Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  OPINION  ካይሮ በፍልስጤማዊያን ደም እና በኢትዮጵያ ውኃዎች መካከል
OPINION

ካይሮ በፍልስጤማዊያን ደም እና በኢትዮጵያ ውኃዎች መካከል

Ethioreview newsEthioreview news—February 12, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

1971 ላይ የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ተፈረመ – በዚህም ግብፅ ለእስራኤል የሀገርነት ዕውቅ ሰጠች – የእስራኤል ባለሙያዎችም ‘ጣና በለስን’ ሳይውሉ ሳያድሩ ለቀው ወጡ…. አሁንም ቢሆን የካይሮ መንግስት ፍልስጤማዊያን ከጋዛ መሬት ሙሉ በሙሉ ተሰድደው መሬቱ ለእስራኤል ቢተላለፍ ከአልሲሲ ግላዊ አቋም አኳያ ወደ ኋላ እንደማይል፣ የቲራን እና ሳናፊር ደሴቶቻቸውን ለእስራኤል ስትራቴጂክ ፍላጎት መሟላት ለሳኡዲ ያስተላለፉበትን የቅርብ ጊዜ ውሳኔ ማውሳት በቂ ነው።

የዓባይ:ልጅ

~የግብፅ እና የእስራኤል ፍጥጫ፤ ካይሮ የካምፕ ዴቪድ የሰላም ስምምነትን እንደምታፈርስ ዛተች~

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በተለይም ከካይሮ እስከ አንካራ፣ ከጋዛ እስከ አፍሪቃ ቀንድ ከሚስተዋሉ የአሰላለፍ መልኮች ጋር የሀገራት መሪዎችና የስለላ ኃላፊዎች ወደ ካይሮ ጉዞ የማድረጋቸው አንድምታ፣ ከጋዛ/ሐማስ ጉዳይ ባሻገር ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ስንስል ያላቸው ቁማሮችም ይመስላሉ —። ሰሞነኛው የግብፅና እስራኤል ‘ታንቲራ’ የካምፕ ዴቪድ ስምምነትን መንካት መጀመሩ ይበልጥ ሀገራችንን የሚመለከት ያደርገዋል። ካይሮ በዚሁ የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ወቅት ኢትዮጵያን የተመለከተው ይዘት ቁልፍ ሆኖ የተካተተ እንደነበርና በዚህም በሀገራችን የከፍታ ፕሮጀክቶች ላይ ጥቁር ጥላውን አሳርፎ ስለመቆየቱ የሚያወሳውን ታሪክ እዚጋ ልብ ይሏል…።

More stories

በካይሮ የተዘረጋው ሰሞነኛ ሴራ ይፋ መሆኑ ጩኸት አስነሳ

October 9, 2022

ኧረ የሕግና የሕሊና ያለህ ?!

November 25, 2022

“ከጊዜያዊ መፍትሄ ዘላቂ ጥቅም አይገኝም!” ዐቢይ አሕመድ

April 9, 2023

ብራስልስና መቀሌ

February 19, 2022

እስከ ትናንት ድረስ ከወጡ ዓለም አቀፍ ዘገባዎች ውስጥ አበይት የሆኑትን ብቻ ብንመለከት፤
▪️የእስራኤሉ መሪ ቤንያሚን ናታንያሁ በራፋህ ለሚደረገው ወታደራዊ ወረራ ለመዘጋጀት ተጠባባቂ ወታደሮቻቸው እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
▪️ግብፅ ራፋ ላይ እስራኤል ያቀደችውን ጥቃት ፈፅሞ አልቀበለውም’ አለች።
▪️”ግብፅ በሰሜን ምስራቅ ሲና ከእስራኤል በሚያዋስናት ድንበር 40 ታንኮች እና ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎቿን አሰማራች።”
▪️”የእስራኤል ጦር በጋዛ ድንበር ወደምትገኘው ራፋህ ከተማ የሚገፋ ከሆነ 45 አመት የዘለቀውን የካምፕ ዴቪድ ስምምነት እንደምትዘርዝ ግብፅ ዛቻ አሰማች”
▪️”ሳዑዲ እና UAE እስራኤል በራፋህ የምታደርገውን ዘመቻ በፍፁም እንደማይቀበሉትና አደገኛ መሆኑን አስታወቁ”

በዛሬው ዕለት ደግሞ ተከታዮቹ ክስተቶች ተስተውለዋል፦
▪️”ግብፅ የሚሳኤል መከላከያ ስርአቶችን ወደ ጋዛ ሰርጥ ድንበር እያንቀሳቀሰች ነው። በቅርብ ጊዜ ውስጥም የእስራኤል ወታደሮች እዚሁ ቦታ(ራፋህ አካባቢ) ሊታዩ ይችላሉ።
▪️”እስራኤል በራፋህ የአየር ድብደባ ጀመረች”
▪️”እስራኤል የራፋ ዘመቻዋን በተመለከተ ከምእራባዊያን የቀረበላትን ጥሪ ውድቅ አደረገች”
▪️”የ CIA ዋና ዳይሬክተር William J. Burns በነገው ዕለት ወደ ካይሮ ያቀናል።”
ዳይሬክተሩ ከቀናት በፊት (ጥር 18, 2024), ሞቃዲሾን ጎብኝተዋል። እስራኤልንም በተመሳሳይ..።
▪️”የቱርኩ መሪ ኤርዶኻን ከነገ በስቲያ ረቡዕ ካይሮን ሊጎበኙ ነው”
▪️”የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒ ካይሮን ሊጎበኙ ነው። የኳታር ጠቅላይ ምኒስትርም በተመሳሳይ..።
.
. እዚህ ላይ ካይሮ የካምፕ ዴቪድ ካርድን እንደማስፈራሪያ መምዘዟ እስካሁን ድረስ ከ 26 ሺህ በላይ የፍልስጤማዊያን ህይወት ከተቀጠፈበት የጋዛ ቀውስ ብሎም ከሐማስ ጉዳይ ባሻገር ካይሮ አሁንም በፍልስጤማዊያን ህይወትና በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ላይ የወጠነችው ሴራ መኖሩን በጉልህ የሚጠቁመን ክስተት ነው – ከካምፕ ዴቪድ የስምምነት ይዘት ውስጤ በተለይም ሀገራችንን የሚመለከተውን ነጥብ ማውሳት ተገቢ ይሆናል።

▪️የካምፕ ዴቪድ ሥምምነት በኢትዮጵያ ላይ፤

የእስራኤልን ምስረታ ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም ከግብፅ መንግስት ዕውቅና ይሰጣት ዘንድ የእስራኤል ዋነኛ አጋር የሆነችው አሜሪካ የካይሮን ስስ ብልት የሚነካ ካርድ መዘዘች…
ይኸውም በወንዛችን ዓባይ ውሃ ላይ ግድብ እንድንገነባ ለደርግ መንግስት ገፀበረከት የማቅረብ ‘አማላይ’ ቁማር ነበር። “በረሃብ የተቸገረ ህዝብህ በምግብ ራሱን እንዲችል ድጋፍ እናርግልህ፤ ወዳጅነታችንም ይበልጥ ይጠናከር” አሉት…

በመቀገል ወደ ‘ጣና በለስ’ የልኡካን ቡድን አሰማሩ፤ ማሽኖችን በመትከል እንቅስቃሴ ላይም እስራኤሎች መታየት ጀመሩ። ዋሽንግተን ፖስት እና ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጦችም ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ ግድብ ለመገንባት ስራ ስለመጀመሯ አለም እንዲሰማው አደረጉ…

በመጨረሻም ለእስራኤል ዕውቅና ከልክሎ የቆየው የወቅቱ የግብፅ መሪ አንዋር ሳዳት አሜሪካን መማፀን ነበረበት “ግድቡን አስቁሚ” በማለት። ይህን ተከትሎ በተደረጉ ንግግሮች 1971 ላይ የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ተፈረመ – በዚህም ግብፅ ለእስራኤል የሀገርነት ዕውቅ ሰጠች – የእስራኤል ባለሙያዎችም ‘ጣና በለስን’ ሳይውሉ ሳያድሩ ለቀው ወጡ…. አሁንም ቢሆን የካይሮ መንግስት ፍልስጤማዊያን ከጋዛ መሬት ሙሉ በሙሉ ተሰድደው መሬቱ ለእስራኤል ቢተላለፍ ከአልሲሲ ግላዊ አቋም አኳያ ወደ ኋላ እንደማይል፣ የቲራን እና ሳናፊር ደሴቶቻቸውን ለእስራኤል ስትራቴጂክ ፍላጎት መሟላት ለሳኡዲ ያስተላለፉበትን የቅርብ ጊዜ ውሳኔ ማውሳት በቂ ነው።
ይሁንና አልሲሲ ይህን ለመተግበር የአረብ አበዳሪ ሀገራት የሆኑት UAE, ሳዑዲ, ኳታርና ሌሎችም አይፈቅዱም፤ በሌላ ወገን ሐማስ እና ኢራን በከፋ ደረጃ የሚሳተፉበት ይሆናል።
ከሁሉም በላይ ግን ይህን ውሳኔ የአልሲሲ ካቤኔ በራሱ እንደማይቀበለው ነው የሚዘገበው። ይህም ግብፅ ከእስራኤል ጋር የከረረ ውጥረት ውስጥ እንዲቀጥሉ ሲያደርግ በአንፃሩ ደግሞ ኢትዮጵያ ከግብፅ የሚፃረር ስትራቴጂክ አጋር እንድታገኝ የሚያደርግ ይሆናል። በተለይም እስራኤል እና ግብፅ ከጦርነት በመለስ የሚፈጥሩት የዲፕሎማሲ መቆራቆሳቸውና እና ርስበርስ በስጋትና በጥርጣሬ እየተያዩ መቀጠላቸው ነው ለአዲስ አበባ የተሻለ ስትራቴጂክ ፋይዳ የሚያስገኘው(እንደሚመስለኝ)።

የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያን ለማደናቀፍ ካይሮ ትላንት የተጠቀመችበት የቁማር ካርድ ለዛሬ የሚያገለግለበት ጂኦፓለቲካዊ ተጨባጭ በአንፃራዊነት የለም ሊባል ቢችልም፣ ጉዳዩን በአንክሮ መከታተልና በፍጥነት የሚለዋወጠውን ቀጣናዊ የብዝኃ ሀገራት ቁማር ታሳቢ ያደረገ ርተግባር ማከናወን የክቡር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ቁልፍ የቤት ስራ የሚሆንይመስላል…
ሠላም ለአለማችን!

Esleman Abay

የዓባይልጅ esleman abay

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚያም ምን ተካቶበታል?
የትግራይ ኢንደስትሪ ቢሮ 217 ኢንዱስትሪዎች ስራ መጀመራቸውን አመነ ወይስ ካደ?
Related posts
  • Related posts
  • More from author
OPINION

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

April 8, 2026
OPINION

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

April 8, 2026
OPINION

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – የሃሰት ትርክ ዘመቻ በደቦ

March 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2