Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ECONOMY  የዋጋ ግሽበትን ወርዷል፤ ብሄራዊ ባንክ ግሽበትን ለመቆጣጠር የወሰደው እርምጃ ውጤት ነው ይላል
ECONOMYNews

የዋጋ ግሽበትን ወርዷል፤ ብሄራዊ ባንክ ግሽበትን ለመቆጣጠር የወሰደው እርምጃ ውጤት ነው ይላል

Ethioreview newsEthioreview news—May 16, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሚያዝያ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 23.3 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ይፋ አድርጓል። መንግሥታዊው ተቋም ይፋ ያደረገው አሀዝ ከቀደመው መጋቢት ወርም ሆነ ከ2015 ተመሳሳይ ጊዜ አኳያ የዋጋ ግሽበት የሚያድግበት ፍጥነት የመቀነስ አዝማሚያ እንዳሳየ የሚጠቁም ነው።

በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት መረጃ መሠረት ባለፈው መጋቢት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 26.2 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ከአንድ ዓመት በፊት ማለትም በሚያዝያ 2015 በአንጻሩ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 33.5 በመቶ ነበር።

“ባለፈው ዓመት የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 33.5 በመቶ ነበር” ያሉት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ ባለፈው ሣምንት ኢትዮጵያ ታምርት በተባለው ንቅናቄ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር “በአሁኑ ጊዜ ወደ 23.3 በመቶ ቀንሷል። ስለዚህ በ10.2 በመቶ ቀንሷል። ይኸ ትልቅ ዕምርታ አድርገን ነው የምንወስደው” ሲሉ ተደምጠዋል

አቶ ማሞ የሚመሩት ብሔራዊ ባንክ በነሐሴ 2015 ሥራ ላይ ባዋላቸው መመሪያዎች እና የፖሊሲ እርምጃዎች የዋጋ ግሽበትን በመጪው ሰኔ ከ20 በመቶ በታች የማውረድ ዕቅድ አለው።

More stories
pp

ወልቃይት – የብልጽግና ውዝግብ፤ ተፈናቃይ ዜጎች የመንግስት መከራው

March 21, 2023

ጤና ሚኒስትር “ደግፉኝ” ሲል ለወገን ጥሪ አቀረበ

December 15, 2021

በአራት መጋዘን የተከማቸ የምግብ ዘይት በነዋሪዎች ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ

March 7, 2022

የፀጥታ ስጋት ዝርፊያና ሌብነት በትግራይ “ከጦርነቱ በላይ የከበደን ዘረፋ ሆኗል”

June 4, 2022

ባደጉት ሀገሮች የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ የሚቀመጠው ግብ ግልጽ እንደሆነ የሚናገሩት የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ “የብሔራዊ ባንክ ከ20 በመቶ በታች ስላለ በጣም አስቸጋሪ ነው። 18፣ 17፣ 16…አይታወቅም” ሲሉ ይናገራሉ።

የዋጋ ግሽበት በ19.9 በመቶ እንኳ ቢወርድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕቅዱን “አሳክቻለሁ ሊል ይችላል” የሚሉት ዶክተር አብዱልመናን የታየው ለውጥ ወደ ዕቅዱ የሚመራ ቢሆንም ብዙ እንደሚቀር አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕቅድ በነሐሴ 2015 ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት ከዋጋ ግሽበት በተጨማሪ የበጀት ጉድለት፣ የገቢ እና ወጪ ንግድ ሚዛን መዛባት በመሳሰሉ ሥር የሰደዱ ፈተናዎች በተቸገረበት ወቅት ነው።

ዕቅዱን ለማሳካት ብሔራዊ ባንክ ይወስዳቸዋል ከተባሉ እርምጃዎች መካከል ለመንግሥት የሚሰጠውን የቀጥታ ብድር በመቀነስ ከ2015 አኳያ “ከሲሶ (ከ1/3ኛ) እንዳይበልጥ” መገደብ ይገኝበታል። ይሁንና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሪፖርቱን በወቅቱ ለሕዝብ ይፋ ባለማድረጉ ቃል በገባው መሠረት ለመንግሥት የሚሰጠውን ብድር መገደቡን ማረጋገጥ እንደማይቻል ዶክተር አብዱልመናን ገልጸዋል።

ብሔራዊ ባንክ በገበያው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን በመቀነስ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ሲነሳ የተከተለው ሌላው እርምጃ ባንኮች የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ ያነጣጠረ ነው።

የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ባንኮች የሚሰጡት ብድር ባለፈው ዓመት ካቀረቡት ከ14 በመቶ እንዳይበልጥ ገድቧል። ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ሲያጋጥማቸው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሚወስዱት የአስቸኳይ ጊዜ ብድር የሚከፍሉት ወለድ “ከ16 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ” ብሏል።

በሚያዝያ 2016 አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 23.3 በመቶ ሆኖ የተመዘገበው የገንዘብ አቅርቦት ዕድገትን ለመግታት በተወሰደው እርምጃ ምክንያት እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ቅዳሜ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።

ላለፉት ዘጠኝ ወራት ገደማ ብሔራዊ ባንክ የተከተለው እርምጃ የዋጋ ግሽበትን በ2017 ሰኔ ወር ከ10 በመቶ በታች ለማውረድ ጭምር የተወጠነ ነው። አቶ ማሞ ምኅረቱ ባለፈው ሣምንት “ኢትዮጵያ ታምርት” በተባለው ንቅናቄ መድረክ ላይ ተገኝተው ሲናገሩ በዋጋ ግሽበት ላይ የታየው ለውጥ ብሔራዊ ባንክ የወሰዳቸው እርምጃዎች ውጤት እንደሆነ ገልጸዋል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረበት 36 በመቶ ወደ 18 በመቶ ዝቅ ማለቱን የጠቀሱት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይኸም የመንግሥታቸው “የተጠናከረ እና የተቀናጀ እርምጃ” ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

“ያሰብንውን አሳክተናል ብለን ነው የምንወስደው” ያሉት የብሔራዊ ባንክ ገዥ “በተለይ core inflation ላይ የሞነተሪ ፖሊሲ ውሳኔያችን ግልጽ የሆነ ውጤት አምጥቷል ብለን እናምናለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

ይኸ ይዘት የሚያነቡት ጽሁፍ አካል ነው። አቅራቢው Twitter ይዘቱን የሚያቀርብ ሲሆን አጠቃቀምዎን የተመለከተ መረጃ “ይዘቱን አሳይ” የሚለውን ሲጫኑ በቀጥታ ሊሰበስብ ይችላል።.

በዋጋ ግሽበት ላይ የታየው ለውጥ ለብሔራዊ ባንክ አዎንታዊ ትርጉም የሰጠ ቢሆንም ሸማቾች ግን የተለየ ፋታ የሚያገኙበት አይደለም። የዋጋ ግሽበት የሚገኝበትን ደረጃ ለማወቅ የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ ሲሰራ የናሙና አወሳሰድ፣ የሚሰላበት መንገድ እና ትንታኔው ሸማቾች በለት ተለት ግብይት የሚገጥማቸውን ያሳያል ወይ የሚለው ጉዳይ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።

በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ መሠረት ምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት በሚያዝያ ወር 27 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ2015 ሚያዝያ ወር አኳያ ዳቦ እና ጥራጥሬ 35.3 በመቶ፣ አትክልቶች 34.2 በመቶ፣ ሥጋ 25.2 በመቶ  የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል።

ወተት፣ አይብ እና እንቁላል የመሳሰሉ የምግብ ግብዓቶች የመሸጫ ዋጋ 18.3 በመቶ ሲጨምር ዘይት 12.2 በመቶ፣ ፍራፍሬ 6.7 በመቶ እንዲሁም የምግብ ምርቶች 21.6 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል።

የዋጋ ግሽበት የሚቀንስበት ፍጥነት “በጣም በዝግታ ነው” የሚሉት ዶክተር አብዱልመናን ለውጡ በአፋጣኝ በሸማቾች ላይ የሚንጸባረቅ እንዳልሆነ ያስረዳሉ።

“ሸማች ሊመገባቸው የሚችላቸው ወይም ወጪ ሊያወጣባቸው የሚችላቸው ነገሮች ይደመሩና በዚያ ላይ ተመርኩዞ [የዋጋ ግሽበት ምጣኔ] ይሰላል” የሚሉት ዶክተር አብዱልመናን የስሌቱ መሠረት የሆነው የምግብ ቅርጫት “ለሁሉም ሰው ላይሠራ ይችላል” ሲሉ እንደ ሰዉ አቅም እና ፎጆታ እንደሚወሰን አስረድተዋል።

የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ብሔራዊ ባንክ ገቢራዊ ካደረጋቸው እርምጃዎች መካከል ባንኮች የሚያቀርቡትን ብድር ለመገደብ የተላለፈው ውሳኔ በአዲስ አበባ የሪል ስቴት ገበያን ሲያንገጫግጭ ታይቷል።

ከ2015 ሚያዝያ ወር አኳያ ዳቦ እና ጥራጥሬ የ35.3 በመቶ፣ አትክልቶች የ34.2 በመቶ፣ የሥጋ 25.2 በመቶ  የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል።

ባንኮች የሚሰጡት ብድር ላይ በተጣለው ገደብ ምክንያት በሪል ስቴት ገበያ የገዢዎች ፍላጎት የተቀዛቀዘ ሲሆን የመሸጫ ዋጋም የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል።

“በተለይ በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ዋጋ እንዲጨምር ያደረገው ከባንክ የሚገኝ መጠነ ሰፊ ብድር ነው” የሚሉት ዶክተር አብዱልመናን “ነጋዴዎች ለንግድ ብለው ብድር ይወስዳሉ፤ ወደ ሪል ስቴት ያውሉታል። ያ ገንዘብ ደግሞ የመኖሪያ ቤትን ዋጋ እያናረው መጣ” ብለዋል።

የሀገሪቱ ትልልቅ ኩባንያዎች በዋንኛነት የከተሙበት የአዲስ አበባ የሪል ስቴት ገበያ ባለፉት ዓመታት በገዢዎች ፍላጎት እና የመሸጫ ዋጋ ዕድገት ሲታይበት ቆይቷል።

ባንኮች ሲያቀርቡት ከቆዩት ከፍ ያለ ብድር በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች ዋና ከተማዋ የሀገሪቱ ዜጎች ተመራጭ ማረፊያ መሆኗ የመኖሪያ ቤቶች የመሸጫ ዋጋ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። ዘርፉ የከተማዋን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት መሙላት ባይችልም የዕድገቱ ዘላቂነት በበርካታ ባለሙያዎች ጥያቄ የሚነሳበት ሆኖ ቆይቷል።

“የአሴት ዋጋ እና የገንዘብ አቅርቦት (ብድር) በየትኛውም ዓለም በቀጥታ የተገናኙ ነገሮች ናቸው” የሚሉት ዶክተር አብዱልመናን ብሔራዊ ባንኮች ብድር በከፍተኛ መጠን እንዲቀርብ ሲፈቅዱ የመኖሪያ ቤት ዋጋ እንደሚጨምር ያስረዳሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን የመሳሰሉ ተቋማት ቆንጠጥ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ መከተል ሲጀምሩ በአንጻሩ የመኖሪያ ቤት የመሸጫ ዋጋ ይቀንሳል። በኢትዮጵያም የሆነው ተመሳሳይ እንደሆነ የተናገሩት ዶክተር አብዱልመናን “አሁን ብድር በገፍ አይገኝም። በገፍ ብድር ስለማይገኝ ግንባታውም ተቀዛቀዘ ገዢውም የለም” ሲሉ ተናግረዋል።

እሸቴ በቀለ ታምራት ዲንሳ DW

ECONOMYNEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Ethiopian MP Rebukes Egyptian Media’s Misinformation Campaign Against GERD
አሜሪካ ለኢትዮጵያው ከንግግርና ውይይት ውጭ አማራጭ የለም አለች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2