርቶች ለብቻ እንዲሆኑ በመክፈል እንደ አዲስ የተዋቀረው ግሩፑ፣ የደረሰበትን ሀብትና ዕዳውን የመለየትና ጥፋቶችን በመመርመር በሕግ የሚገዛ አገራዊ ተቋም ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የቀድሞው ሜቴክ ከተመሠረተበት ጀምሮ እስካሁን ያለውን አጠቃላይ ሒሳብ ኦዲት መደረግ የተጀመረ መሆኑን፣ እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ ያለውን በማጠናቀቅ ከ2012 ዓ.ም. በኋላ ያለው በሒደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኦዲት ሪፖርቱ ግኝት መሠረት ከኪሳራው በተጨማሪ፣ በሀብት ደረጃ የተመዘገቡት እንዲሸጡ በማድረግ ለግሩፑ ገቢ እንዲሆን እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት ያለ አገልግሎት የተቀመጡ 5 ቤቶችን ወደ ገንዘብ ለመቀየር በቅርቡ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል፡፡
” የቀድሞ የድርጅቱ አመራሮች የዝርፊያ ሥልት አሁንም ድረስ በተለያዩ መንገዶች እየቀጠለ በመሆኑ፣ ከኪሳራ እንዳይላቀቅ ማነቆ እየሆነ ነው ” ብለዋል፡፡
በቅርቡ ይፋ የተደረገው የፓወር ኢኪዩፕመንት ፋብሪካ ውስጥ የሚገኙ ስምንት አመራሮች #ከብረት_ስርቆት ጋር በተገናኘ መያዛቸው አንዱ ማሳያ መሆኑን፣ ሌሎች አመራሮችም ቀስ በቀስ ተጠያቂ እንደሚደረጉ አሳውቀዋል።
መረጃው የሪፖረተር ጋዜጣ ነው።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም።… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






